tgoop.com/learn_with_John/717
Last Update:
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"
+ የሰጠኸኝ ሴት +
እግዚአብሔር አዳምን "አትብላ ካልሁህ ዛፍ በላህን?" ብሎ ጠየቀው:: አዳምም :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ አለ::
የሰጠኸኝ ሴት! በጣም ይገርማል:: ሚስቴ አላለም::
አዳምና ሔዋን የተገናኙ ቀን አዳም ያለውን አስታውሱ
"ይህች አጥንት ከአጥንቴ
ይህች ሥጋ ከሥጋዬ" ብሎአት ነበር::
ምንም እንክዋን አዳም ወላጆች ባይኖሩትም ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ብሎም ነበር::
ራቁታቸውን ቢሆኑም አይተፋፈሩም ነበር::
አሁን በራቁቱ ብቻ ሳይሆን በሔዋንም አፈረባት::
እናትና አባቱን ይተዋል እንዳላለ ሔዋንን ራስዋን ተዋት::
ከሚስቱ ጋር መተባበር ቀርቶ ክስ ጀመረ::
አካሌ አጥንቴ ሥጋዬ ማለቱ ቀረና የሠጠኸኝ ሴት አለ::
የጫጉላው ጊዜ አለፈና ከሚስትነትዋ ሴትነትዋ ብቻ ታየው::
በጋብቻ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሠጠንን ነገር
ሁሉ ቀድመን የራሳችን እናደርጋለን ነገሮች ሲበላሹ ግን ባለቤትነቱን ወደ እርሱ እንመልሰዋለን::
የሠጠኸኝ ሥራ
የሠጠኸኝ ወላጆች
የሠጠኸኝ ሰፈር
የሠጠኸኝ ሀገር
የሠጠኸኝ መሪ
የሠጠኸኝ ጓደኞች
የሠጠኸኝ ደካማ ሥጋ
የሠጠኸኝ ዓይን...
ትናንት ሲሠጠን ዘምረን የተቀበልነውን ሥጦታ ዛሬ ለምሬት እንጠቅሰዋለን:: የሠጠኸኝ የሠጠኸኝ .... ሠጠኝና በላሁ ብለን ቀርጥፈን ለበላነው ዕፀ በለስ ፈጣሪን እንከስሰዋለን::
✍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹
🕊 🕊 🕊 🕊 🕊 🕊
🕊 🕊🕊
🕊
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
🌹 የእግዚአብሔር ቸርነት 🌹
🌹 የእመቤታችን ጸሎት 🌹
🌹 የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ🌹
🌹 የቅዱሳን ሁሉ በረከትና ረድኤት 🌹
ከሁላችን ጋራ ይሁን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
የፍቅር ዘመን፤ የቸርነት ፤የይቅርታ፤የምህረት አመት ያድርግልን፤
🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🥀🕊🥀🌹🥀 🕊🥀🌹🥀🕊🥀🌹🥀🕊
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
🕊🕊 🕊 🌹🌹🌹🕊🕊🕊
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/717