tgoop.com/tseomm/6415
Last Update:
መምህር ኃይለ ማርያም ዘቦሩ ሜዳ እንደጻፉት ነው።
ስንት ጊዜ ብዙ ብለው ዛሬ ለጠየቁት ጥያቄ ከመጽሓፋቸው "እፎይ" መልስ ሰጠ፣ 'ውዱ' ተሰደበ አሉ።
#አባቱን_የጠላ_የሰው_አባት_ይሰድባል
ይህ በሀገራችን የተለመደ የአበው ብሂል ነው። ውነትም ዘሎ የሰው አባት የሰደበ ሰው አባቱን ለስድብ አጋልጦ መስጠቱ ሳይታለም የተፈታ ነው።
ሰሞኑን በክርስትናና በስልምና ጎራ ተሰልፈው ተዋሥኦ ሲያደርጉ በነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ምክንያት የመግለጫ ጋጋተዎችን ሰምቻለሁ። ተዋሥኦ ወደ ጸብ እንዳይቀየር መሥራት መልካም ቢሆንም መግለጫዎቹ ግን ያተኮሩት (የሃይማት ተቅዋማት ኅብረትና የስልምናው ምክር ቤት ያወጡት) ችግሩን ወደ መፍታት ሳይሆን ክርስቲያን ወንድሞች እንዳጠፉ እንደ ገፉ። ስልምና እንደ ተገፋ አድርገው ነው።
ለዚህ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሆነው እፎይ የተባለው ወንድም ነው።
#ይህ_ወንድማችን በስብከት መልክ ቀርጾ የለቀቀው፤ ወይም በአውደ ምሕረት ያስተማረው ነገር የለም። በማኅበራዊ ሚዲያ ለክርክር ተሰልፈው ያቀረባቸው ጥያቄዎች ናቸው። መልሱ ቀላል ነው የቻለ ሃይማኖታዊ መልስ መስጠት። ወይም ሐሳቡን መቃወም ካልሆነም ክርክሩን ማቆም ነው። ከተከራከሩ በኋላ ግን በሕጉም ያለ ሕጉም ማስፈራራትና የመግለጫ ጋጋታ በጎ አይደለም።
#ማንም_የማንንም ሃይማኖት መሞገት እንጂ ማንቋሸሽ አይችልም ግን ሚዛናዊነት ያስፈልጋል።
መግለጫ የሚወጣው ለስልምና ብቻ ነውንዴ?
እስከ ዛሬ ክርስትና ሲነቀፍ ማን መግለጫ ሰጠ።
የሚዲያውንን የነአቡ ሀይደርን የዘወትር ነቀፋ እንተወውና በመጽሐፍ መልክ ብቻ በክርስትና ላይ የተደረገውን ድፍረት እንመልከት።
1.መጽሐፍ ቅዱስ ስለመሐመድ ምን ይላል? አሕመድ ዲዳት፤ 1989
2. ስለኢየሱስ እውነተኛ መረጃ፤ ዶ/ር ማንህ ሐምማድ አልጆሐኒ
3. ኢየሱስ እውን ፈጣሪ ነውን? አሕመድ ዲዳት፤ 1988።
4. እስልምና እና ክርስትና፤ መሐመድ አሊ አልሑሊ።
5. ክርስቶስ በኢስላም፤ አሕመድ ዲዳት፤ 1999።
6. የሴቶች መብትና እኩልነት በኢስላምና በክርስቲያን እምነት (አቀራረቅ) አሕመዲን ጀበል 2001።
7. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነውን? 2003።
8. ለአብነት ያህል 1መቶ ስሕተቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ በዛኪር ናይክ(ትርጉም፦ አሕመድ ዐሊ) 2003።
9. የመጽሐፍ ቅዱስ ምሥጢር በሙስሊም መነጽር፤ ቀመር ሑሴን።
10. ክርስቶስ ማን ነው? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች።፤ አሕመዲን ጀበል፤ 2001።
እነዚህና የመሳሰሉት መጻሕፍት ክርስትና ላይ አነጣጥረው ሲጻፉ።
ማን መግለጫ አወጣ?
ማን ተከሰሰ?
ማን የሞት አዋጅ ታወጀበት?
ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፉን በመጽፍ
የአፍን በአፍ፤ ስትመልስ ኖረች እንጂ እንደዚህ ያለ ጋጋታና አዋጅ አላወጣችም። ታዲያ ዛሬ ምን ተገኘ?
ወደው ፈቅደው ሚዲያ ከፍተው እነከራከር ብለው ቀርበው እንደ ሕጻን ጨዋታ መተፋፈር መልካም አይለም። ሃይማኖቱ እንዲከበርለት የሚፈልግ የሰው ሃይማኖት አይነቅፍም። ከላይ የተዘረዘረው መጽሐፍ የተጻፈውኮ ክርስትናን ለማወደስ አይደለም ለማዋረድ እንጂ። ታዲያ ምንሁኑ ነው አሁን?
መፍትሔ
1. ተዋሥኦ/ክርክር አንፈልግም የሚል አካል በግልጽ ተናግሮ መተው።
2. ከመስመር የወጣ ነገር ካለ ሁሉም በየቤቱ መምከር። እንደ ጠቢብ ወላጅ(ጠቢብ ወላጅ ልጁ ከሌላ ልጅ ጋር ተጣልቶ ሲመጣ ቀድሞ ልጁን ይቀጣል ይገርፋል፤ ሞኝ ወላጅ ግን የራሱን ልጅ ትቶ የጎረቤት ልጅ ይሰድባል።)
3. ክርክሩ ከቀጠለ በአስተዋይ ሰው መጠን ተደማመጦ መከራከር። ከዚህ የወጣው ለማንም አይጠቅምም።
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6415