TSEOMM Telegram 6220
+++ሥዕለ እረፍታ ለማርያም+++

በሠዓሊ ኃይለ ማርያም ሽመልስ (በቅዱሳት ሥዕላት ዙርያ አማካሪ፣ ጥናትና ሒስ አድራጊ) 0913 05 2824

++++++++++===+++++++++++
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍት በዓል አደረሳችሁ። ከሥር የእመቤታችን የእረፍትና የግንዘት ታሪክን መሠረት በማድረግ ትውፊቱን ጠብቀው የተሣሉ ጥንታዊያን የብራና፣ የእንጨት ገበታ (ኢቆና)፣ እና የግድግዳ ቤተ መቅደስ ሥዕሎች ቀርበዋል።

የእመቤታችን የእረፍት ሥዕል እንደተሣለበት መደብ እና ያለው የቦታ ስፋት የሚጨመሩ ወይም የሚቀነሱ አካላት አሉበት።

በአጠቃላይ ሲሣል የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋ በክብር አልጋ ላይ ሆና (ተቀምጣ / ጋደም እንዳለች)፤
ቅዱስ ነፍሷን ጌታችን በእልፍ አእላፍ መላእክት ተከቦ ሲቀበላት፤
ቅዱሳን ሐዋርያት እያዘኑ ከበዋት መብራት አብርተው፣ መጽሐፍ እያነበቡ እና እያጠኑ፣ ቅዱስ ጷጥሮስ በግርጌ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራስጌ ሆነው፣
ቅዱሳን መላእክት እያጠኑ፣
ቅዱሳን ደናግል አዝነው፣
ቅዱስ ዳዊት በገና እየደረደረ፣ ቅዱስ እዝራ በመሰንቆ እያመሰገነ በአጠቃላይ በአስደናቂ መንፈሳዊ ደስታ ይሣላል።

ማስታወሻ፥ የእመቤታችን የእረፍት ሥዕል ላይ ታውፋንያን አስገብቶ መሣል ጸያፍና ተገቢ ያልሆነ ነው። ምክንያቱም ስንክሳር፣ ተአምረ ማርያም ሆነ ሌሎች አዋልድ መጻሕፍት እንደሚነግሩን ታውፋንያ በዚህ በተቀደሰ መንፈሳዊ ስፍራ አስቀድሞ አልነበረም።

የቤተ ክርስቲያን የሆኑት ቅዱሳት ሥዕላት እንወቅ፣ እንመልከት እና እንጸልባቸው። በስጦታ ይሁን  ወይም በስእለት ለቤተ ክርስቲያንም እንስጥ።

ጥንታዊ ቅዱሳት ሥዕላት ለማየት ለማውረድ፣ ለሌሎች ለማጋራት ከፈለጉ @ethioicons ቤተሰብ ይሁኑ።
👍31

tgoop.com/tseomm/6220
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6220

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

To edit your name or bio, click the Menu icon and select “Manage Channel.” Just as the Bitcoin turmoil continues, crypto traders have taken to Telegram to voice their feelings. Crypto investors can reduce their anxiety about losses by joining the “Bear Market Screaming Therapy Group” on Telegram. In 2018, Telegram’s audience reached 200 million people, with 500,000 new users joining the messenger every day. It was launched for iOS on 14 August 2013 and Android on 20 October 2013. How to Create a Private or Public Channel on Telegram? Concise
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American