tgoop.com/tseomm/6515
Last Update:
በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል በረከት፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል ኀሳር፤ በኹለተኛዋ ሄዋን በኩል ክብር፤ በመጀመሪያዋ ሄዋን በኩል ከገነት መባረር ፤ በኹለተኛዋ ሄዋን ኦ ገነት ነባቢት በተባለችው በድንግል በኩል ወደ ገነት መመለስ ኹኖልናል። ቅ/ኤፍሬም ሶርያዊ በሄዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ። በድንግል ማርያም ምክንያት የገነት ደጅ ተከፈተ ይለናል።ቀጥሎም እፀ ሕይወትን እንበላ ዘንድ ዳገመኛ ከእፀ ሕይወት አደለን ይላል። ይሄ ንፅፅር ምን ያሳናል ?በእመቤታችን ምክንያት የገነት በር ተከፈተ ማለት የገነትን በር የከፈተቸው የሚላት"የክርስቶስን ደም ትቶ ወይም ነጥቆ ነው እንዴ ? አይደለም። ነገር ግን የገነትን በር የከፈተው የክርስቶስ ደም ደማዊት ሥጋዊት መንፈሳዊትም ከኾነችው ከእመቤታችን የተገኘ ስለኾነ ነው። ዓለም የዳነበት የክርስቶር ደም ከሰማይ የወረደ አይደለም።ሥጋ ከሰማይ አላወረደም። ኢያውረደ ሥጋ እምሰማያት እንዳለ አባ ጊዮ መጽ ምስ" >የዓለም መዳኛ የኾነው ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም የተከፈለ ከዳግማዊት ሄዋን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ መድኀኒት ከመድኀኒቱ መገለጫ እና ከምክንያቱ ጋራ አያይዞ መጥቀስ ሥርዓቱ ነው ። እመቤታችን መስቀልንም ኾነ እመቤታችንም ቤዛ ፥መድኀኒት፤ የገነት መክፈቻ እያሉ ደራስያን ሊቃውንት ሲገልጧቸው በእነርሱ በኩል ስለተፈጸመው ነገር ነው ። ወይም በእነርሱ በኩል የተፈጸመውን የማዳን ሥራ ለእነርሱ እየሰጡ መናገር ለተፈጸመው የማዳን ሥራ የድኀነቱ ማከናወኛ መንገድ ወይም በር ስለ ኾኑ ነው።መንገዱ እና በሩ ክርስቶስ መኾኑን አንዘነጋም ። ነገር ግን ክርስቶስ የድንግልን ማኀጸን እና መስቀልን ለዙፋንነት ተጠቅሟል። የንጉሥን መንግሥት ከነ ዙፋኑ መግለጥ ግድ ነው። ድንግል በእባብ ለተደበቀው ዲያብሎስ በሥጋ ተሰውሮ መጥቶ ድል ይነሳው ዘንድ መሰወሪያ የኾነው የሥጋው መገኛ ኹናለች።መስቀልን በመስቀል ተሰቅሎ አምላኬ አምላኬ እያለ ሊውጠው የቀረበ ዲያብሎስን መቀጥቀጫ አድርግታል። በኹለቱም የማዳን ሥራ ሠርቶባቸዋል።
☑️ቤዛን ምትክ" ብንለው በገነት ባጣነው እፀ ሕይወት ምትክ መስቀል ኹኖልናል። ስለዚህ መስቀል ቤዛችን ነው ቢል ድኀነት ስለተፈጸመበት በእፀ ሕይወት ፈንታ ስላገኘነው ነው ነው። ዳግመኛም በእፀ በለስ ምክንያት ብንወድቅ በእፀ መስቀል አዳነን ለማለትም ነው ። እመቤታችን የሄዋን ቤዛ ስንላት
ምትኳም መድኀኒቷም፥ ጥላዋም ፦ ጫማዋም ለማለት ነው። የሄዋን ማሰሪያ የተፈታባት እመቤታችን ናት ዮ አፈሃይ"።ማሰሪያው ደግሞ ገመድ ወይም ሰንሰለት አይደለም።ኀጢአት መርገም ፍዳ ነው። ምክንያቱም የሄዋን መርገሟ ፍዳዋ በደሏ ከእመቤታችን ሲደርስ አቁሟል።የጠፋው ወይም የጠወለገው የጎሰቆለ የሄዋን ባሕርይ በእመቤታችን ንጹሕ ኹኖ ተገኝቷል። በዚህም የባሕርይዋ መመኪያ ኹናታለች። ዳግመኛ አማናዊ የሄዋን መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚች እናት ተገኝቶላታል። ስለዚህ ሄዋን ባሕርይዋ ነጽቶ ክቡር ኹኖ የተገኘባትን የእመቤታችን ባሕርይ መመኪያ ቤዛ ብትለው ትችላለች። እንዲያውም እመቤታችን የድኀነቱ ሱታፌዋን እንመልከት።የአዳም ቤዛ የኾነው የክርስቶስ መገኛ ናት። ክርስቶስ የዓለም ቤዛ ነው ። ም የመጀመሪያው አዳም የኹሉም አባት ነው።ኹለተኛው አዳም ክርስቶስም የኹሉ አባት ነው። የመጀመሪያዋ ሄዋን የኹሉ እናት ናት።ኹለተኛዋ ሄዋን ማርያምም የኹሉ እናት ናት። የመጀመሪያዋ የዓለም ኹሉ ሞት ምክንያት ናት።ኹለተኛዋ ማርያምም የዓለም ኹሉ ድኀነት ሕይወት ምክንያት ናት። ምክንያቱም ዲያብሎስ ዓለሙን ኹሉ ማለት ሰውን ኹሉ ድል ለማድረግ ኀጢአትን ወደ ዓለም ለማስገባት ሄዋንን በለስን ተጠቅሟል። ክርስቶስም ሕይወትን ወደ ዓለም ለማስገባት መስቀልን ሴቲቱ ድንግል ማርያምን ተጠቅሟል። መስቀልን። ወደ ዓለም በገባው ኀጢአት ምክንያት ሄዋን የኹልጊዜ ተጠሪ እንደኾነች ኹሉ ወደ ዓለም ለገባው ድኀነት፥ ሕይወት ደግሞ ድንግል ማርያም የምንጊዜም ተጠሪ ናት ።ስለዚህ ቤዛዊተ ኲሉ ቢሏት፥ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ አንችን ለዓለም ቤዛ አንድም ድኀነት ውብ አድርጎ የፈጠረ ቢባል ትክክል ነው። ሄዋን ቀታሊተ ዓለም ከኾነች እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ናት። ዓለምን ኹሉ የወከለች ማርያም የዓለሙ ቤዛ መገኛ በመኾኗ እና የወደቀችው ሄዋን ምትኳ የመዳኗ ምክንያት የመድኀኒቷ ማከናወኛ እና የዓለም ድኀነት መሠረት የተጣለ በማኀጸነ ማርያም ነው እና የዓለም የድኀነት መሠረት የተጣለባት በመኾኗ ቤዛ መባሉ ከልክም በላይ የልክ ልክ ነው ።
☑️ዳግመኛም እመቤታችን የማየ ገቦው፤ የደመ ገቦው መገኛ ናት። በማየ ገቦው ተጠምቀን እንድናለን።ማየ ገቦ ግን ከድንግል ከተገኘ ሥጋ የተገኘ ነው። ደመ ገቦውን ወይም ከጎኑ የፈሰሰ ደሙን ጠጥተን እንድናለን።
ደም የተገኘበት ክርስቶስ ግን በሥጋ የተገኘ ከድንግል ማርያም ነው። የጌታ ስደት የድኀነታችን አካል እና ለቤዛነት የተፈጸመ ነው ።የሚሰደድ ሥጋ የተጋኘ ግን ከድንግል ነው።ማለት መለኮት ከእርሷ ባሕርይ ባለ መከፈሉ እንጅ የተሰደደው ሥግው ቃል መኾኑ ግልጥ ነው። የክርስቶስ ረኀብ የድኀነታችን አካል ለቤዛነት ለካሳ የተፈጸመ ነው። የሚራበው ሥጋ ግን የተገኘ ከእርሷ ነው። የክርስቶስ ስቅለቱ ሞቱ የዓለም ድኀነት ነው። የሚሰቀል ሥጋ የሚሞት ሥጋ የተገኘ ግን ከድንግል ማርያም ነው ።እመቤታችን የክርስቶስ የቤዛነት ሥራ ኹሉ ይመለከታታል። ቤዛነት የተፈጸመበት ሥጋ መገኛ ናት።ቤዛ ዓለም ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን መገቢያ በር መንገሻ ዙፋን መራመጃ መንገድ መገናኛ ድልድይ መውጫ መውረጃ መሰላል አድርጓታል። ኹኖም ቀራንዮ ላይ የተሰቀለችው ፥የሞተችው ፥ ወደ ሲኦል በአካለ ነፍስ ወርዳ ሲኦልን የበረበረችው እርሷ ናት አንልም። ነፍሳትን ከዲያብሎስ እጅ የማረከችው ወደ ገነት ያስገባችው ቀጥታ እርሷ ናት አንልም።ብለንም አናውቅም።ይሄ ኹሉ የተፈጸመበት ጌታ ግን በእርሷ በኩል በእርሷ እንደመጣ እናውቃለን።እርሷም የዚህ የማዳን ሥራ ከዚህ እና ከዚህ በጠለቀ በሚታይ ምሥጢር ተሳታፊ ናት።ስለዚህ ቤዛ ቤዛዊት መድኀኒት ትባላለች። እመቤታችን ኀጢአት አልባ ናት።ያለ ዮሴፍ ሰሎሜ ቢሰደዱ ስለ ኀጢአታቸወም ነው።እመቤታችን በዚህ ዓለም ያገኛት መከራ ኹሉ ስለምኗ ይኾን?ያለ ኀጢአቷ የአዳምን ስደት የተሰደደልጇን ተከትላ ወይም ከልጇ ጋራ መሰደዷም በአጠቃላይ በዚህ ዓለም የተቀበለችው መከራ የጌታን የቤዛነት ሥራ ይተካል።ይተካከላል አንልም እንጅ ለዓለም ግን ቤዛ ነው። ጌታ ያለ ኀጢአቱ የተሰደደው ስደት ስለ ሰው ነው። የእናቱም ለእርሱ መክበሪያ ለሰዎች ደግሞ ቤዛ ማለት የድኀነቱ አካል ነው። ይሄ ሰፊ እይታ ያሻዋል..። ጥላው ጫማው ጋሻው በመጽሐፍ ቅዱስ ቤዛ ተብሏል።እመቤታችንም ከጥላ ከጫማ ከጋሻ አታንስም። ጋሻ ከጦር ከሠይፍ በማዳኑ ቤዛ ተብሏል።እመቤታችንም በአማላጅነቷ በነገረ ድኀነት ባላት ሱታፌ ቤዛ ትባላለች። ጥያቄ ??????
እስራኤልን ባሕር ከፍሎ ማን አሻገራቸው ?
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6515