tgoop.com/tseomm/6552
Last Update:
+ + ብዙ ዐየን + + +
በዚህ ሂደት ብዙ ዐየን። የብዙ ብዙ ተዛዘብን። በተለይ ባለሁለት መልኮችን። ቀን ቀን እዚህ ፤ ማታ ማታ እዚያ የሚረግጡ ብዙ ነበሩ። አጋጣሚውን ተጠቅመው ሊያጠቁንም የሞከሩ ነበር። አይተን እንደአላየን፤ ሰምተን እንደአልሰማን አልፈናል። ሁኔታው የሚጠይቀው ይህንን ነበረና።
ይህን መዋቅራዊ ሂደት ለማደናቀፍ አንዳንዶች ድግስ ደግሰው አበሉ። አንዳንዶች እኛ ዕግድ እንዳይተለለፍብህ ስንታገልልህ፤ እገሌ ዕግደ እንዲተላለፍ አደረገ አሉ። አንዳንዶች አንተ ብቻ ታግስ፥ ለአንተ የሚስማማ ውሳኔ እንዲወሰን እናደርጋለን አሉ። አንዳንዶች እኛን ከያዝክ ዕዳው ገብሰነው ማለታቸውን ሰማን። አንዳንዶች ለጊዜው የማኅበራዊ ሚዲያውን ጫጫታ ለማብረድ ዕግድ ተጣለብህ እንጂ፥ አጥፍተህ አይደለም እያሉም እንደሆነ ሰማን። እውነታዎቹ ግን እነዚህ አይደሉም። እዚህ ደብዳቤ ላይ የሰፈረው ነው።
ደጋግሜ በግሌም፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራን ባሉበት ለአቶ ጸጋዬም ሆነ ለፍኖተ ጽድቅ ሰዎች ያልኳቸውን እዚህ ላስታውስ እወዳለሁ። “ፍኖተ ጽድቅ ኦርቶዶክሳዊ የሚያደርገው ወይም የሚያሰኘው ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ጠብቆ ማገልገሉ እንጂ፥ የቅዱስነታቸው መሔድ፤ የጳጳሳቱ መመላለስ፤ የኦርቶዶክሳውያን መምህራን መገኘትና የቴክቶክ ወንድሞች ዘገባ አይደለም። ኦርቶዶክሳዊ አሰተምህሮን ካልጠበቀ ለውግዘት ያቀርበው ይሆናል እንጂ፥ አይረባውም።”
አሁንም በይፋ የምለው ይህንኑ ነው። መዳኛህ ኦርቶዶክሳዊ መሆንህ እንጂ፥ ሰዎችን ለመያዝ በመሞከር አይደለም። ሂደቱ ያሰተማረን ይህንኑ ነው። ይቆየን። ለሂደቱ በዝርዝር እመልሳለሁ ።
👉መምህር ታደሰ ወርቁ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6552