tgoop.com/learn_with_John/672
Last Update:
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም
እምይዕዜሰ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሰላም።"
#በውስጣችን_ፍቅረ_እግዚአብሔር_እንዳይለመልም_ምን_ያግደዋል?
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
# መፍረድ፣
# አለመርካት፣
# ማጉረምረም፣
# ምስጋና_ቢስነትና_ትእዛዛቱን_አለመፈጸም ያግዱናል።
በማንኛውም ሁኔታ ደስተኞች ከሆንንና፣ ስለ ሁሉም ነገር የምናመሰግነው ከሆነ፤ እግዚአብሔርም ይደሰትብናል። መከራ ቢገጥመንም እንኳን እንቅረበው፣ እናመስግነው። ከዚያም "እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ ፈቃድ ቢሆን'ኮ ይህንን መከራ ከእኔ ለማስወገድ አይሳንህም ነበር" እንበለው። ችግሩ ሁሉ ይወገዳል።
ማጉረምረምን ትተን አመስጋኞች መሆን ይጠበቅብናል። እያንዳንዳችን የምስጋና ቃላትን መናገር ከተለማመድን (ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ፥ የልብ ሳይሆን የአንደበት ብቻ ቢሆንም)፤ ከጊዜያት በኃላ ልምዳችን ይሆንና ከሙሉ ልባችን እንናገረዋለን (እናመሰግናለን)። ቢሆንም ግን "#ላመሰግንህ_ሻለሁና_ከሙሉ_ልብ_የመነጨ_የምስጋናን_ቃላት_በአንደበቴ_አኑር" ብለን ልንማጸነው ይገባል። ሁሉ በእጁ የሆነ አምላክ ወዲያው ይሰጠናልና።"
✍✦እማሆይ ኄራኒ✦
የሰላም ሌሊት ያድርግልን
ምስጋና ይሁን
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ
አንድ አምላክ ለሚሆን እስከ ለዘለዓለም
አሜን አሜን አሜን
BY እልመስጦአግያ+++
Share with your friend now:
tgoop.com/learn_with_John/672