tgoop.com/learn_with_John/677
Last Update:
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"
💥 ተወዳጆች ሆይ! ትዘምራላችሁ፡፡ [ከጸሎታቱ ትሳተፋላችሁ፡፡ ቅዳሴውን አስቀድሳችሁ] እምነታችሁን ትመሰክራላችሁ፡፡ ይህን ኹሉ አድርጋችሁ ስታበቁ ግን አትቆርቡም፡፡ ለምን? ከሰማያዊው ማዕድ የማትሳተፉት ለምንድን ነው? አንዳንዶቻችሁ፡- “እኔ ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ ልቆርብ አይገባኝም” ብላችኋል፡፡ እንዴ! እንደዚህ’ማ ካላችሁ ከመዝሙሩም፣ ከጸሎታቱም፣ ከቅዳሴውም ልትሳተፉ አይገባችሁማ!
💥 እስኪ ንገሩኝ! የንጉሥ ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ መላእክት “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” እያሉ የሚያመሰግኑት የሚያገለግሉትም ማዕድ በፊታችሁ አለ፡፡ ንጉሡ በፊታችሁ አለ፡፡ ታዲያ እናንተ እንዲሁ ቁልጭልጭ እያላችሁ ትቆማላችሁን? ልብሳችሁ አድፎ ተዳድፎም ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረ ኾናችሁ ወደ ቤታችሁ ትመለሳላችሁን?
💥 ወደ መንግሥተ ሰማያት፣ ወደ ሰማያዊው ንጉሥ ማዕድ ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠርቶን ሳለ ተዘጋጅተን እንደ መቅረብ ወደ ኋላ እንላለንን? እንደዚህ የምናደርግ ከኾነ ታዲያ ተስፋ ድኅነታችን ምንድን ነው?
💥 “መቅረብ ያልቻልኩት’ኮ” ብለን ደካማ መኾናችንን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንችልም፡፡ ተፈጥሮአችንን እንደ ምክንያት ማቅረብ አንችልም፡፡ እንዳንቀርብ የሚያደርገን ደካማ መኾናችን አይደለም፡፡ አዎን ከሰማያዊው ማዕድ እንዳንሳተፍ የሚያደርገን እንዲሁ ሳንዘጋጅ ልል ዘሊላን ኾነን መቅረባችን እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡
💥 ስለዚህ እማልዳችኋለሁ!
🥀ንስሐ ገብተን እንደ ቸርነቱም ተዘጋጅተን
🥀 በፍርሐትና በረዓድ ኾነን [በግድ]
እንቅረብ እንጂ “ኃጢአተኛ ስለ ኾንሁ”
ብለን አንራቅ፡፡
🥀 ከኃጢአት ኹሉ የሚያነጻን የክርስቶስ ደም እንጂ ኃጢአተኛ ነኝና አይገባኝም ብለን መራቃችን አይደለምና፡፡
💥 ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በድፍረት ወደ እርሱ መቅረብ ይቻለን ዘንድ ዛሬ በፍርሐትና በረዓድ ኾነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ ያኔ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” ከሚላቸው ጋር ዕድል ፈንታችን ፅዋ ተርታችን በመንግሥተ ሰማያት ይኾን ዘንድ ዛሬ ወደ ሰማያዊው ማዕድ እንቅረብ፡፡
✍በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
📚 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ እንደተረጎመው
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/677