tgoop.com/tseomm/6619
Last Update:
አንተ! የሃይማኖት ችግር እንደሌለብህ፣ አፈንጋጭም እንዳልነበርክ አውቃለሁ፤ እስከዛሬም በአንተ ላይ ምንም ዓይነት የሀይማኖት ነቀፋ አይቼ አላውቅም። ነገር ግን በቅርቡ የተፈጠረው ነገር የሚያኮራ ሳይሆን በእጅጉ የሚያሳፍር መሆኑን አንተም ታውቃለህ። ለእኔ ከደረሰኝ ሰነባብቷል ። ይህ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም። ሰው ያየው ከብዙ ጥቂቱ ነው። አንተ የግልህን ጉዳይ በንስሃ ታጥባለህ። ከጥፋትህ ማግስት በምታደርገው ተግባር ግን ይባሱኑ የተሸከምከው ክህነት በሰው ልቦና ውስጥ ክፉኛ ዋጋ ያጣል፤ መሳንክልም መሆን ነው። ሌሎቹ ዲያቆናትና ካህናት ዋጋ ቢስ የነወሩ ሆነው ይታሰባሉ።
የጥሞና ጊዜ ውሰድ!
ስለዚህ፣ የጥሞና ጊዜ ውሰድ። በክህነትህ ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋገር። አማን ሻሎም እንኳን ፕሮቴስታንቱን መንፈቅ አርፎ ነው የተመለሰው። አንተ እንዴት በሳልስትህ ብቅ ትላለህ? ይህ ፈጽሞ ነውር ነው። እንደ እህት የምመክርህ፣ የተቀበልከውን ታላቅ ኃላፊነት አክብረህ አስከብር!ለቤተክርስቲያን ክብርህ ተጨነቅ!
በቲክቶክ አጥቢያ ያላችሁ ካህናትና መምህራን፣ እንዲህ ዓይነቱን ነገር እያያችሁ እንዴት ዝም ብላችሁ ታያላችሁ? ገስጻችሁ ከማስተካከል ዝም ማለታችሁ የራሳችሁን ክህነት እንደሚያቃልል አታውቁም? ለቤተክርስቲያን ክብሯ ለሆነው ክህነቷ ካልተጨነቃችሁ ምን ትሰራላችሁ? ፍትሀ ነገስት አንቀጽ 6 ምን ይላል?
...
ሌሎቻችሁን ወጣቶቹን እረዳችዃለሁ ''ሽታዬ! ሽታዬ!'' እየተባባላችሁ ነው።
©ማርያማዊት አባተ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6619