tgoop.com/tseomm/6820
Last Update:
የአ/ምንጭ ዝጊቲ አቡዬ ቤተክርስቲያንን ከ1ቢሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየገነባች ለምትገኘው እህታችን የጋሞ ኦቾሎ ኦርቶዶክሳዊ ሴቶች የአደራ እና የቤተሰባዊ ክብር ሽልማት ባህላዊ አልባስ አጎናጸፉ።
***
በጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም ምልጃ እና ረድኤት በቅድስት ሥላሴ ምህረት በሥጋ ደዌ ከሚያሰቃያት የጡት ካንሰር የአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ጸበልና ዕምነት በመጠቀም የመዳኗን ቸርነት ምክንያት አድርጋ
በተሰጣት ቀሪ ዕድሜ ከተረፋት ላይ ሳይሆን ያላትን አፍስሳ ከ1 ቢሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ13 በላይ ግዙፍ የእንግዳ አዳራሽ፤መንበረ ጵጵስና፣የልዩ እንግዳ ማረፍያ፣የግብር ቤት፣ማስመስከርያ አብነት ትምህርት ቤት ፣የማኒፋክቸር ማቀነባበርያ አዳራሽ፣ሼሮል፣ድልዲህ፣የጸበል ቤት ጨምሮ በማነጽ እያገለገለች የምትገኘው እህታችን እና ቤተሰቧ
በአንዳንድ የሥጋ ዝለት በአገልግሎቷ እንዳትደክም የአደራ ቃል ከጋሞ ኦቾሎ ኦርቶዶክሳዊ ሴቶች የተሰጣት ሲሆን እርሷ ላይ የሚደረገው ማንኛውም አይነት ነገር ከአንድ የጋሞ ሴቶች ላይ እንደሚደረግ በመግለጽ ከሴቶች መሃከል እንደ አንዷ እንደሆነች እራሷን እንድትመለከት የጋሞ ብሔረሰብ የክብር ልብስ ብፁዑ አቡነ ኤልያስ በተገኙበት በአውደምህረት ላይ አልብሰዋታል።
ይህ መርህ ግብር በዋናነት እህታችን እያከናወነችው ለሚገኘው መንፈሣዊ አገልግሎት ስንቅ እና መጽኛ ይሆናት ዘንድ የተደረገ የእህትነት ድጋፍ ነው።
መርኃግብር የተከናወነው የኡሞ ላንቴ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ምረቃ በሚከናወንበት ሲሆን የእህታችን አገልግሎት በጋሞና አከባቢ ዞኖች ውስጥ ጉልህ ሚና ያለው ነው።
አገልጋይ እንዳይዝል በጎውን እያሰቡ ማበርታት አገልግሎትን ማስቀጠል ነው። እግዚአብሔር ያጽናሽ ያበርታሽ!!!
እህታችን እና ቤተሰቧን በጸሎታችሁ አስቧት
©Kune Demelash kassaye -Arba Minch
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6820