ኩባንያችን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የንግድ ሥርዓቱን በዲጂታል ለማዘመን የሚያስችል ውይይት አደረገ።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ጋር የሀገራችንን የንግድ ሥርዓት ለማዘመን በሚያስችሉ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።
በዚሁ ወቅት የሚኒስቴር መ/ቤቱ የጀመራቸው የዲጂታል ተግባራት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ፈጣን የፋይበር ኮኔክቲቪቲ፣ አስተማማኝና ስኬላብል የክላውድ አገልግሎት እና የስማርት ኃይል ሶሉሽን አስፈላጊነት ላይ ክቡር ሚኒስትሩ አጽንዖት ሰጥተዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ ኩባንያችን ባለፉት አምስት ዓመታት የገነባውን ግዙፍ የመሠረተ ልማት አስመልክተው ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይህም ለዲጂታል አገልግሎቶች መስፋፋት እና ለዘመን ገበያ እውን መሆን መደላድል መፍጠሩን አብራርተዋል።
አክለውም 'ዘመን ገበያ' በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ የዲጂታል ገበያ ትስስር በመፍጠር ለነጋዴዎችና ለሸማቾች የግብይት ሂደቱን እንዳቀላጠፈ፣ ምርቶች በስፋት እንዲቀርቡ እንዳስቻለና አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት አስተዋጽዖ ማበርከት መጀመሩን አስረድተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ውስጥ ኢኮሜርስ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ መንግስት ለዘርፉ አስፈላጊውን የፖሊሲ እና መዋቅራዊ ድጋፎችን ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
አክለውም ዘመን ገበያ የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን እውን ለማድረግ ያለውን ጉልህ ሚና እንዲሁም ኢኮሜርስ እንደ ሀገር የጋራ ራዕይ በመሆኑ ለስኬታማነቱ የመሪነት ሚናቸውን እንደሚጫወቱ ቃል ገብተዋል።
ክቡር ሚኒስትር ለሰጡን የላቀ ማበረታቻና ገንቢ አቅጣጫ እንዲሁም ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ በጋራ ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን።

👍69❤61🤩2🙏1
tgoop.com/telebirr/5567
Create:
Last Update:

BY telebirr

Share with your friend now:
tgoop.com/telebirr/5567