tgoop.com/tseomm/6453
Last Update:
“አብደላህ ቢን ዑበይድ እንዳወሳው አንድ ሰው እንዲህ አለ፡- አቡ አበዱራህማን ሀይ ለምንድነው ሁል ጊዜ ሁለቱን ጠርዞች ብቻ ስትነካቸው የማይህ? ብሎ ጠየቀው፡፡ እርሱም የአላህ መልእክተኛ እነርሱን መንካት ኃጢአትን ይደመስሳል ሲል ሰምቼዋለሁ አለ፡፡” (ሱናን አል-ናሳኢ 2919)
ልብ በሉ! ይህ ሐሳብ ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ የሚያምኑት እምነት ነው፡፡ሰይጣን ግን በሙስሊሞች ሲጫወትባቸውና በክርስቶስ እንዳይድኑ ሲጋርድባቸው በውሸት ከሰማይ የወረደ ድንጋይ እያስባለ ሲቀልድባቸው ይኖራል። እንደ ክርስትናው እውነት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአት የሌለበት ሲሆን ሰዎች ራሳቸውን ማዳን ስለማይችሉ ሊያድናቸውና በእነርሱ ፈንታ ምትካዊ ሞት ለመሞት ወደ ምድር ወርዷል፡፡ በመስቀል ላይም የሰዎችን ኃጢአት ተሸክሟል፡፡ በሙስሊሞች እምነት መሠረት ልክ እንደዚሁ ካዕባ ከሰማይ ነጭ ሆኖ የወረደ ሲሆን በሙስሊሞች ኃጢአት ምክንያት ጠቆረ፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን ንፁህ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኃጢአታቸውን ተሸክሞ ሊያነፃቸው እንደሚችል በመካድ ድንጋይ ኃጢአታቸውን መሸከም መቻሉን ማመናቸው የሚያስገርም ነው፡፡
★ ካዕባ በአላፍ ፊት ይመሰክራል★
“ኢብን አባስ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ ስለ ጥቁሩ ድንጋይ እንዲህ አለ፡- በአላህ እምላለሁ! በፍርድ ቀን የሚያይባቸው ሁለት ዓይኖች እና ማን እንደነካው የሚናገርበት ምላስ ይሰጠዋል፡፡” (ጃሚ አት-ትርሚዲ ቅፅ 2 መጽሐፍ 4 ሐዲስ 961)
እንግዲህ ሐዲሱ በግልፅ እንዳስቀመጠልን ካዕባ በፍርድ ቀን ስለሙስሊሞች ይመሰክራል፡፡ ታድያ እንዴት ነው አንዳንድ ሙስሊሞች ካዕባን ብንነካውም ባንነካውም ለውጥ የለውም የሚሉን? ኃጢአታቸው እንዲሰረይላቸው አይፈልጉምን? በፍርስ ቀን እንዲመሰክርላቸው አይፈልጉምን?
ዘመንኛ ሙስሊሞች ከዑመር ጋር ተስማምተው ካዕባን መንካት ነቢዩን ለመታዘዝ እንጂ ምንም መንፈሳዊ (ሃይማኖታዊ) ጥቅም የለውም ሲሉን ነቢያቸው እየዋሸ ነው ማለታቸው ይሆን?
ማጠቃለያ
ከላይ ያየናቸውን ነጥቦች በሙሉ በአንድነት ስናጤን ካዕባ የእስልምና ጣዖት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ከእስልምና በፊት ዓረቦች ድንጋይ ያመልኩ ከነበረ፤ የአምልኳቸው አካል ድንጋዩን መዞር እና መሳም ከነበረ፤ በዓረብ አገራት የሚመለኩ ድንጋዮች “ካዕባ” ተብለው ከተጠሩ፤ ካዕባ በመካ ከነበሩ 360 ጣዖታት አንዱ ከነበረ፤ ሙስሊሞች ደግሞ ያንኑ የዓረብ ድንጋይ አምልኮ ተግባር የሚፈፅሙ ከሆነ “ካዕባን አናመልክም” የሚሉበት አንደበት የላቸውም፡፡ ዓረቦቹ ድንጋዮቻቸውን እያመለኩ የሚያደርጓቸውን ተግባራት እነዚያኑ እያደረጉ እንዴት ነው “ካዕባን አላመለክንም” የሚሉን? ሙስሊሞች ካዕባን እያመለኩ ካልሆኑ ዓረቦቹም ድንጋይ ያመልኩ ነበር ተብለው ሊከሰሱ አይገባቸውም፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በድንጋዮቻቸው ዙርያ ተመሳሳይ ድርጊት ይፈፅማሉና፡፡
ለሌሎችም ሼርና ታግ አድርጓቸው
👉ታሪኩ አበራ እንደጻፈው
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6453