tgoop.com/learn_with_John/722
Last Update:
"መልካም ነው የዛሬው ቀጠሮዋችን የጻድቃን ቀጠሮ ይመስለኛል፡፡" አልኩት ፈገግታ በተሞላበት ገፅታ ፤
"እርሶ ያሏቸውን ሁለት ሀሳቦች እኔም ሳላስባቸው ውዬ አድሬ አላውቅም ፤ የአቅም ማነስ ስላለብኝ እንጂ በምችለው ሁሉ አቋሞን ለመጋራት ዝግጁ ነኝ፡፡ አይጠቅምም እንጂ የሚጠቅም ከሆነ ዛሬውኑ ለሀገሬ ብሞት ለነፍሴ አልሳሳም፡፡ ነገር ግን ቅድም ባነሷቸው ሁለት ሐሳቦች የምንቸገር ይመስለኛል፡፡ስለ ዕፅዋት ምርምርና ስለአቡሻኸር የቀመር ትምህርቶች የመማር ፍላጎት ነበረኝ ሰው ማግኘት ስላልቻልኩ ነው እንጂ፤አሁን አሁን ትምህርቱ እየጠፋ ስለመጣ እሱን ለማግኘት ሳንቸገር አንቀርም፡፡ሌላውየዕፅዋትየምርምሩን ከፍተን ስራ ስንጀምር በህብረተሰቡ በኩል ሊመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ እንዴት እንደምንቋቋመው ብናስብበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ተቃውሞው የሚበረታው የቆሎ ተማሪ ሁነህ ስትሰራው ነው፡፡ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ሜድስንና የፋርማሲ ተማሪዎን በአይጥና በዝንጀሮ ሲገፉ ቢውሉ ስማቸው ዶክተር ነው፡፡ አንድ ቆሎ ተማሪ ግን ይህንን ሲያደርግ ሲታይ መጠርያ ስሙ ጠንቋይ ነውየሚባለው"አልኩት፡፡
"ብቻ አብረከኝ ለመስራት ዝግጁ ሁን እንጂ እሱ አንተን አያሳስብህም፡፡ ትምህርቱ ጠፍቷል የሚያስብል መጃ የለም አልጠፋም፡፡ ኢትዩጵያ ውስጥ ጠፍተዋል የሉም የሚባሉት ሁሉ እውነት የጠፋ እንዳይመስልህ አልጠፉም፡፡ የጠፋው የግል ጥቅም ሳያሸንፈው ኢትዩጵያን ማገልገል የሚችል ሰው ነው ፡፡"
" ይህ ትምህርት ኢትዮጵያ ውስጥ ላለመጥፋቱ ምን ማረጋገጫ አለህ"አልኩት በንግግሩ መሀል ጣልቃ ገብቼ፡፡
" እኔ ረጅም ጊዜዬን ያሳለፍኩት እንዲህ አይነት ሙያ ያላቸውን በመፈለግ ነው፡፡ በዚህ የስራ ቆይታዬ ኢይዩጵያ ውስጥ ምን እንዳለና ምን እንደሚሰራ፣ የሚያስፈልጋት ምን እንደሆነ ሳጠና ነው የቆየሁት አንተ ጠፍተዋል ያልካቸው የአቡሻኸር መምህራንም ከየትኛው ገዳም እንዳሉ እስከተደበቁበት ዓላማ ድረስ መረጃው አለኝ፡፡እኔ ያጣሁት አብሮኝ የሚሰራ ሰው ብቻ ነው፡፡ ሁለተኛው ሀሳብም ቢሆን ያን ያክል የሚያሳስብ አይደለም እውነት ነው ተነክቶ የማያውቀውን ሀሳብ ስትነካና ስትጀምር ለግዜው ጠንቋይ ተብለህ መጠራትህ የማይቀየር ነው፡፡ ውጤታማ ስትሆን ደግሞ ስምህ ይቀየራል ፤ ይህ ማለት ዶክተር ተብለህ በክብር ትጠራለህ፡፡ ምን ግዜም አንተ መልካም ነው ያልከውን ሐሳብ ስትጀምረው ሁሉም ሰው ላይወድልህ ይችላል፡፡ኪሳራም ትርፍም እንዳለ በማሰብ ውጤቱ ላይ አተኩረህ ከሰራህ ደግሞ ተቋዋሚህ ደጋፊህ ይሆናል" አለኝ፡፡
በምወዳት ሀገሬ ምዬ ሀሳቡን ለመጋራት ቆርጬ መነሳቴን ገለፅኩለት ፡፡ሌላ ግዜ ለመገናኘት በቀጠሮ ልንለያይ ስንል" ሐሳቤን ስለተጋራኸኝ አመሰግንሃለሁ በዚህ አቋምህ ከፀናህ በሚቀጥለው ቀጠሯችን ለረጅም ጊዜ የሰበሰብኳቸውን ውድ የጥበብ መፃሀፍ አሳይለሀለው "ብሎኝ ተለያየን፡፡
ፌላሌምሌሞንም🌱
ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል ....😍😍😜
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/722