tgoop.com/tseomm/6528
Last Update:
ቅዱስ ሄሬኔዎስ(St. Irenaeus : C.130 - 202 AD) ስለ እመቤታችን የሔዋን ምትክነት(ቤዛነት) እንዲህ ብሏል፦ "Just as Eve was still a Virgin and became by her disobedience the cause of death of herself and whole Human race; so Mary too, espoused yet a Virgin, became by her obedience the cause of salivation of both herself and whole Human race. - ሔዋን ድንግል ሳለች ባለመታዘዟ ለራሷና ለሰው ልጆች ሁሉ የሞት ምክኒያት ስትሆን፥ ማርያም ግን ድንግል ሳለች በመታዘዟ ለራሷና ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳን ምክኒያት ሆናለች።'' (Against the Heresies 3.22.24)።
በሊቁ እንደተብራራ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 3 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘው የሔዋንና የእባቡ ንግግር ወደ ሞትና ጥፋት እንዳደረሰን በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 የተጻፈልን የእመቤታችንና የመልአኩ ንግግር ወደ ሕይወት መርቶናል። ይልቁንም እመቤታችን "እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" ብላ የመልአኩን ቃል መቀበሏ የሰው ልጆችን ሁሉ ወክላ ከእግዚአብሔር ዓለምን የማዳን ሐሳብ ጋር የተባበረችበት ቁልፍ የነገረ ድኅነት መሠረት ነው። በዚህም የሰው ልጆች "የባሕርያችን መመኪያ" እንላታለን።
ቅድስት ድንግልን "ቤዛዊተ ዓለም" ስንላት ለዓለም ሁሉ ድኅነት ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ፍጹም ቤዛ ከሆነን ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አስተካክለን ሳይሆን በመዳናችን ውስጥ "ዳግሚት ሔዋን" በመሆን ያደረገችውን ሱታፌ ለመግለጽ ነው።
© በአማን ወላዲተ አምላክ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6528