tgoop.com/learn_with_John/674
Last Update:
መልክአ ኢየሱስ ለበረከት በጥቂቱ
🌹🌹🍀🍀🌹🌹🍀🍀🌹🌹🍀🍀
ለአዕይንቲከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
ምሉዕ የሆነ እንደጠራ የምንጭ ዉሀ ለሚሆኑ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ጌጥን በተጌጠ የአቀማመጥ መነፅር የሚተያዩ ናቸውና፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ኃጢአትን ሁሉ ይቅር የምትል ይቅር ባይ ነህና፡፡ አቤቱ በይቅርታህመነሳንስ እርጨኝ፡፡ ከበረዶም እነፃ ዘንድ ከኃጢአቴ እጠበኝ፡፡
ለአእዛኒከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
የፍጥረትህን ጥሪ ከመስማት ቸል ለማይሉ ጆሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህሊናትን ሁሉ ለሚገዛ ውስጣዊ ህሊናህ ጉዳዩን ያስተላልፋሉና፡፡
ለዘባንከ
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠር ግርፋትን ለተቀበለ ዘባንህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ይህም ሁሉ ሲሆን መለኮቱ ከሱ አልተለየምና፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ልምላሜንና የፍሬ ዘለላን የተሸከምክ የወይን ሐረግ ግንድ ነህ፡፡ ለወዳጅህ የሠርግ ቤትን ባዘጋጀህ ጊዜ፡፡ እኔን የማዕዱ አስተናባሪ (የወይን ማድጋ?) አድርገኝ፡፡
ለልብከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
መንታ ለሆኑ ኩላሊቶችህ አቀረብ ለሚሆን ልብህ ሰላምታ ይገባል፡፡ የኅሊናህ መንፈስ ወደ አነዋወሩ የሚመላለስበት ነውና፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ሥጋን ከመለኮት ጋር ያዋሐድክ ፍጹም አምላክ ነህ፡፡ ስለ አንተ በቀል ነነዌ በተፋረደች ጊዜ፡፡ በመቅደስህ ውስጥ አለቃ አድርገኝ
፤ ለኅሊናከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
የበጎ ነገር ምንጭ ለሆነ ኅሊናህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ለሰው ልጅ ሁሉ ቸርነትን ከማድረግ አይቆጠብምና፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከዓለም ላይ ጨለማን ያስወገድህ እውነተኛ ብርሃን አንተ ነህ፡፡ ከላይ በኪሩቤል ላይ ተቀምጠህ የውቅያኖስን ጥልቅነት ትመለከታለህ፡፡ ስለዚህም ልዑልና የተመሰገንህ ነህ፡፡
ለአብራኪከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
የምድር ነገሥታት የሰማይ መላእክት የሚሰግዱላቸው፡፡ ከላይ ወደታች ከታች ወደ ላይ በማለት ስግደትን ላዘወተሩ ጉልበቶችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ለመታሰቢያህ የሚሆን የአልባስጥሮስን ሽቱ በተቀባህ ጊዜ፡፡ በዚያን ቀን ወይም ያን ጊዜ፡፡እህት በሆነችኝ በወደድሁ ነበር፡፡
ስብሐት ለከ አምላኪየ፡፡
አምላኬ ሆይ፤ በራስ ጠጉሬ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ፤ በአጥንቶቼ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል፡፡ ጌታዬ ሆይ፤ በሚታየው ሁሉ ቁጥር ምስጋና ይገባሃል፡፡ ንጉሴ ሆይ፤ በማይታየውም ሁሉ ቁጥር ምስጋና ይባሃል፡፡ የሦስትነትህንም ምስጋና ሁል ጊዜ አፌ ይናገራል፡፡
ሰላም ሰላም ለኮሎን መልክእከ፡፡
ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤
ከአባትህ መልክ ልዩነት ለሌለው መልክህ ደግሜ ደጋግሜ ሰላም እላለሁ፡፡ ለእኛ ስትል ዓሥራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል ለተቀበልክ ላንተ ምስጋና ይገባል፡፡
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ስለ እናትህ ስለ ማርያም ብለህ ከዓይነ ሞት ሠውረኝ አምላኬ አምላኬ ስልህ ልቡናህ አይጽናብኝ፤ አዳኚዬ አምባ መጠጊያዬ አንተ ነህና
አምላከ ምድር ወሰማያት፡፡
የሰማይና የምድር አምላክ ሆይ፤ የባሕርና የቀላያት አምላክ ሆይ፤ የፍጥረቱ ሁሉ አምላክ ሆይ፤ የቀደሙ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ፤ የመላእክት አምላክ ሆይ፤ የነቢያትና የሐዋርያት አምላካቸው ሆይ፤ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ሆይ፤ አቤቱ ሁላችንን ማረን ይቅር በለን፡፡ በደላችንንም አታስብብን፡፡ የእጅህ ሥራዎች ነንና፡፡የእኔንም የአገልጋይህን በደሌን ፋቅልኝ አጥፋልኝ አሜን፡፡
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/674