TSEOMM Telegram 6521
‘ኦሪት ማለት ዋዜማ ማለት ናት፤ ዋዜማ ፍጹም በዓል ማለት አይደለችም፡፡ የእስራኤል ትልቁ ችግራቸው የኦሪቱን የዋዜማ ድግስ ከበቂ በላይ በልተው ሆዳቸው ስለሞላ ታላቁ የሐዲስ ኪዳን በዓል አምልጧቸዋል፡፡ ዛሬም ኦሪት ላይ ተቸክረው የቀሩ፣ በጽድቄ፣ በገድሌ በትሩፋቴ እድናለሁ ብለው እንደኩራት የሚናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ደም የዘነጉና የረሱ ብዙዎች አሉ፡፡ ይኸንን ታላቁን የሰባ ግብዣ ከዚህ መመገብ ያቃታቸው፡፡’
እዚህ ላይ ዋዜማን በኦሪት፣ በዓልን ደግሞ በወንጌል መስለው ከተናገሩ በኋላ ከላይ እንዳልኩት ወደ ሐሜት ነው የገቡት፡፡ በመሠረቱ የአይሁድ ችግራቸው ሊቀ ጳጳሱ እንዳሉት ዋዜማውን ‘ከሚገባው በላይ በልተው በመጥገባቸው’ አይደለም፣ ዋዜማውማ የሚያጠግብ ቢሆን ምን ችግር ነበረው? ጉዳዩ ዋዜማው ያጠግብ ነበረ ወይ ነው? ያ ማለት ኦሪት ሰዎችን ማዳን ወይም መቤዥች ችላ ነበረ ወይ? የኦሪት ድግሱስ አንዴ ተበልቶ ለዘላለም የማያስርብ ነበረ ወይ? ኦሪት ካጠገበችማ የወንጌል መምጣት ለከንቱ ሆነ፡፡ ባይሆን አይሁድ ዋዜማውን አክብረው ዋናውን በዓል ሳያከብሩ ቀሩ ወይም በዋዜማው በቃቸው ቢሉ ያማረ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ከደቂቃዎች በፊት ‘ኦሪት ጨካኝ ናት’ ያለ ሰው ኦሪትን ዋዜማ፣ ወንጌልን ደግሞ በዓል ሲያደርቸው፣ ዋዜማን ጨካኝ እያላት እንደሆነ እንዴት ይዘነጋል? ዋዜማ ዋናውን በዓል መቀበያ ናት፣ መቆያ፣ ኦሪትም ዋናዋን እናት ወንጌልን ለመቀበል የቆየንባት ሞግዚት ሕግ ናት ቢሉ ያማረ ነበር፡፡
ሌላው በዚህ ክፍል ያቀረቡት ዘለፋ ነው፡፡ ‘ዛሬም ኦሪት ላይ ተቸክረው የቀሩ፣ በጽድቄ፣ በገድሌ በትሩፋቴ እድናለሁ ብለው እንደኩራት የሚናገሩ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ደም የዘነጉና የረሱ ብዙዎች አሉ፡፡’
ይኸ ተሐዲሶና ፕሮቴስታንት ኦርቶዶክስን በተመለከተ የሚናገሩት እንቶፈንቶ የሆነ ሐሜት ነው፡፡ ይኸ ጽንፍ የያዘ ምልከታ እኛን አይመለከተንም፡፡ ሊቀ ጳጳሱን ከውጭ ወደ ውስጥ የጮኩት ያስባለን ይኸን መሰሉ ነው፡፡ አባታችን የአይሁድን ክፋትን ደግነት ባነጻጽሩበት ክፍል ላይም ሌላ ስሕተት ሠርተዋል፣ እንዲህ ይላሉ፣
‘እኔ መቼም የአይሁድ ከክፋታቸው ደግነታቸው በጣም ይከፋል፣ ከክፋት የከፋ ደግነት! ምን አሉ? ውኃ ጠማኝ ባለ ጊዜ ጉሮሮን የሚሰነጥቅ መራራ ሐሞት አቀረቡለት፡፡ እርሱን በመስቀል ላይ እየሰቀሉ፣ ይኸንን የመሰለ፣ ሥረ ወጥ የሆነ ልብስ መቀደድ የለበትም፡፡ ይልቁንም ለደረሰው ይድረሰው ብለው በልብሱ ላይ እጣ ተጣጣሉ፣ ያ ማለት ዐይንን አጥፍቶ ለግንባር እንደመጨነቅ፣ እግር ቆርጦ ለጫማ እንደማሰብ ማለት ነው፡፡ እነሱ ፍርፋሪ፣ ጨርቅ ላይ ነው የሚጣሉት፣ እኛ የጨርቅ ጉዳይ ሊያነጋግረን አይችልም፣ እኛ ጨርቅ ላይ አይደለንም፣ ዋናው ላይ ነው፣ መድኃኒቱ ላይ ነው፣ ፀሐይ ላይ ነው ያለነው፣ እኛ በጨረቃና በከዋክብት አንጨቃጨቅም፣ ዋናው ጸሐይ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እነሆ በቀራንዮ የተደገሰው ታላቁ ግብዣ፣ ሥጋየን ብሉ ደሜንም ጠጡ ብሉ ብሎ አሳልፎ የሰጠን በእውነት፡፡’
ይኸ ንግግራቸው በተጣርሶ የተሞላ ብቻ ሳይሆን ከቅዱሳት መጻሕፍት ከሊቃውንቱ ብሎም ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላቸው ነው፡፡ ሲጀምር አይሁድ ‘ተጠማሁ’ ሲላቸው ሆምጣጣ ማምጣታቸው ክፋታቸው እንጂ ደግነታቸው አይደለምና አባታችን በንጽጽሩ ለከንቱ ደከሙ፡፡ ሲቀጥል ልብሱን ሲካፈሉ አሁንም የክፋታቸውን ጥግ የሚያሳይ እንጂ እንዳልኩት ‘ዐይንን አጥፍቶ ለግንባር እንደመጨነቅ’ እንዳሉት ያለ ቅንጣት የመጨነቅ መንፈስ የለውም፡፡ ለአባታችን ችግር የሆነባቸው ንግግሩ የሳቸው ሳይሆን፣ የተሐዲሶ የፕሮቴስታንት እና ከውጭ ወደ ውስጥ የተጮኸ መሆኑ ነው፡፡
‘እኛ ጨርቅ ላይ አይደለንም’ ምን ማለት ነው? የክርስቶስ ጨርቁ ዋጋ የለውምና አይሁድ በመከፋፈል ደከሙ እያሉ ነው? አባታችን በርካቶች የቅዱሳንን ጥላቸውን፣ ጨርቃቸውን እየነኩ የሚፈወሱ መኖራቸውን አላነበቡም ይሆን? ወይስ ማጣጣል የፈለጉት ምንድነው? ‘ፀሐይ ላይ ነው ያለነው፣ እኛ በጨረቃና በከዋክብት አንጨቃጨቅም’ ማለትስ ምንድነው?
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ‘ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ፣ ዘአኰነኖ መዓልተ ለፀሐይ ከመ ያብርህ ለነ ውስተ ጠፈረ ሰማይ’ ካለ በኋላ ‘ፀሐይ ይበቃል’ ብሎ አልተወውም፡፡ ይልቁንም ‘ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ዘአኰነኖሙ ለወርኅ ወለከዋክብት ከመ ይሰልጡ ግብሮሙ በሌሊት’ በማለት ያመሰገነው፣ ያደነቀው፡፡ አስተውሉ ሊቁ በጥንቃቄ ነው ግብሮም በማለት ሥራቸው በሌሊት ይፈጽሙ ዘንድ አሠለጠናቸው ያለው፡፡ ‘ብርሃናቸውን ያበሩልን ዘንድ’ አላለም ሊቁ፣ የብርሃናቸው ምንጭ ፀሐይ መሆኑን ያውቃልና ሚና አላቀያየረም ወይም አልተምታታበትም፡፡ የጨረቃና የከዋክብት ግብራቸው ከፀሐይ የተቀበሉትን በሌሊት መግለጥ ነው፡፡ ፀሐይ የክርስቶስ፣ ጨረቃና ከዋክብት ደግሞ የቅዱሳኑ ምሳሌ የሆኑት በዚህ ንጽጽር ነበር፡፡ ጨረቃና ከዋክብት ከምንጩ ፀሐይ የተቀበሉትን ብርሃን በሌሊት ጨለማ እንደሚገልጡ፣ ቅዱሳንም ከፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ የተቀበሉትን ክብርና ጸጋ በሌሊት በሚመሰል ጨለማ ዐለምን ለማብራት ነው የሚተጉት (ከመ ይሰልጡ ግብሮሙ በሌሊት)፡፡ ‘ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ’ ያላቸው ደግሞ ራሱ ባለቤቱ ነው፡፡ ‘እኔ የዐለም ብርሃን ነኝ’ ካለ በኋላ ‘’እኔ ዐለምን ስላበራሁ እናንተ ምንም አታድርጉ’ አላለም፡፡ ይልቁንም ‘ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ። መልካሙን ሥራችሁን ዐይተው አምላካችሁን ያመሰኙ ዘንድ’ እያለ አባታቸው ቅዱስ እንደሆነ እነሱንም ቅዱሳን ይሆኑ ዘንድ አዘዛቸው እንጂ፡፡ ለዚያ ነው ይኸ የተቆነጸለ ትችትዎት ከመላዋ ወንጌል ጋር ያጋጫዎታል የምንለው፡፡ ለዚያ ነው ጩኸቱ ከንቱ የሆነ የተሐዲሶና የፕሮቴስታንት እንቶፈንቶ ነው ያስባለን፡፡
2ኛ ከ20ኛ ደቂቃ ጀምረው ‘ነይ ነይ እምየ ማርያም ቤዛ ነሽ አሉ ለዓለም፣ እመቤታችን ቤዛ አይደለችም፣ ቤዛ ልጇ ነው፤ አትደንግጡ፣ ቤዛ ልጇ ነው፡፡ ነይ ነይ ቤዛ ነሽ አሉ ለዐለም ተብሎ አይሰበክም፣ ቤዛ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ የእግዚአብሔር ልጅ ብቻ ነው፣’ የሚለው ንግግራቸው ነው፡፡ በዚህ ላይ ብዙዎች አስተያየት ስለሰጡበት በዚህ ጽሑፍ አልሄድበትም፡፡
3ኛ የክርስቶስን ፈራጅነትና አማላጅነት በተመለከተ ያለውን ፕርቶቴስታንታዊና ተሐዲሶዊ ትችት ከስብከታቸው ጋር የግድ የሚላቸው ባይሆንም ዐላማቸው ቤተ ክርስቲያንን መጎንተልን ከውጭ ሆኖ መተኮስ ነውን? በሚያስብል መልኩ ሮሜ 8፡34 አንሥተዋል፡፡ እንዲህ ይላሉ፣
‘አሁን በእኛ ቤትና በሌላ ቦታ እንደትልቅ መጨቃጨቂያ ተደርጎ በሮሜ 8፡34 ምን የሚያከራክር ነገር አለው? መጽሐፍ ቅዱሱ የሚያከራክር ነገር የለምኮ፣ አባ ስረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ፣ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፣ በሉቃ 23፡ 34 ላይ ይኸ የተናገረው የይቅርታና የምልጃ ቃል ለዘላለሙ ሲያድን ይኖራል፡፡ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ይናገራል፣ አንድ ጊዜ የተናገረው ቃል ለዘላለሙ ይሠራል፡፡’

tgoop.com/tseomm/6521
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6521

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

"Doxxing content is forbidden on Telegram and our moderators routinely remove such content from around the world," said a spokesman for the messaging app, Remi Vaughn. Telegram Android app: Open the chats list, click the menu icon and select “New Channel.” Channel login must contain 5-32 characters Content is editable within two days of publishing Hashtags
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American