TSEOMM Telegram 6214
ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ(1926-1989)- የእንደቸርነትህ መዝሙር ደራሲ

-ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ በ1926 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ ከአባታቸዉ ከአቶ ዓለሜ እንግዳና ከእናታቸዉ ከወ/ሮ አዲሴ አሥራት ተወለዱ፡፡ እድሜያቸዉ ለትምህርት ሲደርስ ጥንታዊ ወደሆነው ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤት ገቡ፡፡ ከዚያም ንባብ፣ ዜማ እና የግዕዝ ቅኔ በተወለዱበት ደብረ ኤልያስ ከተማሩ በኋላ የቅኔ ሙያቸውን ለማሻሻል ወደ ዋሸራ ቅኔ ቤት ሄደው የግዕዝ ቅኔን አስፋፍተዋል፡፡

-በ1942 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ ከዚያም ወደ ውጭ ሀገር ተልከው ከካይሮ ኮፕቲክ ዩኒቨርስቲ በባችለር ኦፍ ዴቪኒት(በትምህርተ መለኮት) በዚሁ ዩኒቨርስቲ በአፍሪካ ጥናት ኤም .ኤ.ዲግሪ፣ ከአሜሪካ ደግሞ በማስተማር ዘዴ
ኤም.ኤ.ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከኢጣልያ ፔሩጅያ ዩኒቨርስቲ በኢጣልያኛ ቋንቋ ዲፕሎማ ማግኘታቸው ታውቋል፡፡ እንደገና በ1965 ዓ.ም ወደ ካይሮ ተመልሰው በአፍሪካ ጥናት በ1970 በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

-ዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ በቤተክህነትና በመንግስት መሥሪያ ቤቶች ለረጅም ዘመናት በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በትምህርት ሚኒስቴር በመምህርነት፣ በጠቅላይ ቤተክህነት የታሪክ ፣የድርሰትና የስብከት ክፍል መምሪያ እንዲሁም በአገር አስተዳደር ሚኒስቴር የጥናትና ምርምር ክፍል ኤክስፐርት በመሆን ሀገራቸውንና ወገናቸውን በቅንነት አገልግለዋል፡፡ በካይሮ ለኢትዮጵያውያን ኮሚውኒቲና ለግብጻውያን በጽሕፈት ሚኒስቴር ትዕዛዝ የአማርኛ ቋንቋ አስተምረዋል፡፡ ከዚያም ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ የቋንቋና የባህል ኤክስፐርት፣ የግዕዝ ቅኔና የመጻሕፍት ትርጓሜ ክፍል ተጠባባቂ ኃላፊ በመሆን በከፍተኛ ትጋትና ቅንነት በጡረታ እስከ ተገለሉበት ድረስ አገልግለዋል።

-በሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት ካበረከቱዋቸው ሥራዎች መካከል

1.)የግዕዝና የቅኔ አመጣጥ ከነሚዛኑ

2)የግዕዝና የአረብኛ ቃላት ተዛምዶ በሚሉ ርዕሶች ከፍተኛ ዋጋ ያላቸዉ የምርምር ሥራዎች ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም "የአረብኛ ቋንቋ መማሪያና ምክር በኪስ" የሚሉ መጻሕፍት አሳትመው ለንባብ አብቅተዋል፡፡

-በቋንቋ ችሎታ በኩል ከፍተኛ ተሰጥዖ ስለነበራቸው ከአማርኛ በተጨማሪ የግዕዝ ፣ የአረብኛ ፣የእንግሊዝኛ፣ የጣልያንኛ፣ የክላሲክ ግሪክና የኮፕቲክ ቋንቋ ችሎታቸዉ ከፍተኛ ነበር፡፡

-ዶ/ር ኢሳይያስ ግጥም የመጻፍ፣ ለገጠሙት ግጥም በሙዚቃ ምልክት(ኖታ) ዜማ የማውጣትና የመዘመር ልዩ ችሎታ ነበራቸው። በቅድስት ሥላሴ ት/ቤት ሳሉ ለትምህርት ቤቶችና ለትያትር የመዝሙር ደራሲ ነበሩ፡፡ የጻፉትም የመዝሙር ስብስብ ሥራ በስምንት አይነት ልዩ ልዩ ድምጾች በምልክት (በኖታ) ተዘጋጅቶ በመርሐ ጥበብ ማተሚያ ቤት ታትሞ ወጥቷል፡፡ ይህንንም መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እየተዘዋወሩ አስተምረዋል፡፡

-በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በየአድባራቱና ገዳማቱ በየዕለቱ ማታ ማታ ከሚሰጠው ትምህርት በኋላ የሚዘመረው "እንደቸርነትህ" የሚለው የመዝሙር ጸሎት ከዶ/ር ኢሳይያስ ዓለሜ ሥራዎች አንዱ ነው። ነፍስ ይማር።

ምንጭ:- ደ/ኤልያስ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
👍2

tgoop.com/tseomm/6214
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu

Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6214

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Select “New Channel” As five out of seven counts were serious, Hui sentenced Ng to six years and six months in jail. Ng was convicted in April for conspiracy to incite a riot, public nuisance, arson, criminal damage, manufacturing of explosives, administering poison and wounding with intent to do grievous bodily harm between October 2019 and June 2020. Telegram has announced a number of measures aiming to tackle the spread of disinformation through its platform in Brazil. These features are part of an agreement between the platform and the country's authorities ahead of the elections in October. The initiatives announced by Perekopsky include monitoring the content in groups. According to the executive, posts identified as lacking context or as containing false information will be flagged as a potential source of disinformation. The content is then forwarded to Telegram's fact-checking channels for analysis and subsequent publication of verified information.
from us

Telegram ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
FROM American