tgoop.com/tseomm/6383
Last Update:
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሠራር ሚዛናዊ እና ፍትሐዊነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባ ተመላከተ !
መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
መቻቻልን፣ አብሮነትንና ፍትሕ ላይ የተመሰረተ የአንድነት መስተጋብርን ከምንመለከትባቸው ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሚዛናዊ እና ፍትሐዊነት ላይ ተመሥርቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገራቸው የሃይማኖት አባቶች ከሰሞኑ በተፈጠሩ ኢትዮጵያዊ አንድነትን ከሚሸረሽሩና የሃይማኖትን ነጻነት ከሚጋፉ ተግባራት አኳያ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነት የጎደለው እና በፍትሐዊነት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ቅርብ የሆኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንደገለጹት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው በሕግ ከተሰጠው ኃላፊነት አሠራር አንጻር ከሰሞኑ በጉባኤው ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ በተግባር ያለፉ ነገር ግን ትኩሳታቸው ዛሬም ድረስ ያሉ እውነታዎችን መጋፈጥ ያልቻለ መሆኑን ነው የገለጹት።
የመግለጫው ሀሳብ ይህንን "ማኅበረሰባዊ ትንኮሳ የጀመሩት ኦርቶዶክሳውያን ነን የሚሉ መሆናቸው እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ነን የሚሉትም አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት የገቡበት እንደሆነ" ተደርጎ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑ እና ያለፉ እውነታዎችን መሠረት ያላደረገና አንድን ወገን ብቻ ማዕከል አድርጎ መተላለፉ ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት።
ከዚህ ቀደም ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች ዘመቻ በተጨማሪ ክርስቶስ ማን ነው? 303 ወሳኝ ጥያቄዎች ፣ ሰይፉን ፍለጋ፣ ኢየሱስ የኢስላም ነቢይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማን በረዘው፣ ክርስትና መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?፣ ክርስቶስ በኢስላም ፣ ሙሐመድ የታላላቆች ታላቅ የሚሉና ሌሎችም የክርስትናን አስተምህሮ በቀጥታ የሚዘልፉ፣ የሚያንቋሽሹ እና የሚያጥላሉ የጥላቻ ሀሳቦችን የያዙ መጻሕፍት ጭምር ሲዘጋጁ እና ለተዘጋጁትና ለተሰራጩትም ባለቤት እያላቸው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤው በእነዚህ የክርስትና መሠረተ እምነት ላይ ጥላቻን በሚያቀነቅኑ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ አንድም እርምጃ ሳይወስድና እነዚህ የጥቃት መነሻዎች እያሉ ኦርቶዶክሳውያን ነን የሚሉ ግለሰቦች የጀመሩት የጥላቻ ንግግር በሚል አጥቂንና ተጠቂን በቅጡ ያልለየ ፍረጃ ተቀባይነት ዝቅተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
ሌላኛው የሃይማኖት አባት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት መልአከ ምሕረት ወልደ ገብርኤል ናቸው ለሚዲያችን በሰጡት አስተያየት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፈው ማክሰኞ ያወጣው መግለጫ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን እና ተቋሙ ይህንን ድርጊት በተለመለከተ በድጋሚ አጢኖት ይቅርታ ሊጠይቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዚህና በሌሎች የሕዝብ አስተያየቶች ላይ የሚለው ነገር እንዳለ ብለን የተቋሙን ሃሳብ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
በተጨማሪም ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት በሆኑ ጉዳዮች መሰደብና መጥላላት ላይ ትኩረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮችን በተመለከተ ያለው ነገር የለም።
©ተ.ሚ.ማ
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6383