tgoop.com/tseomm/6499
Last Update:
በአጥቢያችሁ በዓመት ለምን ያኽል ጊዜ ታቦት ይወጣል? ስንት ድርብ ታቦት አለ? ለክርስቶስ ተብሎ የመጣውን ሽቶ ሽጦ መክበር የሚፈልጉ ሰዎች ክርስቶስን የሚያገለግሉት የሽቶው ብር ተሽጦ ገቢ እስከተደረገ ድረስ ብቻ ነው። ካልሆነ ጉባኤው ክርስቶስን መስማቱን ትቶ “ይህ ገንዘብ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይገባ ነበር” በሚል የእንጉርጉሮ ቃል እንዲሞላ ለማድረግ ፈጣኖች ናቸው።
ከላይ ስትመለከቱት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ካላቸው ፍቅር የተነሣ የሚመስል ውስጡ ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስከበር የተፈጠረ አጀንዳ መቅረጽ የሚችሉ ይሁዳዎች በእኛ ዘንድ ብዙ አሉ።
የተነሡት አለቆች፣ ጳጳሳት እና ሌሎችም አገልጋዮች ሁሉም ሥራ አበላሽተው ቤተ ክርስቲያንን በድለው ይመስላችኋል? ምናልባትም የሴቲቱን ዕንባ እንጅ የያዘችውን የአልባስጥሮስ ሽቶ ስለማይመለከቱ በከረጢት ያዦች ዘንድ ነገራቸው ስላልተወደደ ይሆናል ዮሐ. 12፥6።
ይሁዳ ይኼውላችሁ ከሚፈሰው እንባችን ይልቅ የሚፈሰው ሽቶ የሚያስቆጨው ከዳኑ ነፍሳት ይልቅ ከነሱ የሚያገኘውን ጥቅም የሚያስቀድም ሰው ካገኛችሁ ይሁዳ እሱ ነው።
ይሁዳ በሌላም ቦታ አለላችሁ። ይሁዳ ክርስቶስን ሸጠ፤ ጸጋውን ሽጦ መኖር የሚፈልግ ስንት ይሁዳ አለ መሰላችሁ? መጽሐፍ እንደነገረን ክርስቶስ ጸጋ ሆኖ ተሰጥቶናል ዮሐ. 1፥18 ይህንን ጸጋ ምዕመናንን ከመጥቀም በቀር ለሌላ ጥቅም ማዋል ይሁዳነት ነው።
ለሚያስተምር መምህር የሚገባውን ዋጋ መክፈል ምዕመናን የታዘዙት ትዕዛዝ ነው። ሐዋርያው እንደነገረን በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል የለምና።
ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላም አይገኝም። መምህራንም መንፈሳዊውን ዘርተው ሥጋዊውን እንዲበሉ ተፈቅዶላቸዋል። ነገር ግን ከአሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት የተለየ መቀበል ከይሁዳ በቀር ማንም የማያደርገው ነውረኛ ገንዘብ dirty money ነው።
ቤተ ክርስቲያን በየቀኑ “ለይሁዳ ወልዱ ወውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ” እያለች ብትረግመውም ይሁዳ ግን ዛሬም አለ። የሄው በእኔ ውስጥ፣ በእናንተም አጠገብ ይሁዳን አገኘሁት።
እስኪ የእናንተን ሀሳብ ልስማ? ይሁዳ አለ ወይስ ሞቷል?
©️ስምዐኮነ መልአከ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6499