tgoop.com/nshachannel/1063
Last Update:
እምነትና መታመን ከአማኝና ከጽኑ ጓደኛ እንደሚወረስ ሁሉ መጠራጠርም ከተጠራጠረ ባልንጀራ ይወረሳል፡፡ ስለሆነም ከእነዚህ ሰዎች ጋር ባልንጀራ ከመሆን መራቅ ይገባል! ይህን ልናደርግ ባንችል እንኳ ንግግራቸውን በንቃት በማዳመጥ የሚሉትን በሙሉ አለማምን ያስፈልጋል፡፡
የመጠራጠር ምንጮች ከሆኑትና ጥርጥሬን ከሚያነሳሱት ነገሮች መካከል አንዱ ንባብ ነው፡፡ መጠራጠር ያለባቸውን መጻሕፍት ሙሉ ለሙሉ ከእኛ አስወግደን ሊገነቡን የሚችሉ መጻሕፍትን መርጠን ማንበብ እንጂ እምነትንንና ሞራልን የሚያጠፉ መጻሕፍትን ማንበብ አያስፈልግም፡፡ አንዳንድ ጸሐፊዎች የጸኑ ጻድቃንን በመቃወም በአንባብያን ውስጥ ጥርጥሬን ያነሣሣሉ፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሌሎች የማያውቁትን እነርሱ እንደሚያደርጉት አድርገው ያቀርባል፡፡ ሌላው የጥርጥሬ መንሥኤ በአብዛኛው ሐሰት ሆኖ የሚገኘው ሐሜት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዙሪያ የሚነጋገሩ ወሬዎችን ማመን የለብንም፡፡ እኛም እነዚህን ሐሜቶች እንደ ገደል ማሚቶ ደጋግመን አናስተጋባ! ይህን የምናደርግ ከሆነ በጥርጥሬ የተሞላን ሰዎች እንሆናለን፡፡
ከዚህ አንጻር የአባታችን የአብርሃምን ታሪክ ስንመለከት እርሱ ለረዥም ዓመታት ምንም ልጅ ሳይወልድ ቆይቷል፡፡ አንድ መከራ ወይም ችግር ገጥሞአቸው ለረዥም ጊዜ ያለ ምንም መፍትሔ የሚቆዩ ሰዎችም በዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡
በመከራ የሚመጣ መጠራጠር
ጌዴዎን በጥርጥሬ ውስጥ በነበረ ጊዜ የእግዚአብሔርን መልአክ የጠየቀው ጥያቄ ለዚህ ምሳሌ ይሆነናል፡፡ ‹‹… እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ እግዚአብሔር ከግብጽ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራቱ ወዴት አለ?›› (መሳ.፮፥፲፫)
ከፊት የተጋረጠ ታላቅ አደጋ ወይም መከራ ሰውን ጥርጥሬ ውስጥ እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡ የእስራኤል ሠራዊት በጎልያድ ፊት የነበራቸው የጥርጥሬ ስሜት ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ግን ከሠራዊቱ በእምነት ምንም ዓይነት ጥርጥሬ ሳያድርበት በሙሉ ልብ ሆኖ ጎልያድን ‹‹እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል…›› ብሎታል፡፡(፩ኛ ሳሙ. ፲፯፥፵፮)
መከራ ለረዥም ጊዜ ሲረዝምና አንድ ሰው በጥርጥሬ ማዕበል ውስጥ ሲወድቅ የእግዚአብሔርን ምሕረት ይጠራጠራል፤ ወይም ሰውየው በእርሱ ላይ ጥንቆላ እንደተደረገበት አድርጎ ስለሚቆጥር የሚመጣበትን ችግር ለማስቆም ወደ ጠንቋዮች ቤት ይሄዳል፡፡ መከራና ረዥም ጊዜ በሀሳብና በጥርጥር ያልተሞላ ብርቱ ልብ ይፈልጋል፡፡
ጥርጣሬ የሰውን ልጅ እምነት ከሚሸረሽሩ ዋነኛ መሰናከያዎች ውስጥ በመሆኑ ውስጣችን እንዲኖር መፍቀድ የለብንም፤ ከእግዚአብሔር የሚያርቀን እና ለጥፋት የሚዳርገን እንዲሁም ከአምላካችን ደኅነትን እንዳናገኝም የሚያግተን በመሆኑ ልንጠራጠር አይገባም፡፡ በዚህ ጊዜም ከመጣው ቸነፈር እና መከራም ፈጣሪያችን ሊጠብቀን በፍጹም ልብ ማመን እንጂ መጠራጠር አይገባም፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን በፍጹም እምነት እንድናምን ይርዳን፤ አሜን፡፡
[ምንጭ፤ የዲያብሎስ ውጊያዎች (፪ኛ መጽሐፍ)፤ በግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ፤ ትርጉም አያሌው ዘኢየሱስ]
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1063