Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
19536 - Telegram Web
Telegram Web
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች የኦንላይን መለማመጃ ፈተና መስጠት ተጀምሯል፡፡

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈጻሚ በተሰራው ሶፍትዌር አማካኝነት ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚፈተኑ ተማሪዎች የመለማመጃ ፈተና በመሰጠት ላይ ነው።

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈፃሚ አዱኛው አለበል እንደገለጹት የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ኢንተርኔት ባለባቸው አካባቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1,670 ለሚሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የአይሲቲ ባለሙያዎች በተሰራው ሶፍትዌር የበየነ መረብ የመለመጃ ፈተና ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም የመለማጃ ፈተናው አስፋላጊነት ተፈታኝ ተማሪዎች ቴክኖሎጅው ጋር አንዲግባቡና ለቀጣይ ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የመለማመጃ ፈተናው ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 07/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ጠቅሰው በቀጣይ የአዊ ብሄረሰብ ትምህርት መምሪያ በሚያወጣው መርሀ ግብር መሰረት የበየነ መረብ (ኦንላይን) ሞዴል ፈተና እንደሚፈትኑም ገልፀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይዘጋጁ!

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈታና ተፈታኝ ተማሪ ከሆኑ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ለፈተና በቂ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ ትምህርቶችን ማግኘት ይችላሉ።

በትምህርት ሚኒሰቴር የተዘጋጁ የሁሉም ትምህርት አይነቶች የቲቶርያል ቪዲዮዎችን ለማግኘት 👇
https://examinfo.moe.gov.et/guide

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።

በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡

በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ ከላይ ተያይዟል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።

መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተላከ ነው።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
📚 የፈተና መርሃግብር

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ፋይዳ

" ከግንቦት 18/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ግዴታ ነው " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፦
- የትምህርት መረጃ ድጋሜ ለመውሰድ፣ ለማጣራትና ለማረጋገጥ
- Official Transcript ለማስላክ
- ስም ላይ የፊደላት ግድፈትን ለማስተካከል
- True Copy ለማግኘት እና የድጋፍ ደብዳቤ ለማጸፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተገልጋይ ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የግዴታ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ አገልግሎቱ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ላይ የትምህርት መረጃ አገልግሎት ዘወትር በሥራ ቀናት እየሰጠን እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተገልጋዮች https://services.eaes.et ላይ ባሉበት ሆነው በማመልከት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

በተጨማሪም " በኢትዮ ፖስታ ወይም በተወካይ በኩል አገልግሎቱን ባሉበት ሆነው ማግኘት  ይችላሉ " ብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#NationalExam

በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 608 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ/ም የሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና ላይ 608 ሺህ ተማሪዎች ይቀመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ፈተናው በወረቀት እና በበየነ መረብ ይሰጣል።

ፈተናውን በወረቀት የሚወስዱ ተማሪዎች እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ይወስዳሉ።

ፈተናውን በበይነ መረብ የሚወስዱት ደግሞ ፦
- በዩኒቨርሲቲዎች፣
- በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች፣
- በጤና እና መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጆች
- በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ባሉ ኮምፒዩተሮች ይፈተናሉ። ተማሪዎቹ ግቢ ማደር ሳይጠበቅባቸው ከቤታቸው እየተመላለሱ ነው ፈተናውን የሚወስዱት።

በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና በሁለት ዙር ሲሆን ይህም የሆነው በበይነ መረብ የመፈተን አቅምን እና የተፈታኝ ተማሪዎችን ቁጥር ለመጨመር እንዲሁም ያለውን የመሰረተ ልማት አቅም ለማሳደግ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍ ኤም ሲ በሰጠው ቃል አስረድቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አሉባልታ ...
Anonymous Quiz
37%
Malignancy
43%
Hearsay
12%
News
8%
Recount
"በድጋሜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ጊዜ አልተራዘመም፡፡" - ትምህርት ሚኒስቴር

የመውጫ ፈተና በድጋሜ ተፈታኞች የፈተና ጊዜን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡

አሁን ላይ የመወጫ ፈተናውን በድጋሜ የሚወስዱ ተፈታኞችን የምዝገባ ሁኔታ እየገመገመ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

በድጋሜ የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚፈተኑት ጋር አብረው ፈተናውን እንደሚወስዱ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ከሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየው የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ተፈታኞች ምዝገባ ነገ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡

በቀሩት ሰዓታት ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et

Note:
በዲሲፕሊን ምክንያት የመውጫ ፈተና ውጤታችሁ የተሰረዘባችሁ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ማዕከል ድጋሚ ተፈታኞች፤ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ ምዝገባ ማድረግ የምትችሉ መሆኑ በሚኒስቴሩ መገለፁ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ በመጪው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍለ ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ 3 እና 4/2017 ዓ.ም ይሰጣል የተባለ ሲሆን የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ደግሞ ከሰኔ 10 እስከ 12 እንደሚሰጥ ተጠቁሟል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#MoE
#ተራዝሟል

በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በድጋሜ ተፈታኝ አመልካቾች ምዝገባ እስከ ግንቦት 14/2017 ዓ.ም ተራዝሟል፡፡

በመሆኑም ዳግም ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ቀነ ገደብ ውስጥ እንድታጠናቅቁ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡

ይመዝገቡ 👇
https://exam.ethernet.edu.et

የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ የግድ ነው፡፡

ምዝገባ ለማድረግ የቪዲዮ ቲቶሪያል ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=C9KkQ9AHd2o

ትምህርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
🔻https://www.tgoop.com/Tmhrt_Ministers
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/06/25 16:08:31
Back to Top
HTML Embed Code: