tgoop.com/tseomm/6391
Create:
Last Update:
Last Update:
ከአርባ ምንጭ ዚጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል አክብረው እየተመለሱ በነበሩ ምዕመናንን ላይ የመኪና አደጋ ደርሶ በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን ከዚህ ዓለም ድካም ዐረፉ !
መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
መነሻቸውን ሐዋሳ እና ሻሸመኔ ከተማ አድርገው የመጋቢት አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስን ዓመታዊ ክብረ በዓልን በአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ በማክበር ወደ መጡበት በመመለስ ላይ የነበሩ ምዕመን በወላይታ ዞን በዴሳ ከተማ መሻገሪያ ድልድይ ሥር በደረሰ ከባድ የመኪና አደጋ ከ20 በላይ ምእመናን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
አደጋው ዛሬ ምሽት 12:30 አካባቢ የደረሰ ሲሆን የተሳፈሩበት መኪና ወንዝ ውስጥ የገባ በመሆኑ የሟቾች ቁጥር ከእዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነው የተነገረው።
በአደጋው የተጎዱ ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናንን በወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ላረፉት ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6391