tgoop.com/nshachannel/1057
Last Update:
ራስን መንቀፍ
ራሱን የማይነቅፍ ሰው እርሱ ትክክል እንደሆነና እንዳልተሳሳተ አድርጎ ስለሚያስብ ምንም አይነት ስህተች ቢሰራ እንኳ ይቅርታ አይጠይቅም። ከወንድሙ ጋር ሲጋጭ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ራሱን አያነሣሣም። እርቁ እንዲመጣ የሚፈልገው ከሌላ ወገን ነውና። ግን ለምን? ይህን የሚያመጣው ማንነት ነው! ሌላው ቢቀር እኔነቱ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሠራ አድር ስለሚያሳምነው ስህተቱንም በእግዚአብሔር ፊት እንኳ እይናዘዝም።
ራስን መንቀፍ የሚመጣው ከትሕትና ሲሆን ትሕትና ደግሞ ራስን ወደመካድ ይመራል። ትሑት ያልሆነ ሰው ራሱን አይነቅፋም አይኮንንም። ሁልጊዜ የሚነቅፈው ሆነ የሚኮንነው ሌሎችን ነው። እንዲህ ዓይነቱን ሰው ለምን ሌሎችን እንደሚነቅፍ ብትጠይቁት ይህን በማለታችሁ ብቻ እንኳ ይገሥጻችኋል።
አንድ ራሱን ምንጊዜም በዓለማዊ ዘዴዎች የማያጎላና የማያከብር ሰው ዋናውና ተቀዳሚው ዓላማው ራሱን ከስህተትና ከጥፋት ማንጻት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ሰው ሁልጊዜ ራሱን ይወቅሳል፣ ስህተቶቹን ይመረምራል፣ ለስህተቶቹም ማስተካከያ ይወስዳል፡፡
በአንድ ወቅት ጳጳሱ ቴዎፊለስ መነኮሳት አባቶች የሚኖቱበትን በአት ሲጎበኙ የዚያ ቦታ አስጎብኚ ለሆኑት መነኩሴ በዚህ ሳሉ ስለገኟቸው ቅዱስናዎች ሲጠይቋቸው “እመኑኝ አባቴ! ከሁሉም ነገር በላይ ራስን ከመውቀስ የሚበልጥ ቅድስና የለም!” በማለት መልሰውላቸዋል፡፡ ይህ አንድ ሰው ራሱን ብቻ እንጂ ሌሎች ሰዎችን፣ አካባቢውንና እግዚአብሔርን የማይወቅስበት መንፈሳዊ መንገድ ነው፡፡
ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የወቀሰ ሰው በወዲያኛው ዐለም ከመወቀስ ይድናል። ሰው ራሱን የሚወቅስበት ምክንያት ወደ ንሰሐ ለመቅረብ ነው። ንሰሐ ከገባ ደግሞ እግዚአብሔር ሐጢያቱን ይቅር ይለዋል። ራሱን ከማክበር አንጻር ራሱን የማይወቅስ ሰው ግን ሳይሻሻል በሐጢያት ውስጥ በመወቀስ ይኖራል።
ቅዱስ እንጦንስ “እኛ ራሳችን ከወቀስን ዳኛው በእኛ ይደሰታል።” ብሎ የተናገረው ምንኛ እውነት ነው! ከዚህ በመቀጠልም “እኛ ሐጢያቶቻችንን የምናስታውሳቸው ከሆነ እግዚአብሔር በንሰሐ ይረሳልናል፤ እኛ ሐጢያቶቻችንን የምንዘነጋቸው ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስታውሰናል፡፡” በማለት ተናግሯል።
ራስን መውቀስ ከሰዎች ጋር ለመታረቅ ይረዳናል፡፡ ሰውን “አንተ ትክክል ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አስመልክቼ የተሳሳትሁት እኔ ነኝ . . . ” በማለት ይቅርታ መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ እነዚህ ቃላት የወንድምህን ቁጣ ሰለሚገቱት ይታረቅሃል፡፡ ይህን ሳታደርግ ራስህን ነጻ ለማውጣት የምትከራከር ከሆነ ግን ጠላት ስህተትህን ለማጋለጥ ማንም አይደርስበትም፡፡
ይህን አስመልክቶ ቅዱስ መቃርስ የተናገረው አባባል ምነኛ ድንቅ ነው! “ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ሳይወቅሱህ አንተ ራስህን ውቀስ!”
[አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ]
BY ፍኖተ ሕይወት
Share with your friend now:
tgoop.com/nshachannel/1057