TSEOMM Telegram 6408
የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በርካታ ምእመናንን በማጭበርበር የማይገባውን ገንዘብ በወሰደው ዲያቆን ላይ ሥልጣነ ክህነቱን የመሻር እርምጃ መወሰዱን አስታወቀች።

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ፋዲ ሹክሪ ኢስካንዳርን ተብሎ የሚጠራውን የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበረውን ግለሰብ የዲቁና ማዕረግ መገፈፉን ቤተ ክርስቲያኒቱ አስታውቃለች።

ግለሰቡ ከብዙ አመታት በፊት ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አሜሪካ ተሰደው እዚያ መኖር እንደጀመሩ የገለጸችው ቤተ ክርስቲያኒቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች መካከል እየተዘዋወረ፣ እዚያ የሚገኙትን የኮፕቲክ አብያተ ክርስቲያናትን እየጎበኘ፣ ከወጣቶች ጋር ጓደኝነት መመሥረትና ከጳጳሳትና ከካህናት ጋር መቀራረብ ጀምሮ በተለይም ግሪክ ከሚገኙት የኮፕት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ የዲቁና ማዕረግ አግኝቷል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በመግለጫዋ ይኸው ግለሰብ በአውሮጳ ሀገራት የሚገኙ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት አባላትን አመኔታን ካገኘ በኋላ በሚኖሩባቸው ሀገራት የመኖሪያ ፈቃድ ሂደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ድጋፍ መስጠት እንደ ጀመረ እና ይህን ተግባር ለመፈፀም በእነዚህ ሀገራት ውስጥ ካሉ ባለስልጣናት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳለው በመናገር በውሸት ከበርካታ ምእመናን ብዙ ገንዘብ ተቀብሏል ነው ያለችው።

እንደ መግለጫው በእነዚህ ሀገሮች የሚገኙ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እነዚህን ድርጊቶች መፈጸፀሙንና በሀሰት ከምእመናን የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ወደ ስርቆት መግባቱን ካወቁበት በኋላ፣ ሌሎችን ምኤመናን እንዳያታልል በተለያየ መንገድ ማስጠንቀቂያ ሲልኩ፣ አንዳንዶቹም የወሰደባቸውን ገንዘብ እንዲመልስለት ለማሳመን ሞክረው ነበር፣ ግለሰቡም ለአንዳቸውም ምላሽ ሳይሰጥ አልፎ ተርፎም የማታለል ሥራውን ቀጥሎ ነበር። ከምንም በላይ ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ የተባሉት በግሪክ የኮፕት ሊቀ ጳጳስ እሱን ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም።

ብፁዕ አቡነ ጳጳስ ጳውሎስ ቅዱስነታቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊን በዚህ ጉዳይ ላይ ካማከሩ በኋላ፣ ከስህተቱ እንዲመለሱ ፍቃደኛ ባለመሆኑ፣ አካሄዱን ለማስተካከል ተከታታይ ሙከራዎች ቢደረጉም ምንም ተግባራዊ ምላሽ ባለማግኘታቸው፣ በብዙ ሰዎችና ቤተሰቦች ላይ ቁሳዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ፣ ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሁንታ የቀድሞውን ዲያቆን ሥልጣነ ክህነት ሽረዋል።
በሊቀ ጳጳሱ የወጣው ውሳኔ ቅዱሳን ቁርባንን ከመቀበል ፣ የዲያቆን አገልግሎትን እና በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሁሉንም አይነት አገልግሎቶችን በዓለም ላይ እንዳይቀበል ማድረግንም ይጨምራል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በዚህ ጉዳይ ባወጣችው መግለጫም የቀድሞው ዲያቆን ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የለበሰውን የቤተክርስቲያን ልብስ ማውለቅ እንዳለበት በማሳሰብ ይህንን መጣስ ከምእመናን ህብረት ሙሉ በሙሉ እንዲገለል ያደርገዋል ብላለች።

ይህ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እርምጃ በተለይም በማጭበርበር፣ በማታለል እና ሙስና በመሳሰሉት የክፋት ተግባራት ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላትን የማይቀያየር አቋም አመላካች ነው።

እኛስ ከዚህ ምን እንማር ይሆን?

ዘገባውን ለማሰናዳት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ይፋዊ ድረገጽ እና ሲ ኤም ሲን ተጠቅመናል።
5

tgoop.com/tseomm/6408
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6408

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The court said the defendant had also incited people to commit public nuisance, with messages calling on them to take part in rallies and demonstrations including at Hong Kong International Airport, to block roads and to paralyse the public transportation system. Various forms of protest promoted on the messaging platform included general strikes, lunchtime protests and silent sit-ins. Click “Save” ; Find your optimal posting schedule and stick to it. The peak posting times include 8 am, 6 pm, and 8 pm on social media. Try to publish serious stuff in the morning and leave less demanding content later in the day. A new window will come up. Enter your channel name and bio. (See the character limits above.) Click “Create.” Content is editable within two days of publishing
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American