Telegram Web
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ወንድም እህቶች ቲክቶክ መንደር ምንም ኸይር ነገር ቢተላለፍም እንኳን አለመጠቀሙ 90% ጠቃሚ ነው

ስለሆነም  ወንድምም ሆናችሁ እህቶችም ኡስታዞችም እባካችሁ ወደ ቲክቶክ መንደር ሙስሊሞችን አትጋብዙ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ ነው

ከቻላችሁ በቲክቶክ ላይ ያሉ ሙስሊሞችን ወደ ቂርአት ሴንተር ወደ ሌሎች ሚድያወች አምጡ

በሆነ ጊዜ እኔም ገብቸ የሚተላለፈው ነገር አይደለም ወጣቶችን ህፃናትን የሚያታልሉ ነገሮች ናቸው ያሉት እንደኔ ቲክቶክ ያስጠላል ።

ከሚድያ ሁሉ የምጠላው ቢኖር ቲክቶክ!!

✍️ወንድም አቡ ረያን
👍20
وخيرُ من نبتدأ بهِ أيّامنا، كلامُ المولى عزّ وجلّ، فالحمدُ للهِ الذِي جعل أُنسنا فِي كتابهِ.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ما هو أفضل شيئ يتركه للإنسان بعد موته: العلم أم
الصدقة الجارية أم ولد صالح يدعو له؟

🎙الشيخ عزيز بن فرحان العنزي حفظه الله
የእስልምና መግቢያ ስለሆነው
ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱ ረሱሉላ አጠር ያለች ትምህርት

በኡስታዝ አቡ ሙዓውያ ሰዒድ  ሙ/ኑር....
ነገ ማታ
🔖 የጧት ዚክር አትርሱ ...!
~    ~    ~    ~     ~   ~   ~
🌻اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَاْلآخِرَةِ، اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِيْنِيْ وَدُنْيَايَ وَأَهْلِيْ وَمَالِيْ. اَللَّهُمَّ احْفَظْنِيْ مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِيْ، وَعَنْ يَمِيْنِيْ وَعَنْ شِمَالِيْ، وَمِنْ فَوْقِيْ، وَأَعُوْذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِيْ.
#አላህ ሆይ! በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታንና ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡

አላህ ሆይ! በሀይማኖቴ፥ በዚህች አለም ህይወቴም፥ በቤተሰቦቼም፥ በንብረቴም ደህንነትን እጠይቅሃለሁአላህ ሆይ! ነውሬን ሸፍንልኝ፡፡

አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴ  ከኃላዬም፥ ከቀኜም፥ ከግራዬም፥ ከበላዬም ጠብቀኝ፡፡ ከበታቼም እንዳልጠቃ በአንተ እጠበቃለሁ፡፡
   ~
   
www.tgoop.com/https_Asselfya
ወንጀል ኒዕማን(ፀጋን) ያስወግዳል!
2025-07-13
የኮምቦልቻ አህለ ሱና አንሷር መስጅድ ጀመዓ ግሩፕ
💫አድስ ሙሀደራ

🖍እንኮን ደህና መጣችሁ እና ትውውቅ

🎧በሸይኽ አቡ ሙሀሐድ አል-ፋቲህ

በመስጂድ አንሷር ኮ/ቻ

https://www.tgoop.com/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
من الذي فرح بموت الشيخ ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله؟
الشيخ محمد بن هادي المدخلي حفظه الله
من الذي فرح بموت الشيخ ربيع بن هادي
المدخلي- رحمه الله
.

🎙الشيخ محمد بن هادي المدخلي - حفظه الله
...
የጁሙአ ቀን ከሚሰሩ መልካም ስራዎች ውስጥ አንዱ በውዱ ነብያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ ነው። በስራም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ውዱእ ቢኖረንም ባይኖረንም ሰለዋት ማውረድ ትልቅ ምንዳ ያስገኛል።

💦የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ ሰው፦
🔹በአስር እጥፍ አላህ በሱ ላይ ያወርድበታል
🔹አስር መጥፎ ሰራዎች ይሰረዝለታል
🔹አስር ደረጃዎች ከፍ ይደረጋል

📚الباني (صحيح النسائي) جـ1 ص415

◾️اللہم صلے علی محمد وعلے آل محمد کما صلیت علے إبراھیم و علے آل إبراھیم إنک حمید مجید وبارک علی محمد وعلے آل محمد  کما بارکت علے إبراھیم و علے آل إبراھیم إنک حمید مجید
~
www.tgoop.com/https_Asselfya
👍1
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor
አይበቃም ወይ? !
የተከለከሉ ነገሮችን በማየትና በመስማት በርካታ ግዜዎችን አባከን!
የቢድዐ እና የወንጀል ሰዎችን አሉባልታ በመስማትና ሟርተኞች ጋር በመቀማመጥ አመታትን በፌዝ ገፋን! !
ቁጥራቸው የበዛ ቀናቶችና ሌሊቶች ክልክል ነገሮች ታይቶባቸውና ተሰርቶባቸው አለፉ! ! ሁሉም ነገራችንም ተፃፈ!! አንድም ሳይቀር!!
የሸሪዐ ትምህርት መማርን አውርደን በመመልከትና በመዘንጋት ዱንያን በመገንባት ላይ ብቻ ተጠምደን ኢማናችንን አከሰምን! መልካም ስራዎቻችንን አደከምን!!
ወንጀሎችን አለቅጥ በመዳፈር ልባችንን በገዛ እጃችን ገደልን!!! ደካማው ቀልባችን ቁስሉ ፣ በሽታው፣ ጥፋቱ የማይሰማው ሙት እና ደነዝ ሆነ— በዱንያ ስካርና ሐራምን በመዳፈር! !
አረ ይብቃን! ቀብር ያለበት ፣ አኺራ የሚጠብቀው እንምሰል እንጂ! ! የረከሰውን ዱንያ እንገነባለን ብለን አኺራችንን አናፍርስ!! በወንጀሎች "የሚገኘውን" ግዚያዊ እና እንስሳዊ ደስታ በመፈለግ ቀብራችንን አናጨልም! !

አላህን እንፍራ! !
👍10
▪️ከአኼራ የምንዘናጋለት
▪️እርስ በርስ የምንባላበት
▪️አንዱ ሌላው የሚገልበት
▪️እርስ በእርስ የተጨካከንበት
▪️ለሱ ብለን አላህን የምናምፅባት
➡️ዱንያ እውነታው ይህ ነው


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

በአላህ እምላለሁ! ዱንያ (በአጠቃላይ) ከአሄራ አንፃር ስትታይ አምሳያዋ፦ ጣቱ ባህር ውስጥ አስገብቶ እንደሚያወጣው አይነት እንጂ ሌላ አይደለም። (ጣቱ ምን ያክል ውሃ) ይዞ እንደሚወጣ ይመልከት።

📚(ሙስሊም ዘግቦታል)

www.tgoop.com/https_Asselfya
👍2
የልብ መድረቅ በሽታ አደጋው ከባድ ነው። ልቡ የደረቀ ሰው ሐራም መዳፈር ያበዛል። ወንጀል እየፈፀመ አይደነግጥም። የሰው ሐቅ መዳፈሩ አያስጨንቀውም።
ይሄ ሲሆን ዒባዳው ለዛ ያጣል። መስገድ መፆሙን እንጂ የሚያየው የዒባዳውን አሻራ አይፈትሽም።
ልባችንን እንከታተል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
👍5
ስኬታማ ትዳር ለመመስረት የሚረዱ ምክሮች

1. አላህን መፍራት (تقوى الله):

•  ለአላህ ታማኝ መሆን: በትዳር ውስጥም ሆነ በሌላው የሕይወት ዘርፍ አላህን መፍራት እና ትእዛዛቱን መፈጸም ግደታ ነው ፤ ይህም ለትዳር አጋር ታማኝ መሆንን ይጨምራል።
•  የትዳር ትክክለኛውን አላማ ማወቅ: ትዳር ለመመሥረት ዋናው አላማው አላህን መታዘዝ እና መልካም ዘርን ማፍራት መሆን አለበት።
•  በዱዓ  ላይ መበርታት: በመጀመሪያ አላህ መልካም ባል ወይም ሚስት እንዲሰጥ መማጸንና በተጨማሪ አላህ ትዳራችንን እንዲባርክልን መለመን ይኖርብናል።

2. በመልካም ስነ-ምግባር ላይ የተመሰረተ ትዳር መገንባት (حسن الخلق):

•  ለትዳር ስንመርጥ ዲንን መመልከት: ዲን ያለው/ያላት (ሃይማኖተኛ) የትዳር አጋር መፈለግ፤ ምክንያቱም ዲን ትክክለኛውን መንገድ ለመከተል ይረዳል።
•  መልካም ስነምግባር: ጥሩ ስብዕና፣ ገርነት፣ ትህትና እና ለሰዎች ደግ መሆን በትዳር ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
•  በመንሐጅና በአቂዳ ተመሳሳይ መሆን: በአመለካከት፣ በእሴቶች እና በአኗኗር ዘይቤ ተስማሚ የሆነን ሰው መምረጥ።

3. በትዳር ውስጥ መተዛዘንና መዋደድ (المودة والرحمة):

•  ለጋስ መሆን: ለትዳር አጋር በገንዘብም ሆነ በስሜት ለጋስ መሆን እና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማሟላት።
•  ርህራሄና መተሳሰብ: የትዳር አጋርን ስሜት መረዳት፣ ማዘን እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መደገፍይኖርብናል።
•  ይቅር መባባል: በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩትን ጥቃቅን ስህተቶች ይቅር ማለት እና ቂም አለመያዝ፤ ምክንያቱም ፍጹም የሆነ ሰው የለምና  ጥፋት ሲኖር ፈጥኖ ይቅርታ መጠያየቅ ይቅር መባባል ይኖርብናል።

4. ምክክር (الشوری):

•  በጋራ መመካከር: በትዳር ሕይወት ውስጥ ትልልቅ ውሳኔዎችን በሚወስኑበት ጊዜ በጋራ መመካከርና መወያየት፤ ይህም የሁለቱንንም አስተያየት ግምት ውስጥ ማስገባት ያካትታል።
•  አክብሮት: የትዳር አጋርን አስተያየት ማክበር እና በጥሞና ማዳመጥ።
•  መተማመን: በጋራ በመመካከር ውሳኔዎችን መወሰን በመካከላችሁ መተማመንን ይጨምራል።

5. የትዳር ግዴታዎችን መወጣት (حقوق الزوجية):

•  ባል ለሚስቱ: ሚስቱን መንከባከብ፣ መጠበቅ፣ መመገብ፣ ልብስ ማልበስ እና ጥሩ መኖሪያ ማዘጋጀት። በተጨማሪም በትህትና መያዝ፣ ማስተማር እና በሃይማኖቷ ላይ መርዳት።
•  ሚስት ለባሏ: ባሏን ማክበር፣ መታዘዝ (በመልካም ነገር)፣ ቤቱን መጠበቅ፣ ልጆችን መንከባከብ እና የባሏን ስም እና ንብረት መጠበቅ ይኖርባታል።

6. ትዕግስት እና ይቅርታ (الصبر والصفح):

•  በትዕግስት መጽናት: በትዳር ውስጥ ችግሮች እና ፈተናዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ስለዚህ በትዕግስት መጽናትና መፍትሄ መፈለግ ያስፈልጋል።
•  ይቅር ማለት: የትዳር አጋርን ስህተት ይቅር ማለት እና ቂም አለመያዝ ትዳርን ያጠናክራል።
•  ከስህተት መማር: ከስህተት ተምሮ ወደፊት ላለመድገም መሞከር።

7. የቤተሰብን ትስስር መጠበቅ (صلة الرحم):

•  ዘመዶችን መጎብኘት: የሁለቱም የትዳር አጋሮች ዘመዶችን መጎብኘትና መልካም ግንኙነት መፍጠር።
•  ዘመዶችን መርዳት: ችግር ላይ የወደቁ ዘመዶችን መርዳትና አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት።
•  በዘመዶች መካከል ሰላምን ማስፈን: በዘመዶች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ለማስታረቅ መሞከር።
እነዚህና ሌሎችም ብዙ ያልተጠቀሱ ትዳራችንን ስኬታማ የሚያደርጉ ምክሮች አሉ... እነዚህ በመማርና በመተግበር ትዳራችንን ስኬታማ ማድረግ ይኖርብናል።

አላህ ላከቡት ትዳራቸውን ያሳምርላቸው ላላገቡት ሷሊህ የሆነ ትዳርን ይወፍቃቸው

ወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን ኢስማኢል

https://www.tgoop.com/Abu_hibetillah_Asselfiy
👍4
«የሆነ ዘመን አጥንቴ ውልቅልቁ ወጥቶ ስጋዬ ከአፈር ተዋህዶ ማንነቴ ተበታትኖ እኔም መረሳቴ የማይቀር ነው።!!

"ደግሞ ሩቅ እኮ አይደለም ቅርብ ነው በአብዛኛው ከዛሬ መቶ አመት ወዲህ ነው የሚሆነው።!!

"ይህንን ሳስበው ግን እኔም የዱንያ እንዳልሆንኩ ዱንያም የኔ እንዳልሆነች አስባለሁ።ይህን የማስበው ግን የሆነች ነገር ሥትመጣ ነው
አሏህ ሆይ መጨረሻችንን አሳምርልን።
👍15
((ኢማንን ማደስ! ቁ 1))

~

🛑👉የሰው ልጅ በዚህ አለም ሲኖር ከሚያሳስቡት ነገር ሁሉ ሊያሳስበው የሚገባው የኢማኑ ጉዳይ መሆን አለበት!
ነፍስ ከምከስበው ትልቁ ነገር ቢኖር ኢማን ነው። አንድ ባሪያ በኢማን ሰበብ በዱኒያም ይሁን በአኼራ ትልቅ ቦታን ያገኛል። እንደውም የዱኒያም ይሁን የአኼራ መልካም ነገር በኢማን የተገደበ ነው።
ኢማን ይህ ከሆነ እያንዳንዳችን ኢማናችንን መከታተል ግድ ይለናል! እውን ኢማናችን እየጨመረ እና የጠነከረ ነውን? ወይንስ በተቃራኒው እየቀነሰ እና እየተዳከመ ነው? ኢማን ማንኛውንም ነገር ከማደስ የበለጠ ማደስን ይፈልጋል!
ኢማንን ብዙ የሚያዳክሙት ነገሮች አሉ ለምሳሌ:- የዱኒያ ፊትና፣የሰይጣን ወስዋስ፣መጥፎ ጓደኛ፣መጥፎ ቅልቅል(አላህ የሚታመፅበትን ሰርግ ይመስል)፣በመጥፎ የምታዝ ነፍስ እና ሌሎችም ኢማንን የሚያደክሙ ከዚህም አልፈው ከመሰረቱ የሚያጠፉት ነገሮች አሉ።

🛑👉መልእክተኛው ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላአሉ:-
"ኢማን ከናንተ በአንዳችሁ ሆድ ውስጥ ልክ ልብስ እንደሚያልቀው(እንደሚያሩገው) ያልቃል(ያሩጋል) አላህ በቀልባችሁ ውስጥ ኢማንን እንዲያድስላችሁ ለምኑት" አልባኒ ሶሂህ ብለውታል(ሲልሲለቱ ሶሂህ ቁ 1585)

🛑👉መልእክተኛው ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም በዚህ ሀዲስ አላህ በቀልባችን ውስጥ ኢማንን እንዲያድስልን እንድንለምነው አዘውናል!
አዎ ነገሩ ጠንከር ብለን በእውነተኛ ቀልብ ችክ ብለን ዱአ ማድረግ ያስፈልገዋል!
ለነገሩ የሁለት አገር የደስታ መሰረት የሆነው ኢማን ችክ ተብሎ ያልተለመነውን ምን ይለመናል?
በዚህ አለም ካሉ በጣም ውድ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ ውዱ እና የውዱች ቁንጮ የሆነው ኢማናችን ስለሆነ
ኢማናችንን ከሚያዳክሞት ነገር መጠንቀቅ ያስፈልጋል ።

ኢማንን ያጣ በጣም ትልቅ ነገርን አጥቷል በርግጥም ዱኒያ አኼራውን ኸስሯል።

🛑👉እውነተኛ ሂወትንም እየኖረ አይደለም
መብላት፣መጠጣት፣መቆም እና መተኛት…
ይህ የሀቂቃ ትክክለኛ ሂወት አይደለም ይህማ ሂይወት ከሆነ ከሀያው፣ከበጉ በጥቅሉ ከእንሰሳ በምን እንለያለን? እነሱም እንደኛው ይበላሉ፣የጠጣሉ ወ… ወ… ታዲያ ምንድነው ልዩነታችን?
ትክክለኛ ሂወት ማለት አር-ረህማንን መታዘዝ መልእክተኛውን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) መከተል ነው።

🛑👉 አላህ እንዲህ ይላል"እናንተ ያመናችሁ ሆይ (መልእክተኛው) ህያው ወደሚያደርጋችሁ (እምነት) በጠራችሁ ግዜ ለአላህ እና ለመልእክተኛው ታዘዙ" (አንፋል 24)
ሰለፎች ኢማናቸውን ለማደስ ትልቅ ትግል ያደርጉ ነበር !
ኡመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ አንሁ) ለባልደረቦቹ "ኑ (ተሰብሰቡ) ኢማናችንን እንጨምር" ይል ነበር (ኢብኑ አቢ ሸይባ 11/26)

🛑👉ከላይ ያለውን የኡመርን ንግግር ሸይኽ አብዱረዛቅ አል-በድር እንዲህ ሲሉ ያብራሩታል "ጀነትን፣እሳትን፣የአላህን ቃልኪዳን እና ዛቻውን በማውሳት ኢማናችን እስኪጨምር ድረስ እንቀመጥ"
ምንጭ ( ተጅዲዱል ኢማን ገፅ 4)


🛑👉አብዱላህ ኢብኑ መስኡድ (ረዲየላሁ አንሁ) "አላህ ሆይ ኢማንን፣(የዲን) ግንዛቤን እና የቂንን ጨምረኝ) ይሉ ነበር።(አስ-ሱናህ 1/368)

🛑👉አቡ ደርዳእ (ረዲየላሁ አንሁ) "(ኢማኑ) እየጨመረ እና እየቀነሰ መሆኑን እንድሁም የሰይጣን ተንኮል በምን በኩል እንደሚመጣው (አንድ ሰው) ማወቁ ከግንዛቤ(ፊቅህ) ጭምርት ነው" ይላሉ (ኢባና 2/ 849)

🛑👉አንድ ሰው ኢማኑ መቀነሱን እና መጨመሩን ማወቁ በራሱ የሚወደስ ነገር ነው
ብዙ ሰዎች ኢማናቸው ሳያስተውሉት ቀንሱ ቀንሱ ከነአካቲው እስከሚያልቅም አያውቁትም አላህ ይጠብቀን እና ገፍላ ማለት እሄ ነው።

🛑👉((እኛ እርስ በእርሳችን ስንገናኝ ኢማናችን እንዲጨምር ልክ እንደ ሱሀቦች ተዋውሰን እናውቃለን? የኢማናችን ጉዳይ አስጨንቆን አላህ ኢማናችንን እንዲያድስለን እና እንዲጨምርልንስ ዱአ እየደረግን ነውን? እያንዳንዳችን ነፍሳችንን እንጠይቅ ነፍሳችንን እንተሳሰብ))

🛑👉ኡመይር ኢብኑ ሁበይብ "ኢማን ይጨምራል ይቀንሳል" ይሉ ነበር የሚጨምረው እና የሚቀንሰው እንዴት ነው ተባላቸው? "አላህን ባወሳን፣ባመሰገን እና ባጠራን ግዜ(ይህ ኢማንን ይጨምራል) (ከአላህ)በተዘናጋን እና በረሳን ግዜ (ኢማን ይቀንሳል" በማለት መለሱ (አጥ-ጦበቃት 4/381)

🛑👉ኢማሙል አውዘኢይ (ረሂመሁላህ) ኢማን ይጨምራልን ተብለው ተጠየቁ እርሰዎም "አዎ ተራራ እስከሚያክል (ይጨምራል)" አሉ ኢማን ይቀንሳልን? ተብለው ሲጠየቁ "አዎ ከእርሱ ምንም እስከማይቀር ይቀንሳል" በማለት መለሱ (አስ–ሱናህ 5/959)
ከሱሀቦች ከታብእዮች እነሱንም በመልካም ከተከተሉ ታላላቅ አኢማዎች በኢማን ዙሪያ የተዘገበ እጅግ በጣም ብዙ ነው።

🛑👉የኢስላም ታላላቅ አኢማዎችን ከድሩ እስከ ዘንድሩ ያሉትን ታሪካቸውን ብንከታተል ኢማናቸውን ለማደስ የሚያደርጉትን ጥረት እና ክትትልን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ኢማንን ማደስ እንዲህ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን ታወቅን ከውስጣችን ኢማንን የሚጨምሩ እና የሚቀንሱ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም!
በቀጣይ ፅሁፌ ኢማንን የሚጨምሩ እና የሚቀንሱ ነገሮችን ኢንሻ አላህ አቀርብላችኋለሁ


ይቀጥላል

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድዘይን (ህዳር 28/2010)

​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
http://www.tgoop.com/IbnuMuhammedzeyn
2025/08/27 19:25:33
Back to Top
HTML Embed Code: