አዲስ ቲቪ Adiss Tv AMN
Photo
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።
አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ አቶ ተወልደ በፈቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታውቋል።
አየር መንገዱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ አቶ ተወልደ ላለፉት ስድስት ወራት ህክምናቸውን በአሜሪካ ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውሷል፡፡
አቶ ተወልደ ገብረማርያም በጤና እክል ምክንያት የአየር መንገዱ ዋና አስፈጻሚ ሆነው መቀጠል እንደማይችሉ በመግለጽ ለስራ አመራር ቦርዱ የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባው አቶ ተወልደ ያቀረቡትን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉን አስታውቋል፡፡
የስራ አመራር ቦርዱ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ምትክ ለአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጸሚ በቅርቡ እንደሚመድብም ነው የተገለፀው።
አየር መንገዱ በመግለጫው አቶ ተወልደ ከአንድ አስርት ዓመታት በላይ ተቋሙን በመሩበት ወቅት ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን አመልክቷል።
በእርሳቸው አመራር አየር መንገዱ በሁሉም መለከያ የተለየ ስኬት ማስመዝገቡን በመጠቆም ዓመታዊ ገቢው ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተነስቶ አሁን ላይ ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መብለጡን ጠቁሟል።
33 የነበሩት የአውሮፕላን ቁጥሮችም ወደ 130 ማደጋቸውን እና በዓመት የሚያስተናግደው የመንገደኞች ቁጥር ከ3 ሚሊየን ወደ 12 ሚሊየን ከፍ ማለቱን አስታውቋል።
በአጠቃላይ በእርሳቸው አመራር አየር መንገዱ በአራት እጥፍ አድጓል ያለው መግለጫው፥ 700 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያወጡ ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን አየር መንገዱ የገነባው በእርሳቸው አመራር መሆኑን በመግለፅም፥ በአፍሪካ ትልቅ የሚባል ሆቴል፣ የካርጎ ተርሚናል፣ የአቭዬሽን አካዳሚ እና የበረራ ሲሙሌተሮች መገንባታቸውን ለአብነት ጠቅሷል።
መግለጫው አክሎም የስራ አመራር ቦርዱ፣ ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተሰብ ለዚህ አስተዋፅኦዋቸው ከፍ ያለ ምስጋና እንዳላቸው በመግለፅ መልካም ጤናን ተመኝቷል።
@Addis_Tv

አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ለብዙ ዓመታት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት በመምራት ለዕድገት እንዲበቃ መሰረት የጣሉ፣ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ልምድ ያላቸውና በዘርፉ ስኬታማ መሪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ የአየር መንገዱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው አየር መንገዱን ለበለጠ ስኬት ሊያበቁ የሚችሉና ተቋሙ ወደፊት ከሚጠበቅበት የዕደገት ደረጃ ሊያደርሱት እንደሚችሉም የታመነ መሆኑንም አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም በሚሰጡት በሳል አመራርና ትክከለኛ ውሳኔ ሰጭነት ውጤታማ መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡
አቶ ግርማ ዋቄ ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተምረውና አድገው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ለ34 ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አቶ ግርማ በመካከለኛው ምስራቅ የገልፍ አየር መንገድንና ዲኤቾ ኤል ኩባንያንም በኃላፊነት አገልግለዋል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2004 የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው አየር መንገዱን ለሰባት ዓመታት ያህል በዋና ስራ አስፈጻሚነት በመምራት ለዕድገት አብቅተውታል፡፡
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለቀቁ በኋላም በተለያዩ አገራት የአየር መንገድ ከፍተኛ አመራርና የአየር ትራንስፖርት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾመዋል፡፡
የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በገዛ ፈቃዳቸዉ ስራ መልቀቃቸውንና አዲስ የተመሰረተውን ቦርድ አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም አቶ ተወልደ ላለፉት 6 ወራት ህክምናቸውን በአሜሪካ ሲከታተሉ መቆየታቸውን ጠቁመው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ትናንት የተቋቋመው አዲሱ ቦርድ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ በምስጋና አሰናብቷቸዋል ብለዋል።
ይህን ተከትሎም ቦርዱ አቶ መስፍን ጣሰውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙን ተናግረዋል።
አቶ መስፍን ጣሰው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።
ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮም የአየር መንገዱ ስራ አመራር ቦርድ ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ከዚያ በመቀጠል የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 በመቶ ድርሻ ያለበትን አስኪ አየር መንገድን ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን በመምራት ላይ ነበሩ።
ከዚህ ባለፈም እስከትናንት ወዲያ በስራ ላይ ያለው ቦርድ በአዲስ አመራር መተካቱን አቶ ግርማ ዋቄ ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም፡-
** አቶ ተክለወልድ አጥናፍ ፣
** አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣
** ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣
** አቶ ታደሰ ጥላሁን እና
ሁሉንም ሰራተኛና ማኔጅመንት የሚወክሉና በሰራተኞች ተመርጠዉ የቦርድ አባላት የሚሆኑት እስከሚተኩ ድረስ
** አቶ ረታ መላኩ
** አቶ አለማየሁ አሰፋ
የአዲሱ ቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ያለአግባብ ተከማችቶ የተገኘዉ 341ሺ ሊትር ዘይት ለህብረተሰቡ ማከፋፈል መጀመሩን ከተማ አስተዳደሩ አሰታወቀ።
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አካባቢ ያለአግባብ ተከማችቶ የተገኘዉ 341ሺ ሊትር ዘይት በህብረተሰቡ ጥቆማ ተይዞ እንደነበር ይታወቃል።
በአሁን ሰዓት በጉለሌ ክ/ከተማ ባሉ 12 ሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እና በአንድ ዩኒዬን በኩል ባሉ የሸማች ሱቆች በማስገባት ለህብረተሰቡ ማሰራጨት ተጀምሯል።
ከፍተኛ መጠን ያለው የዘይት ክምችት በሁሉም የሸማች ሱቆች ስርጭቱ የጀመረ ሲሆን ህብረተሰቡም በአከባቢዉ ባሉት የሸማች ሱቆች በመሄድ መግዛት እንደሚችል የክ/ከተማው ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስታውቋል።
ሌሎች ምርቶችን የሚያከማቹና በቂ መረጃ ማቅረብ ያልቻሉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሎ የምርመራ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

ከ21 በላይ የሚሆኑ የታሸገ ውኃ አምራች ፋብሪካዎች ስራ ማቆማቸው ተገለጸ።
ውሃ አምራች ፋብሪካዎች ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፣ ጉሙሩክ ኮሚሽን እና አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
በመላ ሀገሪቱ 134 የሚሆኑ የታሸገ ውኃ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በተለያዩ ምክንያቶች 21 የሚሆኑ ፋብሪካዎች ስራ ማቆማቸው ተገልጿል።
የቀሩት ፋብሪካዎችም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ እንዳልሆነ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
የጥሬ ዕቃ ዋጋ መጨመር እና በሽያጭ ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝን አለመጠቀም፣ የጉምሩክ ቀረጥ በኢንቮይስ መሰረት አለመስተናገድ፣ የታሸገ ውኃ መጠጥን እንደ ቅንጦት በመውሰድ አላስፈላጊ የሆነ የኤክሳይስ ታክስ ጫና መፍጠር እና ለአምራቹ የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ አለመስጠት ለስራቸው ተግዳሮት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ቸርቻሪው አምራቹ ከጨመረበት ዋጋ ዉጪ ከሶስት እጥፍ በላይ ዋጋ በመጨመር ለኑሮ መወደድ ዋና ተዋናይ እየሆነ ነው ሲሉም አምራቾቹ ቅሬታ አቅርበዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ገመድ አልባ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሪያ ቤት አቀረበ
ኢትዮ ቴሌኮም ገመድ አልባ 4ጂ ብሮድባንድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ለመኖሮያ ቤቶች ማቅረቡን አስታወቀ።የድርጅቱ ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በሰጡት መግለጫ፤ የአሁኑ አገልግሎት ከዚህ በፊት በገመድ (ፋይበርና ኮፐር) ሲሰጥ የቆየውን አግልግሎት ፈጣን በሆነና በተሻለ ጥራት ገመድ አልባ በሆነ መልኩ አግልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።
እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ማብራሪያ፤ አገልግሎቱ ደንበኞች በመኖርያ አካባቢያቸው አልያም በመረጡት ስፍራ 4ጂ የሞባይል ኔትዎርክን በከፍተኛ ፍጥነት የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል አማራጭ ነው።ይህ አገልግሎት በተለይም የፋይባር እነ ኮፐር ገመዶች በማይደርሱባቸው የመኖሪያ አካባቢዎች ተመራጭ መሀኑን ወ/ት ፍሬህይወት ገልጸዋል።ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ተገድቦ የነበረውን ድርጅቱ ባደረገው የማስፋፊያ ተግባር የ4ጂ አገልግሎትን 136 ከተሞች አግልግሎት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ወይዘሪት ፍሬህይወት ገልፀዋል።

''ኤችአር 6600 ከፀደቀ የኢትዮጵያና የአሜሪካን ግንኙነት የሚሽር ነው'' ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ የኤች አር 6600 ፍላጎት እስካሁን በኢትዮጵያ የተሠሩ መልካም ተግባራትን ኹሉ የሚክድና የሚሸረሽር ነው ብለዋል።
በሳምንቱ ከኤች አር 6600ና ኤስ 3199 የተባሉ አደገኛ ረቂቅ ሕጎች እንዳይጸድቁ ዳያስፖራው በተቀናጀ የአንደነት ዘመቻ እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የውጭ ጣልቃ ገብነት በበቃ ወይም No more ዘመቻ እንዳከናወነ ኹሉ ኤች አር 6600ና ኤስ 3199 የተባሉ አደገኛ ረቂቅ ሕጎች መመከት እንዲችሉ ተወያይተዋል ብለዋል።
በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር የኹለትዮሽ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡
"ከዒድ እስከ ዒድ" ታላቁ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ መርኃግብር የተሳካ እንዲኾን በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን ግጭት ማቆሙን ገለፀ።
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫውም መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ሰለመወሰኑ የወጣ መግለጫ
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ የአየር በረራዎች ቁጥር እንዲጨምር እንዲሁም ለእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ የሚቀርብበትን ስርዓት የተሳለጠ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማደረስ እንዲችሉ የአየር በረራ ተመቻችቷል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በአብአላ-መቀሌ የየብስ ትራንስፖርት መስመር በኩል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መድረስ እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደ አጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑ እየተስተዋለ ነው። በዚህም በትግራይ አጎራባች ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል የሚመጡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ዜጎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እያሳዩ ያለው በጎ ተግባር በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መንፈስ የሚያሳይ ነው። መንግስት እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲደርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንድሚቀንስ በጽኑ ያምናል።
በመሆኑም መንግስት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎቹን ችግር በአፋጣኝ የመፍታት ኃላፊነቱ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።
በዚህም መሠረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህ አጋጣሚ መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ ያቀረባል።
የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል። ይህ የመንግስት ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ መሆኑን መንግስት ያምናል። ይህ በመንግስት በኩል የተላለፈው ውሳኔ አላማው የአስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ በነጻነት ተጓጉዞ ለእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ለመድረስ እንዲችል ነው። በመሆኑም ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚችል ብሎም በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ከንቲባ አዳነች በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የጓሮ አትክልት ንቅናቄን አስጀመሩ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ "ምግባችን ከጓሮዋችን" በሚል መሪ ቃል የጓሮ አትክልት ልማት ንቅናቄን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ከንቲባዋ በአንድ አርሶ አደር ማሳ በመገኘት የጓሮ አትክልት ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት ለየት ያለ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡
የከተማ ግብርና በብዙ ታላላቅ ሃገራት የተለመደ መሆኑን አውስተው በእኛ አገር ደግሞ በብዙ መንገድ የተሸልን በመሆናችን ትንሽ ግብአትና ስልጠና ብናክልበት የከተማ ግብርናን ማስፋፋት እንችላለን ብለዋል።
በተለይም ለአዲስ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ ከሩቅ ቦታ እንደምታገኝ አስታውሰው ፤በዚህ ሂደት ከተማ እስኪደርስ ተበላሽቶ ከመድረሱም በላይ ዋጋውን እንደሚያንረው መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪንና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘም ተደርጎ አንደነበርም አይዘነጋም፡፡
አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን ገልጿል፡፡
ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ዜጎች ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህልን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነው እንዲሻገሩ ጥሪ ማቅረቡን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ በህወሓት አሸባሪ ቡድን ለተፈናቀሉ የአማራና አፋር ክልሎች ዜጎች 18 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ ማሰባሰቡን አስታወቀ፡፡
ድጋፉም ምግብ፣ የቤት መስሪያ ቁሳቁስ፣ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ፣ የቤትና የህክምና ቁሳቁስን ያካተተ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሀላፊ አቶ መለሰ አባተን ጨምሮ የተለያዩ የሊጉ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
አቶ መለሰ ዓለሙ ፥ “ወጣቶች በየዘመኑ የሚሰጣቸው ተልዕኮ አለ፤ የዚህ ዘመን ወጣቶች ተልዕኮ ደግሞ ሀገርን ማዳን ነው” ብለዋል፡፡
“በዚህ ወቅትም ለሀገራችን አለን በማለታችሁ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል” ነው ያሉት፡፡
የገጠሙንን ፈተናዎች በጋራ በመረባረብ እናልፋቸዋለን ያሉት አቶ መለስ ዓለሙ ፥ “ምንም እንኳን ብዙ ፈተናዎች ቢገጥሙንም ከትናንትናው አይብሱም እንሻገራቸዋለን” ነው ያሉት፡፡
“ከወጣቱ ብዙ ይጠበቃል የተጀመረው ተግባር አርዓያ የሚሆን ነው፤ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባልም” ብለዋል፡፡
የተሰበሰበው ሀብት ከዛሬ ጀምሮ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንደሚሰራጭ ተነግሯል፡፡

ለደህንነት አገልግሎት የሚገጠሙ ካሜራዎችን የሰረቁ እና ንብረቶቹን የገዙ ግለሰቦችን ይዞ ንብረቶቹን ማስመለሱን ፖሊስ አስታወቀ
996 ሺ ብር የሚያወጡ ለደህንነት አገልግሎት የሚገጠሙ ካሜራዎችን የሰረቁ እና ንብረቶቹን የገዙ ግለሰቦችን ይዞ ንብረቶቹን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገኘው ሲ.ጀ.ሲ.ኦ.ሲ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ 996 ሺ ብር የሚያወጡ 41 ለደህንነት አገልግሎት የሚውሉ ካሜራዎችን እና 36 የካሜራ መደገፊያዎችን የሰረቁት ተጠርጣሪዎችንና ካሜራዎች በ41 ሺ ብር የገዙ ሁለት ተቀባይ ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት ሁለት ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በድርጅቱ ውስጥ በቀን ሰራተኝነት ሲሰሩ እንደነበር እና የድርጅቱን መግቢያና መውጫ ካጠኑ በኋላ የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ወንጀሉን እንደፈፀሙ በምርመራ መረጋገጡን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ግለሰቦቹ ወንጀሉን በፈጸሙ በአስረኛው ቀን ድርጅቱ ንብረቶቹን መሰረቁን ተገንዝቦ ለፖሊስ ሪፖርት እንዳደረገና ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የወንጀሉ ሪፖርት በደረሰው በሦስተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ንብረቶቹን በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሮባ ዳቦ ቤት አካባቢ ከሚገኙ ከሁለት ግለሰቦች አስመልሶ ምርመራውን መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ የተለያዩ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን የሚቀበልበት የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በውይይቶቹም በርካታ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ግብአቶችን ማሰባሰብ መቻሉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ሆኖም አሁንም ህብረተሰቡን ለማዳመጥ ተጨማሪ አማራጮችን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ካለበት ሆኖ ጥቆማዎችን መስጠት የሚችልበት የስልክ ቁጥሮችን አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ ማንኛውንም ቅሬታና ጥቆማዎችን በነፃነት የሚሰጥባቸው የጥቆማ መስጫ የስልክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት!
አጭር ቁጥር ፡- 👉 9977
የሞባይል ስልኮች
👉 09-00640830
👉 09-00640789
አስፈላጊ የሰነድ መረጃዎችን በቴሌግራም ለማያያዝ እና ለአጭር መልእክቶች( text messages) የሞባይል ቁጥሮችን መጠቀም እንደሚቻል ተገልጿል።

ኦፌኮ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የፓርቲው መደበኛ ጉባኤው ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተውጣጡ የፓርቲው አባላትና ሃላፊዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ አዳዲስ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለጂቡቲ ገበያ ለማቅረብ ተስማሙ
የመጀመሪያው የኢትዮ-ጅቡቲ የአትክልትና ፍራፍሬ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ፍራፍሬና አትክልት ላኪዎች ከ20 በላይ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለጅቡቲ ገበያ ለማቅረብ ተስማምተዋል።
በኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር የተዘጋጀው የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት ክፍተቶችን ለመገምገም እና ወደ ጅቡቲ የሚላኩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማሻሻል ጠቃሚ መድረክ ሆኖ አገልግሏል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አቶ ቢንያም ኤፍሬም፣ ከጅቡቲ ንግድ ምክር ቤት አቶ ሲያድ አሊ ሀሰን እና አቶ ቴዎድሮስ ዘውዲ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ወደ ጅቡቲ የሚላከውን ምርት ለማሳደግ የሚያስችሉ አሰራሮችን ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተለይ አሁን ባለው የአለም የምግብ ቀውስ ወቅት የክልላዊ ንግድን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የጅቡቲ የልዑካን ቡድን በመጪዎቹ በቅርቡ በቢሾፍቱ እና በቆቃ እርሻዎችን ጉብኝት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም ትኩረቱን በመካከለኛና ትላልቅ የማምረቻና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቴክኖሎጂን መጠቀም፣ መቅዳትና ማላመድን መሠረት ያደረገ የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በማውጣት የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
በፖሊሲው አፈጻጸም ሂደት የተገኙ ውጤቶች ቢኖሩም መሰረታዊ ለውጥ ከማምጣት አንፃር ስኬታማ እንዳልነበር ከተደረጉ ጥናቶች መረዳት ተችሏል፡፡
በመሆኑም ለአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ልማት ልዩ ትኩረት የሚሰጥ፤ የኢንተርፕራይዞችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ ከምርታማነታቸው ጋር ያላቸው ትስስር የሚያጠናክር፤ ለፈጠራ ስራ /Innovation/ ትኩረት የሚሰጥ ፖሊሲ በማስፈለጉ፣ ከግብርና እና ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና አይሲቲ ለአገራዊ ብልጽግና መሰረት ተደርገው በመወሰዳቸው በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲታገዙ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፣ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ለውጦች እና ፍላጎቶች ምላሽ መስጠት የሚችል እና የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማትን የሚያፋጥን ሁሉአቀፍ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ታምኖበታል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ግብዓቶች በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
2. ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው የ11 የአስፈጻሚ ተቋማትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ሲሆን በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 መሰረት፡-
• የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣
• የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣
• የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣
• የኢትዮጵያ ደን ልማትን ሥልጣን፣
• የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት፣
• የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣
• የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት፣
• የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና
• የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት
አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል ያጸደቀ ሲሆን ደንቦቹ በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ምክር ቤቱ ወስኗል

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 82 የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መረቁ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የጤና፣ የትምህርት፣ የስፖርት ማዘውተሪያን ጨምሮ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 82 የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መረቁ።
በክፍለ ከተማው የተመረቁት 82 ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
ግንባታቸው ተጠናቆ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የጤና ተቋማት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የተማሪ ምገባ አዳራሾች፣ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ኢዜአ ዘግቧል።
ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ አጠቃላይ 162 ሚሊዮን ብር ወጪ መደረጉ ታውቋል።
በመሆኑም የፕሮጀክቶቹ ምርቃት ከንቲባዋን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ በተገኙበት ተከናውኗል።