tgoop.com/tseomm/6195
Last Update:
ለረ/ፕ መ/ር ግርማ ባቱ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ
________
(ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ/ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም)
ረ/ፕ መ/ር ግርማ ባቱ በቅርቡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመኾን መሾማቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎም በመምህርነት በሚያገለግሉበት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም የምስጋና መርሐ ግብር ተካሒዷል።
የምስጋና መርሐ ግብሩን ያካሔዱት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ሲሆኑ ለረጅም ዘመናት በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ሓላፊነቶችና በመምህርነት ለባረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ታሳቢ ያደረገ እንደኾነ የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሓላፊ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ዩኒቨርሲቲያችን ለቤተክርስቲያናችን ታላላቅ ሓላፊነቶች የሚያዘጋጅ አንጋፋ ተቋም ለመኾኑ የመ/ር ግርማ ባቱ ሹመት ምሥክር ነው ብለዋል። ከዚህ በፊትም ዩኒቨርሲቲው ለቤተክርስቲያናችን ጳጳሳትንና ዐለም አቀፍ ምሁራንን ሲያበቃ የነበረ መኾኑን በአባታዊ መልእክታቸው የገለጹት ብፁዕነታቸው አሁንም ምስጉን መምህራንንና መንፈሳዊ መሪዎችን እያዘጋጀ የሚያቀርብ የጀርባ አጥንት የኾነ አንጋፋ ተቋም መኾኑን በመግለጽ ለመ/ር ግርማ በመምህርነታቸው ላይ ካህንም ናቸው በማለት የእጅ መስቀል ሰጥተዋቸዋል።
በምስጋና መርሐ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚደንት ፕ/ር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ፣ የአስተዳድር ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት መልአከ ኃይል አባ ጽጌድንግል ፈንታሁን እና ለረጅም ዘመናት በመምህረነት ያገለገሉ ምሁራን መልእክት እና በጎ ምስክርነት ያስተላለፉ ሲሆን የትምህርት ክፍል ሓላፊዎችና መምህራን በዕንግድነት ተገኝተው ለመልካም አገልግሎታቸው ስጦታና ማስታወሻ ሰጥተዋቸዋል።
(የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት)
#tsegayekiflu
BY ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu
Share with your friend now:
tgoop.com/tseomm/6195