TSEOMM Telegram 6440
መጋቢት ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የፌስቡክ ገጽ
👉 በድሬዳዋ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ከ፴፮ ዓመት በላይ በአስተዳዳሪነት ያገለገሉት መልአከ ሰላም አባ ወልደ ሩፋኤል ገብረ ዮሐንስ ቆሞስ ሥርዓተ ቀብር የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መጋቤ ሠናያት ቀሲስ ኃይለ ማርያም ገብረ ሚካኤል የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡሕ በድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኀላፊዎች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጸሐፊያን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መምህራን የድሬዳዋ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መዘምራን ወዳጅ ዘመዶቻቸውና በርካታ ምእመናን በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው ለዘመናት በአስተዳዳሪነት በአገለገሉበት ቤተክርስቲያን በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተፈጸመ።

ብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በመልአከ ሰላም አባ ወልደ ሩፋኤል ሞት የተሰማቸውን ሐዘን የገልጹ ሲሆን ለመላው ማኅበረ ካህናት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ለድሬዳዋ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ መጽናናቱን እግዚአብሔር አምላክ እንዲያድልልንና ነፍሳቸውን ቅዱሳን አበው ካረፉበት እንዲያሳርፍ ተመኝተዋል።

በቀብር ሥርዓቱ ላይም ለክቡር መልአከ ሰላም አባ ወልደ ሩፋኤል ገብረ ዮሐንስ ቆሞስ የሽኝት መርሐ ግብር የተከናወነ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡሕና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት የአበባ ጉንጉንና አስቀምጠዋል።

በመጨረሻም ቅኔና መወድስ በመጋቤ ምሥጢር ያሬድ ዘርዓ ቡሩክና ቀሲስ አንተሁን ቀርቦ ሥርዓተ ቀብራቸው በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ተፈጽሟል።
👍21

tgoop.com/tseomm/6440
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6440

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

On June 7, Perekopsky met with Brazilian President Jair Bolsonaro, an avid user of the platform. According to the firm's VP, the main subject of the meeting was "freedom of expression." Done! Now you’re the proud owner of a Telegram channel. The next step is to set up and customize your channel. Channel login must contain 5-32 characters Telegram offers a powerful toolset that allows businesses to create and manage channels, groups, and bots to broadcast messages, engage in conversations, and offer reliable customer support via bots. Ng was convicted in April for conspiracy to incite a riot, public nuisance, arson, criminal damage, manufacturing of explosives, administering poison and wounding with intent to do grievous bodily harm between October 2019 and June 2020.
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American