TSEOMM Telegram 6248
የተሰበረ ጽዋዕ

እዚኽ ፎቶ ውስጥ በአካል የማውቀው ዘማርያምን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ግን በማኅበራዊው ሚዲያ መልስ ሲሰጡና ሲጠይቁ አያቸዋለሁ እንጂ ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም፡፡በወንድሞቻችን ፊት ፕሮቴስታንት ሰባክያን ምላሳቸውን ሲተሳሰር ብዙ ጊዜ አይቻለኹ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ከኦርቶዶክስ ወንድሞች ጋር እንዳትከራከሩ" የሚል አዋጅ ሲያውጁ ሰምቻለኹ ጰንጤዎቹ፡፡
በአጭሩ፥ እኒኽ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክትና ሰዎችን ታመልካለች የሚለውን ፕሮቴስታንታዊ የድር ምሽግ ሲበጣጥሱ ተመልክቻለኹ፡፡ ከዐይን ያውጣችኹ አልላችኹም፡፡ ዐይንም ጆሮም ውስጥ ናችኹና፡፡

ጽንዑ ወኀይሉ፡፡ ለማለት ነው አመጣጤ፡፡

ከእኒኽ ወንድሞች መኻል አንዱ ወይም ኹሉም ሊሳሳቱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቀለም ሠረገላ የማያሰናክለው የለምና፡፡ ደግሞም እኔ እንኳ የሰማኋቸው የሚታረሙ ስሕተቶች አሉ፡፡የሚታረም ነገር ተገኘ ማለት ግን፥ ሙሉ እርሻው አረም ነውና አያስፈልግም የሚል ቧልት መናገር ግን ቅንነትና ወንድማዊ ፍቅር ይጎድለዋል፡፡

በአንድ ወቅት፦
አንድ እጅግ የተከበሩ ሊቅ ከአንዲት ሴት ጋር ድቀት አገኛቸው፡፡ እኒኽን ሊቅ ብዙ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ በዚኽኛው ታሪክ ግን ሰፊው ሕዝብ ስለማያውቃቸው ስማቸውን ልለፈው፡፡ ይኽን ድቀታቸውን የሰማ ደብተራ አንድ ቀን ማሕሌት ውስጥ አገኛቸው ሊቁን፡፡"ደግሞ አንተ እዚኽ ምን ልታደርግ ገባኽ?"
ሲል በፍና ተሣልቆ አፌዘባቸው፡፡ እርሳቸውም "እኔኮ የተሰበርኩ ጽዋዕ ነኝ" ብለው አንጀት የሚበላ መልስ ሰጡት፡፡

የተሰበረ ጽዋዕ ሰባራ ስለኾነ አይጣልም፡፡ንዋይ ቅዱስ ነውና በክብር ከዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ፡፡
እንደዚያ ደብተራ ለቤተክርስቲያን የቀናን እየመሰለን ጥቂት ሸራፋ ያገኘንባቸው ጽዋወችን ኹሉ አውጥተን እንጣል ማለት እጅግ የከፋ በደል ነው፡፡ክርስቶሳዊውን መንገድ የረሳ ነውና፡፡ "ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፥ ለብሓዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት" የምትል ድንቅ የንጉሥ ጉባኤ ቃና አለች፡፡ ግርድፍ ትርጉሟ፦ ገላ'ችን ከተሰበረ በኋላ ሸክላ ሠሪው ክርስቶስ በአዲስ የውኀ ጥምቀት እንደገና ሠራው፡፡ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከጌታዋ የተማረችው የተሰበረን መጠገን ነው፡፡

ችግሩ፥ መጠገን እንደመስበር ቀላል አይደለም፡፡ ለመጠገን ዕውቀትና ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ለመስበር ግን ኦርቶዶክሳዊ የዘብነት ቀለም የተቀባች ምላስ በቂ ናት፡፡

ወንድሞች በጎ ሲሠሩ እናበርታ፡፡ሲስቱ እንክርዳድ ከስንዴ እየለየን በፍቅር እናርም፡፡አልታረምም የሚል ካለ ደግሞ የቤክርስቲያን ቱንቢ ያርመዋል፡፡እንደ ግለሰብእ እኔ ነኝ ቱንቢው ማለት ግን የስሕተት ስሕተት ነው፡፡

በየሚዲያው ሌሎች ጥሩ ወንድሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የተገለጡ ናቸውና ተውኳቸው፡፡
ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው እንደጻፉት
1👍1

tgoop.com/tseomm/6248
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6248

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Click “Save” ; Some Telegram Channels content management tips fire bomb molotov November 18 Dylan Hollingsworth yau ma tei Telegram Channels requirements & features 5Telegram Channel avatar size/dimensions
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American