tgoop.com/tseomm/6501
Last Update:
አክፍሎት ከጤናም ከኑሮ ሁኔታም አንጻር ማክፈል ለሚችሉ አማኞች ነው የትንሣኤ ዕለት የሚቆርቡ ሁሉ የግድ ማክፈል አለባችሁ በማለት ሰዎችን ከሥርዓተ ቁርባን አናርቃቸው በተለይ በሰው ቤት ብዙ አድካሚ ሥራ የሚሠሩ በአረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን በዚህ ጉዳይ የግድ ማክፈል አለባችሁ በሚል የአንዳንዶች የግዴለሽነት ትምህርትን አክብረው ለመቁረብ እየሄዱ ቤተ መቅደስ ውስጥ ሳይቀር እራሳቸውን እንደሚስቱ እንሰማለን
እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥም ብዙ ሰዎች የፋሲካ ሌሊት ደክመው ሰው ሲደግፋቸው ወዘተ እናያለን እነዚህ ሰዎች ከተቀበሉ በኋላም ከታመሙ ከቁርባኑን አላማ እንዲርቁ ሊያደርጋቸው ይችላል
አንድ ቆራቢ ሰው ከመቁቡ በፊት መጾም ያለበት ለ18 ሰዓት ነው እንደ ፋሲካ ያለ ቀን ሲሆን ግን ቢቻለው ያከፍላል ባይቻለው ግን የግድ ሐሙስ በልተህ ነው የምትቆርበው ተብሎ ስላላከፈልህ መቁረብ አትችልም አይባልም በዚህ የግዴለሽነት መመሪያ መሠረት ብዙ ሰዎች ከቁርባኑ ይርቃሉ በተለይ የጤና እክል ያለባቸውና አድካሚ ሥራ የሚበዛባቸው ሰዎች ደግሞ ወይ እራሳውን ከልክ በላይ ጎድተው ከአቅማቸው በላይ መጾም እራሳቸውን እስከመሳት በሚያደርስ መልኩ ቆይተው ይቆርባሉ አሊያም ከሥርዓተ ቁርባኑ ለመራቅ ይገደዳሉ።
አንዳንዶች መቁረብ እፈልግ ነበር ግን ማክፈል ይከብደኛል ብለው በውስጥ ይጠይቃሉ ስለዚህ በሰዎች ላይ ሸክም እያበዛን ከሥጋ ወደሙ እንዳናርቃቸው እናስተውል!
የምንችል ሁሉ የክርስቶስን መከራና ስቃይ እያሰብን አክፍለን እንቁረብ የማንችል ደግሞ ማክፈል ባንችል እንኳን ለ18 ሰዓታት ነገረ ሕማሙን እያሰብን ጾመን እንቁረብ።
👉 መጋቤ ሐዲስ ዘላለም ሐሳቤ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6501