tgoop.com/tseomm/6417
Last Update:
🤔 ማንም ሰው ይነሣና የጉዞ አዘጋጅ ይሆናል!
🤔ማንም ሰው ተነሥቶ ይደራጅና ማኅበር ነኝ ይላል!
🤔ማንም ሰው ተነሥቶ የሆነ ቤተ ክርስቲያን አጋዥና አሠሪ ነኝ የዚህ ገዳም ተጠሪና አስጎብኝ ነኝ ይላል!
እነዚያ ግለሰቦችም ስለ ፈለጉት ገዳም በራሳቸው መንገድ የራሳቸውን ነገር ያስገባሉ!
🤔 ስለ ገዳሙ የተጠና ሙሉ መረጃ ሳይዙ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮን ያልተከተለ ታሪክ መተረክና ጠበልና እምነት የቤተ ክርስቲያኗ መደበኛ የፈውስ መንገዶች እያሉ አዲስ ነገር ለመፍጠር ብለው እንደ ቂቤና እንደዚህ ሾላ ፍሬ በመሳሰሉት ፈውስ ይገኛል የሚል አላማ ይዘው ይነሣሉ
መዓር በዓይን ላይ ማድረግ ብለው ከቤተ ክርስቲያን የማታዘውን ሥራ የሚሠሩ ሰዎች እኔም አንድ ቦታ አይቼ በጣም አዝኛለሁ በዚህም ብዙ እናቶች ሲቸገሩ አይቻለሁ
ቦታው ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የጥቅም ሽርክና ይፈጥሩና ቦታውን እናሳድገዋለን እናንተ ዝም በሉ ይላሉ እሺ ይባላል
ሀገረ ስብከቱም ደኅና ፐርሰንት ስለሚያስገቡ ባላየ ያልፋቸዋል
እንዲህ የሚያደርጉ አካላት ትክክለኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ መሆናቸውንና ሃይማኖታቸውን የሚገልጽ መረጃ እንኳን አያቀርቡም
የሚያገኙትን የገቢ ምንጭና ወጭና ገቢያቸውን የሚቆጣጠር አካል እንኳን የለም
አሁን ደግሞ ጨራሽ ሁለት ወንድማማቾች ተነሥተው የጉዞ ማኅበር ብለው እንደፈለገ ቢንቀሳቀሱ እንኳን የማኅበራት ሕብረት የሚለው ምዝገባ ውስጥ ይገቡና ቤተ ክርሰሰቲያኗ እውቅና ሰጥታናለች ታዋቂዎች ነን ብለው ለንግዳቸው ሌላ መተማመኛ አግኚተዋል
እና እንዲህ እየተሆነ ሕዝበ ክርስቲያኑ የነጋዴዎች መጫወቻ ገዳማቱም የነጋዴዎች መፈንጫ ሆነው መታየታቸው ምንም አይደንቅም
ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የት አለ?
የማኅበራት ሕብረቱ ሕግ የት አለ የቁጥጥር ሥራውስ ምን ላይ ነው?
የእየ ሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎችስ ሥራ ምንድን ነው?
ኦርቶዶክሳውያን ሚዲያዎችና የሚዲያ ባለሙያዎችስ ምን እያደረግን ነው?
አንድ ገዳም ሲተዋወቅና ወደ ቦታው ጉዞ ሲደረግ የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከንግድ ጋር ያልተሳሰረና ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚጠቅም መሆኑ በደንብ መጠናት አለበት ገዳም እያስተዋወቁ የነጋዴ ሕይወት መቀየሪያ መሆን የለበትም።
የአጠማመቅ አይነት የወደፊት ባሌን አየሁት፣ ጊዮርጊስ ፎቶ አነሣኝ ወዘተ የሚል ቅዠት እየተሰማ ነው!
ስንዴ የመስፈር ፕሮግራም፣ ነጠላ የማንጠፍ ሥነ ሥርዓት፣ ስመ ክርስትና የመጻፍ ወዘተ እየተባለ በምን ምክንያት የምዕመናንን ገንዘብ እናግኝ የሚል የንግድ ስልት መቆም አለበት!
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6417