tgoop.com/tseomm/6565
Last Update:
የፍጥረት ሁሉ ደስታ - ልደታ ለማርያም
ግንቦት አንድ ቀን የእመቤታችን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ በፍጹም ደስታ ያሳለፉት ቀን ነው፡፡
የልደቷ ቀን የሐና የደስታ ዕለት ነበር፤ "አንች ያልወለድሽ መካን ሆይ ደስ ይበልሸ የሚለውን ቃል ሰምታበታለችና" /ኢሳ 54፤1/፡፡ የልደቷ ቀን የኢያቄም የደስታ ዕለት ነበር፡፡ ከዕሴይ ግንደ በትር ይወጣል /ኢሳ 11፤1/ የሚለው ቃለ ነቢይ በውድ ልጁ ሲፈጸምና በበትሩ ሠራዊተ አጋንንትን ሲርቁ አይቷልና፡፡
በእርሷ ልደት ነቢያት ሁሉ ተደስተዋል፡፡ ትንቢታቸው ፍጻሜ ሲደርስ ፤ የንባባቸው መንፈሰ ሲገለጥ፣ ሕግ ለጸጋ፣ ኦሪት ለወንጌል ሊያስረክቡ፣ ነገደ ሌዊ ሊቀ ካህንነቱን ለነገደ ይሁዳ ሊያስረክብ ሲሰላለፉ አይተዋልና፡፡ የእርሷ ልደት የያዕቆብ ፍጹም ደስታ ነበረ፡፡ በሕልሙ ከመሬት እስከ ሰማይ ተዘርግታ ያያት መሰላል በእውን ከምድር ወደ ላይ በቅድስና ስትደርስ ለማየት በቅቷልና፡፡ ራስዋ ላይ እግዚአብሔር የተቀመጠባት እውነተኛዋ መሰላላችን በርግጥም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው/1ኛ ቆሮ 11፤1/ አለ፡፡ የእርሷ ራስ ግን ያዕቆብ እንዳየው እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ያለችው ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራሰ ያለው ወንድ በእርሷ ዘንድ ስላልነበረ ነውና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ልዩ መሆኗን ስለሚያውቅ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሺ፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ጽንስሽም እንደ ሌሎቹ ሴቶች አይደለም እያለ ሲሰግድላትና ሲያመሰግናት እርሱን አልፋ ለእግዚአብሔር መቀመጫ ዙፋን ማደሪያ መቅደስ መሆኗን ያየው አባታችን ያዕቆብ በእውነት ደስ አለው፡፡
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የተቤዠለትን አማናዊ በግ ይዛለት የምትወርደውን ዕፀ ሳቤቅ ተወልዳ አይቶ ደስ አለው፡፡ እርሷ ስትወለድ ያች ያያት ቀን መድረሷን አውቆ ፍጹም ደስ አለው፡፡ ይስሐቅም ከታሰረበት ያስፈታችውን ስለእርሱ ፋንታ ቤዛውን ይዛለት ከች ያለችውን ስትወለድ አይቶ በደስታ ቃል ዘለለ፡፡ ከሲኦል እስራት የሚፈታበት ቀንም እንደ ደረሰ በእርሷ ልደት ደወሉን ሰምቷልና ፈነደቀ፡፡
ሙሴ በእርሷ ልደት በደስታ ብዛት ቦረቀ፡፡ ከሩቅ ያያት የማትቃጠል ቁጥቋጦ በሐና ጭን ቁጭ ብላ ሲያይ እንደገነና ወደ እርሷ ሊገሰግስ ወደደ፤ ያኔ ጫማህን አውልቅ ያለውን ድምጽ አቃጨለበትና ባለበት ቆሞ ያያት ጀመር፡፡ ሲያያት ሕብረ ብዙ ሆና አስደነቀችው፡፡ ኦሪትን በሥነ ፍጥረት ሲጀምር በሁለተኛው ቀን ሰኞ እግዚአብሔር ከውኃ ጠፈር ያለውን ሰማይ እንዳሳየው ዛሬ ደግሞ ከመሬት አዳም የተወለደችውን ድንግል አዲስ ሰማይ ሁለተኛ ሰማይ አድርጎ ሲያሳየው ተገረመ፡፡ ያኛው ሰማይ ለዚህ ዐለም ፀሐይ ሲዘጋጅ ወደ ኋላ እንዳየ አሁን ደግሞ የአማናዊው የጽድቅ ፀሐይ መውጫ ስትወለድ ፀሐዩን ሊሞቅ ጊዜው መድረሱን አይቶ ተደሰተ፡፡ እንደገና ሲያያት ደግሞ አሁንም ሕብሯን ለውጣ ታየችው፡፡ ምደር ከመረገሟ በፊት ያለ ዘር ዕፀዋት አዝርእትን ስታበቅል አይቶ የነገረን ሙሴ ከእናቱ ከሔዋን ልጆች ሆና መርገም ያላረፈባት ያለወንድ ዘር የሕይወት እንጀራ ሆኖ የሚሰጠውን ፍሬ የምታስገኘውን አማናዊት ገራኅተ ሠሉስ አይቶ እንደገና አደነቀ፡፡
ሙሴ ከተመስጦ አልተመለሰም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጣት አድርጎ በጽላት ላይ ቃሉን ጽፎ የሰጠው እርሱ አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ የሚታይባትን ጽሌ ተወልዳ ሲያይ ተገረመ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ሲለው ፊቴን ልታይ አትችልም ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ያለው አምላክ የሚወልደባትን ተወልዳ ሲያይ የጌታን ጀርባ በደብረታቦር የሚያይበት ቀን መድረሱን አውቆ በደስታ ዘለለ፡፡ የመገናኛውን ድንኳን የተከለው ሙሴ ከድምፁ በቀር ያላገኘውን አምላክ የሚያገኝባት እውነተኛዋ የመገናኛው ድንኳን ተተክላ ባያት ጊዜ ደስ አለው፡፡ መቅረዝ ፣ ሙዳየ መና፣ ታቦትና የሥረየት መክደኛ ላይ ደም እየረጨ ሲያመልክ የነበረው ሙሴ አማናዊው ብርሃን የሚበራባት መቅረዝ፣ እውነተኛው መና የሚገኝባት ሙዳይ፣ እውነተኛው የሥረየት ደም የሚረጭባት ምሥዋዕ፤ አካላዊ ቃል የተቀረጸባት በሁለተናዋ ጽሩይ ወርቅ በተባለ ፍጹም ንጽሕና ተጊጣ ድንግሊቱን ባያት ጊዜ መደነቁን አበዛ፡፡ ድንኳኑን ሲያስብ እርሷ፣ ታቦቱንም ሲያስብ እርሷ፣ ጽላቱን ሲያስብ እርሷ፣ ሙዳየ መናውንም ሲያስብ እርሷ፣ መቅረዙንም ሲያስብ እርሷ፣ ማዕጠንተ ወርቁንም ሲያስብ እርሷ ስትሆንበት እንዴት አይደነቅ በእውነት፡፡ ሙሴ በዚህ አላበቃም፡፡ ሕግ የተቀበለበትን የጨሰውን ተራራ አስታወሰና ልጁን ዳዊትን ጠራው፡፡
ዳዊትም የአባቱን ሙሴን ጥሪ ሰምቶ ሲነሣ የረጋችው ተራራ ተወልዳ አያትና እርሱም በደስታ ዘለለ፡፡ አዎ "የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ፤ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው " /መዝ 68 ፤ 16/ ብሎ የተናገረላት ተራራ ስትወለድ አይቶ ደስ አለዉ፡፡ ሐላፊውን ብሉይ ኪዳን አባቱ ሙሲ ሲቀበል በነጓድጓድ ድምጽ በረዓድና በፍርሃት ነበረ፡፡ የማያልፈው ሐዲሱ ኪዳን ግን በጸና ተራራ እንደሚሰጥ የተናገረላት ያድርባት ዘንድ የወደደዳት አማናዊት የንጽሕና የቅድስና ተራራ ተወልዳ አይቶ ደስ እያለው መዝሙሮችን በአናት በአናት አከታተለ፡፡ ልጁ ሰሎሞንም "ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው" /መኃ 4 ፤ 1/ እያለ በምስጋና ተከተለው። ኢሳይያስም ንጹሕ ወረቀቱን አይቶ ደስ አለው፡፡ እንደ ታሸገች የተጻፈባት ሀዝብም አህዛብም ይህን ደብዳቤ ልናንብበው አንችልም ያሏት አካላዊ ቃል በድንግልና የሚጻፍባትን ንጹሕ ወረቀት /ኢሳ 29;11/ አይቶ ተደነቀ፡፡ ሕዝቅኤልም ሁለንተናዋ ዝግ ሆኖ እግዚአብሔር ብቻ ገብቶ የወጣባት መቅደሱን ተሠርታ አይቶ ደስ አለው፡፡
ተራ በተራ ሁሉም ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ይዘው ስለእርሷ ያዩትን ራእይ፣ ምሳሌና ትንቢት ፍጻሜውን እያዩ ተደነቁ፡፡ መሐንዲስ የሕንጻውን ንድፍና የሚሠራውን ሕንጻ እንደሚያስተያይ እነርሱም በልደቷ ትንቢታቸውን ከፍጻሜው መጀመሪያ መሠረት ጋር እያስተያዩ ተደሰቱ፡፡
በመጨረሻም የፍትረት ሁሉ አባት አዳም ከልጆቹ ጋር ደስ አለው፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ያለው ጌታው ከጨለማ ሲኦል ሊያውጣው ልጁን ከመሬት ባሕርዩ አንሥቶ እርሷን ሰማይ አድርጎ ሲያያት በእርሷም ላይ እርሱ ፀሐይ ሆኖ ሊወጣ ወገግታውን ሲያሳየው በደስታ አነባ፡፡ የሰጠኸኝ ሴት አሳተችኝ ብሎ የከሰሳት ሔዋንን ተክታ የሚያመሰግናት ሌላ ሔዋን ተወልዳ ሲያይ ደስስስ አለው፡፡ ምሳሌና የሚተካከላት እንደሌለም ሲያይ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ "ለእኗቷ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት" የሚለውን ዘምር አለው፡፡
ልጆቹ ሁሉ ከመረገሙ በፊት ያለ ክብሩን ስላላዩ በተገቢው መጠን የማያደንቁለትን ከስሕተት በፊት የነበረ ክብሩንና ጸጋውን ይዛ ስትወለድ በደስታ ተንሰቀሰቀ፡፡ የአዳምን ለቅሶ ሰምታ ሔዋን እናቷ የመርገም ጨርቋን ጥላ ብድግ አለች፡፡ አንድ ልጇን እያየች በደስታ አለቀሰች፡፡ በልጆቿ ሳይቀር ምነው እባብን ሰማሽው የሚል ወቀሳ እየሰማች ስታዝን የኖረች ምስኪን እናት መርገሟን ወርውራ በቅድስና ከብራ መላአክትን በልጣ እንደ ጨረቃ ስታበራ ስታያት መካሷን አይታ ፈነደቀች፡፡ ያሳታትን ዲያብሎስ በቅድስና መንገዷን ሰውራ የምታስተውን (ግራ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6565