tgoop.com/learn_with_John/704
Last Update:
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"
✍ "ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ልጆቿን ትጣራለች፦ ሁላችሁም ስሟት በሩቁ አትሳለሟት ይልቅስ ቀርባችሁ ተማሯት ከእውቀት የጎደለች የመሰላችሁ በጥበብ ሞልታ ታይዋታላችሁና፤ ከወንጌል የሽሽች የመሰላችሁ ወንጌልን ለብሳ ታዩዋታላችሁና፤ ከክርስቶስ የራቀች የመሰላችሁ ክርስቶስን ስታነግስ ታይዋታላችሁና።
✍ ኑ እናንተ የክርስቶስ ወዳጆች ወደ ክርስቶስ ቅረቡ ኑ ኦርቶዶክሳዊነታችሁን በስም ብቻ አታድርጉት ይልቅስ የህይወት መንገድ እንደሆነች እወቁና በዚህች መንገድ ላይ ተጓዙ፡፡
✍ ኑና ተዋህዶን ግለጧት አንብቧት እዩዋት መርምሯት ፈትሿት፤ የክርስቶስን ምስጢረ ተዋህዶ ታሳያለች፣ የክርስቶስ የአምላክነት ክብር ታስረዳለች፣ የክርስቶስን ሞትና መከራ ታሳስባለች፣ የክርስቶስን ትንሳኤና እርገት ታሳውቃለች፣ የክርስቶስን ዳግም ምፅአት ታመላክታለች።
✍ ተዋህዶን አንብቧት ክርስቶስን ታዩታላችሁ፤ ነገር ግን በትእቢት አይደለም በትህትና ነው እንጂ፤ ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ አይደለም በማሳነስ ነው እንጂ፤ በአፍ አይደለም በህይወት በመኖር እንጂ፤ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ልጆቿን አሁንም ኑ ልጆቼ እያለች ትጣራለችና ቀርበን ፍቅሯን እንቅመስ፤ ማንም ይህንን ፍቅር ቀምሶ ያተረፈ እንጂ የከሰረ፣ ቀና ያለ እንጂ አንገቱን የደፋ፣ የተደሰተ እንጂ የተከፋ፣ ዘለዓለማዊ ህይወትን ያገኘ እንጂ የሞት ሞትን የሞተ የለምና"::
ቃለ ሕይወትን ያሰማን
የሰላም ሌሊት ያድርግልን እግዚአብሔር
የትንቢቱ መፈጸሚያ ከመሆን ይሰዉረን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/704