tgoop.com/nshachannel/1161
Create:
Last Update:
Last Update:
+++ "እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር ጉዞ" +++
ጌታችን ስለ በጎ ባልንጀራ ተጠይቆ ለዚያ መልስ እንዲሆን በሰጠው ምሳሌ ላይ ያሉት ሁለቱ ሰዎች (ካህኑና ሌዋዊው) ያስገርማሉ። እነዚህ ሰዎች በመቅደሱ የሚያገለግሉ ሲሆኑ ቆስሎ የወደቀውን ታማሚ ያዩት ካህኑ የመቅደስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ ሌዋዊው ደግሞ ገና ለአገልግሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ ሳይሆን አይቀርም።(ሉቃ 10፥30-35) ከቤተ መቅደስ የወጣውም ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄደውም ያን በሽተኛ አይቶ ገለል ብሎት አለፈ።
ለምን? ከመቅደስ የወጣው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አገልግሎት ጨርሻለሁ ብሎ ስላሰበ፣ ወደ መቅደስ የሚሄደው ደግሞ የወደቀውን ሲረዳ የምስጋና ሰዓቱ እንዳይታጎልበት ሰግቶ እንደ ሆነስ? ማን ያውቃል?!
ብቻ "ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ" በማለት የተናገረውንና ከታማሚው ጋር ያለውን እግዚአብሔር መንገድ ላይ ጥለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ።
እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መሄድ የሚሉት ፈሊጥ ምን ዓይነት ይሆን?
ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ወይም ከቤተ መቅደስ ስንመለስ ስንት ጊዜ እግዚአብሔርን ገለል ብለን አልፈነው ሄድን?
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
BY ፍኖተ ሕይወት

Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1161