PHRONEMA Telegram 963
+++#የባሕራን_ደብዳቤ#+++

በሰኔ 12 ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ከሚከበርበት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የባሕራንን ደብዳቤ የሚመለከት ነው። ባሕራን መመጽወትና መዘከር ጽኑዕ አገልግሎቱ ከኾነ አባት የተወለደ ነው። እናቱም በዚያ መልካም ግብር ተጸምዳ ትኖር የነበረች ናት። አባትና እናት በአስተሳሰባቸው አንድ ኾነው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሲሠሩ ፡ ጎረቤታቸው ያለው ክፉ ባለ ጸጋ የመልካምነት ክንፉን በቅምጥልነት ሕይወቱ ስላጣው፡ በአስተሳሰብ ልዕልና ከመገኘት ይልቅ መሬታዊ በኾነ ክፋት ቆሳስሏል። የቅዱስ ሚካኤልን መክበር በፍጹም አካሉ፣ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ልቡናው ተጸይፏል። ይህ ሰው ከቤቱ ደጅ ያለውን የመልካምነት ትምህርት ቤት (የባሕራንን ቤተሰብ ሕይወት) ለመማር ባለመፈለግ ደንቁሯል! ይህ በእጅጉ አሳዛኝ የኾነ ሕይወት ነው። የተሰጠውን ሀብት አለመጠቀሙ! ያሳዝናል፤ ያስቆጫልም! ምናልባትም የእኛ ምሳሌ ኾኖ እርሱ ራሱ በአኗኗሩ እንዳይገስጸን እንመርምር!

ባሕራን ስሙን የወረሰው ከተገኘበት ባሕር የተነሣ ነው። ከባሕር ተገኝቶ የተገኘባትን ባሕር በስሙ ተሸክሟት ኖረ። ተወዳጅች ሆይ የተገኘንባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ተሸክመናት ይኾን? ወይስ አኹንም በላዩአ ተንሳፈን እየተጓዝን። ማለትም ተኝተንባት! ንስሓ ላይ ተኝተን፤ ቅድስና ላይ ተኝተን፤ ምጽዋዕት ላይ ተኝተን፤ ክብረ መላእክት ላይ ተኝተን፤ ፈቃደ እግዚአብሔርና ሕገ እግዚአብሔር ላይ ተኝተን የምንጓዘው እስከ መቼ?! ባሕራንን ባሕራን ብሎ የሰየመው የበጎች ጠባቂ እረኛ የነበረው አሳዳጊው ነው። ክርስቲያኖች የኾነውን እኛንም ክርስቲያን ያሰኘን ስለ እኛ የቅድስት ድንግል ማርያምን ፍጹም ሥጋና ነፍስ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ፈቃድ መውጣት ክርስትናን ማጣት መኾኑን ልብ ይሏል።

ከዕለታት አንድ ቀን ባሕራን የጨካኙ ጎረቤታቸውን ሀብት ንብረት የሚወርስ መኾኑ በእግዚአብሔር መልአክ ተነገረ። ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ የባሕራን አባት ሞተ። ባሕራንም የባለ ጸጋውን ሀብት የሚረከብ መኾኑን ባለጸጋው እንዲያውቅ እግዚአብሔር ፈቀደ። ሀብቱ የተሰጠው እንዲጠቀምበት ነበራ! በእጃችን ያለው ገንዘብ እንደ እውነቱ ከኾነ እኛ ጋር ያስቀመጠው የእግዚአብሔር ነው። የተሰጠንን ቍሳዊ ሀብት በፍትሐዊነትና እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ ካልተጠቀምን የሚወሰድብን መኾኑን ልብ እንበል! አስተውሉ!እኛ ራሳችን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መኾናችን ከገባን ሀብት ንብረታችንማ እንዴት የእርሱ አይኾን! አብርሃምን ባለ ጸጋ ያደረገው በተሰጠው ነገር ኹሉ በቅንነት እግዚአብሔርን ማገልገሉ መኾኑን አንድም ከባለ ጸጋው ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ መኖሩ መኾኑን ልብ ይሏል። ባለ ጸጋው ከባሕራን እናት ልጇን የሚንከባከብ መስሎ ተረከበው፤ ወደ ባሕርም በሳጥን አድርጎ አስወረወረው። ከዚያን ባሕራንን ባሕራን ባለው በግ ጠባቂ ባሕራን ባሕር ዳር ላይ ተገኘ። ባሕራንም ተባለ!

ከ20 ዓመት በኋላ ባለጸጋው መንገድ ሲሄድ ባሕራን ካለበት ድንገት ደረሰ። ከአሳዳጊው ታሪኩን ሲሰማ ቀድሞ ያስጣለው መኾኑን ተረዳ፤ የሞት ደብዳቤ አስይዞ ባሕራንን ላከው። የራሱን የሞት ደብዳቤ ይዞ የሚጓዘው ባሕራን ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ወደ ሕይወት ደብዳቤ ገለበጠለት። ብዙዎቻችን ባለማወቃችን ምክንያት የሞት ደብዳቤ ይዘን ወደ ሲዖል እንፈጥናለን። በጭካኔ፣ በጥላቻ፣ ባልተገባ ትችት፣ በሐሜት፣ በሌሎች ሰዎች ውድቀት በመደሰትና በመሳሰሉት የሞት ደብዳቤ ወደ ጥፋት እንፈጥናለን። የዕለት ዕለት የሕይወት መርሐችን ወደ ሞት የሚወስድ እንጂ ወደ ሕይወት የሚያደርስ አይመስልም። ምክንያቱም ዕለት ዕለት እንደ ምግብ ኃጢአትን እየደጋገምን እንፈጽማለንና። እንግዲህ መልአኩ የልቡናችንን ሐሳብ በምልጃው ባያቀናልን ኖሮ እየገሠገሠን ያለነው ወደ ዘረኝነት ሞት፣ ወደ ድንቁርናና ስንፍና ሞት፣ ወደ ቅናትና ትዕቢት ሞት መኾኑን ልብ እንበል!

ቅዱስ ሚካኤል በኃጢአታችን ምክንያት ወደ ተስፋ መቍረጥ የምንጓዘውን ከመንገድ ያግኘን። ከሞት አፋፍ በምልጃው ይታደገን። ወደ ሕይወት የምንገባበትን መልካም ሥራ በሰውነታችን ውስጥ ያለምልምልን። እንግዲህ ያ የባሕራንን ደብዳቤ የሚቀለበስልን በምንሠራው ሥራ አማካኝነት መኾኑን እንረዳ፤ ወደ ጽድቅ እንሩጥ፤ ከጥላቻ ሰውነታችንን እናላቅቅ! ጣዕሙ እጅግ ደስ የሚያሰኘውን የፍቅር ደብዳቤ ከልቡናችን መዝገብ አጽፈን፤ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንገሥግስ። በሕይወታችን ሊገጥሙን የሚችሉትን መሰናክሎች እኛ ባናያቸውም እንኳን መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ይለውጥልናል። ሕይወታችንን በለመለመ የውኃ መስክ አጠገብ የበቀለች ተክል አድርጎ ያሳምረዋል። እንግዲህ የባሕራን ደብዳቤ መነሻዋ ጥፋት መድረሻዋ ግን ሕይወት ኾኗል። አምላካችን እግዚአብሔርም በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ምልጃ የኃጢአት ደብዳቤያችንን ሰርዞ የጽድቅ ያድርግልን አሜን!

tgoop.com/phronema/963
Create:
Last Update:

BY ዮሐንስ ጌታቸው

Share with your friend now:
tgoop.com/phronema/963

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Hui said the time period and nature of some offences “overlapped” and thus their prison terms could be served concurrently. The judge ordered Ng to be jailed for a total of six years and six months. The main design elements of your Telegram channel include a name, bio (brief description), and avatar. Your bio should be: Developing social channels based on exchanging a single message isn’t exactly new, of course. Back in 2014, the “Yo” app was launched with the sole purpose of enabling users to send each other the greeting “Yo.” While the character limit is 255, try to fit into 200 characters. This way, users will be able to take in your text fast and efficiently. Reveal the essence of your channel and provide contact information. For example, you can add a bot name, link to your pricing plans, etc. Those being doxxed include outgoing Chief Executive Carrie Lam Cheng Yuet-ngor, Chung and police assistant commissioner Joe Chan Tung, who heads police's cyber security and technology crime bureau.
from us

Telegram ዮሐንስ ጌታቸው
FROM American