tgoop.com/nshachannel/1104
Last Update:
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ስለ_ቤተክርስቲያን
"አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ ትበልጣለች ቢል አልተሳሳተም፡፡ የኖኅ መርከብ እንስሳትን ወደ ውስጥዋ ብታስገባም እንስሳት አድርጋ ጠበቀቻቸው እንጂ አልለወጠቻቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን እንስሳትን ትቀበላለች፤ ትለውጣቸውማለች፡፡ ለምሳሌ ወደ ኖኅ መርከብ ቁራ ገባ፤ የወጣውም ግን ቁራ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ገባ፤ የወጣውም ግን ያው ተኵላ ኾኖ ነው፡፡ እዚህ ቤተ ክርስቲያን ግን አንድ ሰው እንደ ቁራ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ ርግብ ኾኖ ነው፡፡ ተኵላ ኾኖ ቢገባ የሚወጣው እንደ በግ ኾኖ ነው፡፡ እንደ እባብ ኾኖ ቢመጣ የሚወጣው እንደ ጠቦት በግ ኾኖ ነው፡፡ ተፈጥሮው ወደዚያ ስለሚለወጥ ግን አይደለም፤ ክፋቱ ስለሚርቅለት እንጂ፡፡ ስለ ንስሓ አብዝቼ የማስተምረውም ከዚህ የተነሣ ነው፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ (ንስሐ)
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
"ኃጢአት ሠርተሃልን? ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ ኃጢአትህንም አርቃት፡፡ በአደባባይ የምትወድቀው ቊጥሩ ከምትነሣው ጋር እኩል ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በደል ኃጢአት የምትሠራውን ያህልም ፍጹም ተስፋ ሳትቈርጥ ንስሐ ግባ፡፡ ኹለተኛ ብትበድል ኹለተኛ ንስሐ ግባ፡፡ በስንፍና ተይዘህ በፍጹም ምግባር ትሩፋት መሥራት አይቻለኝም አትበል፡፡ በእርግና ዘመን ብትኾንና ብትበድልም እንኳን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆስፒታል እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡ እዚህ ስትመጣ ካህናት [“እግዚአብሔር ይፍታሕ” ብለው] ከኃጢአት እስራት ፈትተው ይቅርታ ይሰጡሃል እንጂ “ለምን በደልህ?” ብለው አይፈርዱብህምና፡፡ ስለዚህ፡- “አንተን ብቻ በደልሁ፤ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ” ብለህ ለእግዚአብሔር ንገረው፤ ኃጢአትህም ይቀርልሃል (መዝ.50፡4)፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1104