tgoop.com/Apostolic_Answers/3212
Last Update:
የእለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን
ሐዋ ሥራ - 15(ሙሉዋን)
- አንዳንዶች ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው ወደ ክርስትና የሚመጡትን አይሁድ ትገረዙና የሙሴንም ሕግ ትቀበሉ ዘንድ ግድ ነው አሉ(አስቀድማችሁ በሥጋ አይሁድ መሆን አለባችሁ ነው)
- ያኔ ከጳውሎስ እና በርናባስ ከሌሎችም ጋር ክርክር ሆነ ስለዚህም ይህንን ለመፍታት ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሐዋርያቱና ሽማግሌዎች(ጳጳሳት) ሄዱ
- በዚያም የሆነውን ነገር ሁሉ ከሰሙ በኋላ ሐወርያቱና ሌሎችም ተሰብስበው አሕዛብ ላይ ሊያከብዱባቸው እንደማይገባና ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት እንዲሁም ከታነቀ እና ከደም ይርቁ ዘንድ አዘዙ
- ሐዋርያቱም ይህንን ጽፈው ለይሁዳና ለሲላስ(ነቢይ ነበሩ ማለትም ሰባኪያን ማለት ነው የእግዚአብሔርን ነገር ገልጠው የሚያስተምሩ) ለነ ሲላስ ሰጥተው ከነ ጳውሎስ ጋር ወደ አንጾኪያ ላኳቸው.. ይህንንም ደብዳቤ ያነበቡ ሁሉ ደስ አላቸው..
- ሌሎች ወደ ይሁዳ ሲመለሱ ሲላስ እዛው በአንጾኪያ ቀረ ጳውሎስና በርናባስም በዛው በአንጾኪያ እያስተማሩ ተቀመጡ..
- ጳውሎስ በሐዋርያዊ ጉዞው ላይ ከበርናባስ ጋር ሆኖ የጌታን ቃል የተናገረበትን አብያተ ክርስቲያናት ተመልሰው እንዲጎበኟቸው ለበርናባስ ይነግረዋል..
- በርናባስ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ማርቆስን ሊያስከትል ያስባል.. ጳውሎስ ግን ደስተኛ አልሆነም.. ምክንያቱም በመጀመሪያው ጉዞዋቸው ላይም አስከትለውት ጵንፍልያ ላይ ሲደርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ጥሏቸው ሄዶ ነበርና..
- በዚህም ምክንያት በርናባስና ጳውሎስ ተለያዩ
መልካም ውሎ
@Apostolic_Answers