TSEOMM Telegram 6216
አስተርዮ ማርያም
የማይታየው የታየበት፣ የራቀው የቀረበበት፣ የረቀቀው መለኮት በገዘፈ ሥጋ ማርያም የተገለጠበት፣ የወልድ ልጅነት በአብና በመንፈስ ቅዱስ የተመሰከረበት፣ በልደቱ፣ በጥምቀቱ አንድነት በሦስትነት እንዲሁም መለኮት በሥጋ ሥጋም በመለኮት በተዋሕዶ ተገልጦ ምሥጢሩ ገሃድ የሆነበት የመገለጥ የመታየት ጊዜ የሆነው ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ዘመነ አስተርዮ እየተባለ ይጠራል፡፡
በዚሁ በዘመነ አስተርዮ መካከል የሚገኝ ስለሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም “በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም” እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ አስተርዮ ማርያም የምንለው ታላቅ በዓል እናታችን እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም ያረፈችበት መታሰቢያ ሲሆን ቀኑም ጥር ፳፩ ነው፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን የወሰነች፣ ሞትን በሞቱ የመሻር ሥልጣን ያለውን፣ ዓለምን በመዳፉ የጨበጠውን የወለደች ክብርት ቅድስት እመቤታችን ከዚህ ዓለም ድካም የምታርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ ይኸውም ጥር ፳፩ ቀን በዕለተ እሑድ በ፷፬ ዓመቷ፣ በ፵፱ ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቷ ጊዜ መድረሱን ነግሯት በልጇ መቃብር ሆና ጸሎት ታድርስ ነበር፡፡ እንዲህም ብላ ጸለየች፤ ‹‹ልጄ ወዳጄ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሐዋርያትን ሁሉንም፣ ነፍሳቸውንም የለየሃቸውን አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋንና የሙታን አምላክ ነህና›› አለች፡፡ (የጥር ፳፩ ስንክሳር)
በዚህ ጊዜ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ከኤፌሶን አመጣችው፤ ምስጋናም አቀረበላት፤ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብር ተነሥተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ እንዲህም ስትል ጠየቀቻቸው፤ ‹‹ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፤ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ሰማችሁ?›› አለቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም ‹‹ወደ አንቺ እንድንመጣ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፤ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ ወደ አንቺ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደ እርሷ መጣ፡፡ (ጥር ፳፩ ስንክሳር)
እንዲህም አላት ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጥቻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኔ ተሸክሜህ፤ በድንግልና ወልጀህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን ሁሉ አሳያትና ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ሁሉ ነፍሳት መዳን ምክንያት (ቤዛ) ይሆናቸዋል›› አላት፡፡ ‹‹እነዚህን ሁሉ ከማርክልኝስ ይሁን›› አለች፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋን ከክብርት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በይባቤ መላእክት በክብር ነፍሷን ዐሳረጋት፡፡ (መዝገበ ታሪክ ቁጥር አንድ ገጽ ፻፶፭፣ ጥር ፳፩ ስንክሳር)
የእመቤታችን አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን
👍2

tgoop.com/tseomm/6216
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6216

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The creator of the channel becomes its administrator by default. If you need help managing your channel, you can add more administrators from your subscriber base. You can provide each admin with limited or full rights to manage the channel. For example, you can allow an administrator to publish and edit content while withholding the right to add new subscribers. Telegram Android app: Open the chats list, click the menu icon and select “New Channel.” More>> It’s easy to create a Telegram channel via desktop app or mobile app (for Android and iOS): Telegram offers a powerful toolset that allows businesses to create and manage channels, groups, and bots to broadcast messages, engage in conversations, and offer reliable customer support via bots.
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American