Telegram Web
💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
           አሜን

✍️ "በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥
ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን"
📖ቆላስይስ 1፥10-11

           ቀናችንን በጸሎት እንጀምር

      ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥
ሕማማት ሰሞን ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ ቋንቋዎች ትርጉም
       ✥••┈┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈┈••✥

❖ በግብረ ሕማማት (በሕማማት ሰሞን) ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡና የምንጠቀምባቸዉ

➊ የዕብራይስጥ(hebrew)
➋ የቅብጥ (ግብጽ) (coptic)
➌ የግሪክ (ጽርዕ) (greek) ቃላት ይገኛሉ፡፡

📌 የእነዚህ ቃላት ትርጉም በጥቂቱ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡

#ኪርያላይሶን

❖ ቃሉ የግሪክ(ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነዉ፡፡
❖ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ / እመቤታችን" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ / ጌታ ሆይ / አቤቱ" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኤሌይሶን" ማለት ደግሞ "ማረን / ይቅር በለን" ማለት ነዉ፤ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፤ ትርጉሙም "አቤቱ ማረን" ማለት ነዉ፡፡
❖ "ኪራላይሶን" የምንለዉ በተለምዶ ነዉ፤ ይኸዉም "ኪርዬ" ከሚለዉ "ዬ" ኤሌይሶን" ከሚለዉ ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸዉ በአማርኛ "ያ"ን ፈጥረዉ ነዉ፡፡

#ናይናን

❖ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን "መሐረነ / ማረን" ማለት ነዉ፡፡

# አብኖዲ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "አብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ ፡፡

#ታኦስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ጌታ / አምላክ" ማለት ነዉ፡፡ "ታኦስ ናይናን" ሲልም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ማስያስ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "መሲሕ" ማለት ነዉ።
❖ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነዉ፡፡

#ትስቡጣ

❖ "ዴስፓታ" ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን "ደግ ገዢ" ማለት ነዉ፡፡

#ሙዳሱጣ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "ነበልባላዊ" ማለት ነዉ፡፡

#መዓግያ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "እሳታዊ" ማለት ነዉ፡፡

#አንቲፋሲልያሱ

❖ ቃሉ "በመንግስትከ / በመንግስትህ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚኦ በዉስጠ መንግስትከ / አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በዉስጠ መንግስትከ / ቅዱስ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

❖ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ እግዚአ ኲሉ መንግስትከ / የሁሉ የላይ የሆንክ ሆይ በመንግስትህ አስበን" ማለት ነዉ፡፡

#ኤልማስ

❖ የግሪክ ቃል ሲሆን "አምላኪየ / አምላኬ" ማለት ነዉ፡፡

#አህያ ሸራህያ

❖ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን "ያለና የሚኖር" ማለት ነዉ፡፡

❖ እነዚህ ከላይ ያሉና ሌሎች ቃላት ከሌሎች ቋንቋዎች በቀጥታ የተወሰዱ ናቸዉ፡፡

መልካም የሰሙነ ሕማማት ወቅት ይሁንልን

ስብሐት ለከ፤
ሰጊድ ለአቡከ፤
ዕበይ ለመንፈስከ፤
ወምህረተ ፈኑ ለሕዝብከ፤
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡፡    

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽዐነ በፍሥሐ ወበሰላም

ሙሉዉን ያነበበ ብቻ አሜን ይበል እንዲሁ #ሼር ያድርግ

✍️"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል"
📖ምሳ 1፥33

✍️ " #ወአንቢበክሙ አንትሙ #ለዘኢያንበበ አይድኡ
#እናንተ_አንብባችሁ_ላላነበበው_ንገሩ"

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️

🙏 ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ፤ እኔም ለእናንተ ከአዘጋጀው በኃዋላ በድካሜ ብዛት ሳይገባኝና ሳይገባኝ በምጽፈው ድርሳንወ ገድላት መጽሐፍት ላይ የቃላት (የፊደል) ሕፀፅ ቢገኝ በጎደለው እየሞላችሁ በጠመመው እያቃናችሁ አንብቡ በረከት ተካፈሉ እላለሁ ከምንም ጊዜ በላይ ለሀገራችንና ለዓለም ሰላም እንዲሁም ለደካማው ወንድማችሁ እንድበረታ (የተጣልሁ) እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ

"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

               ወስብሐት ለእግዚአብሔር
                              ይቆየን 

አዘጋጅ:- ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘዉብ
"…እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ አመ ከመ ዮም፤ ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም…

"…በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ማቴ 21፥ 18-19

"…የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። ዮሐ 2፥ 13-16
Forwarded from ሰናይት ግዛቸው
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል_7ቱ_የመስቀሉ_ቃላት_7ቱ_ተዐምራት_5ቱ_ችንካሮች_6ቱ_ሰሙነ_ሕማማት_ቀናቶች___5ቱ_ኃዘናት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል
1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_የመስቀሉ_ቃላት
1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሰባቱ_ተዐምራት
ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት
1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_የተቸነከረባቸው_አምስቱ_ችንካሮች
1. #ሳዶር ፣ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. #አላዶር ፣ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. #ዳናት ፣ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. #አዴራ ፤ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. #ሮዳስ ፣ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#የሰሙነ_ሕማማት_ትርጓሜ
#ሰኞ
ይህ ዕለት አንጽሆተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን ይባላል
ይኸውም የሆነበት ምክንያት ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ ሰጠ።
ጌታችን ፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሆተ ቤተመቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ
ሥልጣኑ በጻሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል ነው፡፡
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ረቡዕ
ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት
ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን
ስለሆነ ነው፡፡
መልካም መዓዛ ያለው ቀን ይባላል
የእንባ ቀንም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል
ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል
የምስጢር ቀን ይባላል
የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
የነፃነት ሐሙስ ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ዓርብ
ስቅለት ዓርብ ይባላል
መልካሙ ዓርብ (GOOD FRIDAY) ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#ቅዳሜ
ቅዳምሥዑር
ለምለም ቅዳሜ ይባላል
ቅዱስ ቅዳሜም ይባላል
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
#አምስቱ_ኃዘናት
ልመናዋ ክብሯዋ በእኛ ለዘለዓለም በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች ክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተዓምር ይህ ነው።
በዕለታት ባንድ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኃዘኖች ማናቸው ኃዘን ይበልጣል አላት፡፡ እመቤታችንም ፈጣሪዬ ጌታዬ ሆይ በእኔ ዘንድ እኒህ አምስቱ ኃዘኖች ይበልጣሉ አለችው፤
፩• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው። ሉቃ 2፥34-35
፪• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው። ሉቃ
2፥41-48
፫• ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19፥1
፬• አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው። ዮሐ 19፥17-22
፭• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው። ዮሐ 19፥38-42
⛪️ ጌታችንም እናቱን ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ያገኙሽን እኒህን ኃዘኖችና መከራዎች በሰላመ ገብርኤልና አቡነ ዘበሰማያትን እየደገመ ያሰበውን ኃጢአቱን እኔ አስተሰርይለታለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ አላት፡፡ እናቴ ሆይ ከሞቱ አስቀድሞ በሦስተኛው ቀን ካንቺ ጋር መጥቼ እገለጽለታለሁ፡፡ ይህን ሲናገር ቅዱስ ደቅስዮስ ሰምቶ ምእመናን ያነቧት ዘንድ በእመቤታችን ተዓምር መጽሐፍ ውስጥ ጻፈው፡፡
⛪️ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት በእኛ በልጆቿ ለዘለዓም በእውነት ይደርብን።
__
🌻ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤
🌻ድንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤
🌻ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት
የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ።
🌻ድንግል ሆይ ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች ዕድፍን የምታውቂ አይደለሽም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ።
🌻ድንግል ሆይ የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለሽም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ።
(ሊቁ አባ ሕርያቆስ)
#ምንጭ፦ ታምረ ማርያም፣ ፹፩ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት የሲኦል ደጆች አይችሏትም ቤተክርስቲያን አትታደስም! የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም እንማልዳለን! (መጽሐፈ ምስጢር)
⛪️የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለአባ ይስሀቅ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን፤ አሜን!!!
•••✞✞✞•••✞✞✞•••✞✞✞•••
ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም ግለጽልን። አሜን አሜን አሜን!!!
ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ ምዕዳን

እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡

ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡

የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡

ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡ 

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)


   
ሰሙነ ሕማማት
ማክሰኞ
የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ልዩ የምሴተ ሐሙስ መርሐ ግብር

ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ? ለዚህች ዕለት ያደረሰን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን!

በቤተክርስቲያናችን የፊታችን ሳምንት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት "ሰሙነ ሕማማት" እንደሆነ ይታወቃል። ይህንን በማስመልከት ግቢ ጉባኤያችን በሐሙስ ዕለት፤ "በምሴተ ሐሙስ" ዕለቱን የሚዘክር ልዩ ጉባኤ አዘጋጅታ ጠርታናለች።
📌እጽበተ እግር
📌ትምህርተ ወንጌል
📌ሥነ ጽሑፍ
📌የበገና ዝማሬ
📌ጉልባን
                       
🗓ሐሙስ ሚያዝያ 23፣ 2016ዓ.ም
           🕰    8:30 - 10:30
     
⛪️ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ

.           የኮሜርስ ግቢ ጉባኤ
          📲Join & Share👥
                   👇👇👇
           @commercegebi
           @commercegebi
ረቡዕ
🖍ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

🖍የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

🖍የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

ዕለተ ረቡዕ

ምክረ አይሁድ
በዚህ ዕለት ፫ ዋና ዋና ነገሮች ተፈጽመዋል

1. ምክረ አይሁድ
    አይሁድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመስቀል ምክክር ያደረጉበትና እንዲሰቀል መወሰናቸው ነው ።

2.የእንባ ቀን ማርያም የተባለች ሴት ጌታን ሽቱ መቀባቷ ነው ። ይህች ሴት በወንጌል እንደተጻፈው ዕድሜዋን (ሕይወቷን) በሙሉ በዝሙት ኃጢአት ያሳለፈች ናት ።
ከዕለታት አንድ ቀን እራሷን ስትመለከት መልኳን ተመልክታ ተደነቀች ግን ፈራሽ በስባሽ መሆኗን አስታውሳ ዕድሜዋ አልቆ በጌታ ፊት ለፍርድ ከመቅረቧ በፊት ንስሓ ለመግባት ወሰነች ።በዚህ ዕለት ጌታችን በለምጻሙ ስምዖን ቤት እያለ በኃጢያት የሰበሰበችውን 300 ዲናር ውድ ሽቱ ገዝታ ጌታ ወዳለበት መጥታ የሽቱውን ብልቃጥ ሰብራ በጌታ ራስ ላይ አፍስሳ እግሮቹንም በእንባዋ እያራሰች በጸጉሯም እያበሰች ስለ ኃጢአቷ ይቅርታ በጌታ እግር ሥር ተደፍታ አልቅሳለች ።

3. ከአሥራ ሁለቱም አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ። ሲሰሙም ደስ አላቸው ብርም ይሰጡት ዘንድ ተስፋ ሰጡት።
በሚመች ጊዜም እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈልግ ነበር።” ማር 14፥10-11)

           
               ጸሎተ ሐሙስ
በዚህ ዕለት 6 ዋና ዋና ነገሮች የተፈጸሙ ሲሆን

1.ጸሎተ ሐሙስ ፡- ጌታችን ሕብስቱን በባረከ ጊዜ ቅዳሴ እግዚእ ስለጸለየ ፣ በተጨማሪ በዮሐ ምዕ.17 ላይ ያለውን ረጅም ጸሎት ስለጸለየ እና በጌቴሴማኒ በዚህ ዕለት ስለጸለየ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡

2.የትእዛዝ ሐሙስ፡- የደቀመዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ ጌታችን ‹‹እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› ብሎ ስላዘዘ ዮሐ 13፡4-5 እንደገና በጌቴሴማኒ 3ቱን የምሥጢር ሐዋርያት ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ›› ብሎ ስላዘዘ ማቴ 26፡41 በተጨማሪ ሥርዓተ ቁርባንን ከሠራ በኋላ ‹‹የተቀበልኩትን መከራ 13ቱን ሕማማተ መስቀል ለመታሰቢያ አድርጉ›› ብሎ ስላዘዘ የትእዛዝ ሐሙስ ይባላል፡፡ ሉቃ 20፡22

3.የነፃነት ሐሙስ፡- ጌታችን ሐዋርያትን ‹‹ከእንግዲህ ባሮች አይደላችሁም ወዳጆች ግን ብያችኋለው›› ብሎ የተናገረውን ለማስታወስ የነፃነት ሐሙስ ይባላል ዮሐ 15÷15

4.ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር ስላጠበ ዮሐ 13፡4

5.አረንጓዴ ሐሙስ ይባላል ጌታችን በአትክልት ቦታ /ጌቴሴማኒ/ ስለጸለየ

6.የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡- መስዋዕተ ብሉይን ሽሮ መስዋዕተ ሐዲስን ስለሠራ ሉቃ 20፡22

ከጸሎተ ሐሙስ በቀር በሰሞነ ሕማማት የጌታን መከራ ሞት የሚያስታውሱ ምንባባት ይነበባሉ እንጂ ሥርዓተ ቅዳሴ አይፈጸምም ይኸውም በሌሎች ዕለታት ውስጥ ጌታ ራሱ መስዋዕት ሆኖ ዓለምን ያዳነበት መታሰቢያ በመሆኑ ሁለት መስዋዕት አያስፈልግም በማለት ሲሆን በጸሎተ ሐሙስ ግን የሚቀደሰው የኦሪቱ መስዋዕት ተሽሮ ለሐዲስ ኪዳን የሚሆን ሥርዓተ ቁርባን የተደነገገበት በመሆኑ ነው፡፡
Forwarded from Bketa @¥
✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞

  በነግሕ ጊዜ የሚነበብ ተዓምረ ማርያም

# አምስቱ_የእመቤታችን ኃዘናት፦

1• ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:34-35

2• ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው፡ ሉቃ 2:41-48

3 • ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:1

4 • አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው፡ ዮሐ 19:17-22

5• አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱህ ባሰብኩ ጊዜ ነው፡ ዮሐ 19:38-42
              ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞ ✞
መጋቢት 27 የአምላካችን የክርስቶስ ነገረ ስቅለት
  ✥•••••••••••●◉ ✞ ◉●•••••••••••✥

❖ የነገሥታት ንጉሥ የሕይወት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስን የአይሁድ ጭፍሮች የእሾኽ አክሊል ጐንጒነው በራሱ ላይ ደፍተውለታል፤ የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ኦሪት ዘፍጥረት ላይ አዳምን አስቀድሞ

“ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች” ብሎት ነበርና ያነን መርገም ደምስሶለት ለአዳም ክሷል፡፡
📖ዘፍ 3፥18

❖ ዳግመኛም አዳምና ሔዋን ምክረ ከይሲን ሰምተው የድል ነሺዎች አክሊል ተለይቷቸው ነበርና ያነን ሰማያዊ አክሊል እንደመለሰልን ለማጠየቅ፡፡

❖ ይኽ ለካሳ አምላካችን ስለፈጸመው የድኅነት ምስጢር ቅዱሳት ደናግል በጥልቀት እንዲኽ አብራርተዋል

“አስተቀጸልዎ ከመዝ ለርእሰ ሕይወት አክሊለ ሦክ …”
👉የሕይወት መገኛ ርሱን የእሾኽ አክሊልን አቀዳጁት፤ መላእክትን የብርሃን ራስ ቁር የሚያቀዳጃቸው የነገሥታት ገዢ የሚኾን ርሱን የሾኽ አክሊል አቀዳጁት፤ በሾኽ አክሊልም ከራሱ ክፍል ያቆሰሉት ሺሕ ናቸው፤ ከራሱም ቊስሎች ደም እንደ ውሃ በዝቶ ፈሰሰ፤ ፊቱም ደምን ለበሰ ሰውነቱም በደም ተጠመቀ፤ የጽዮን ልጆች እናቱ ያቀዳጀችውን አክሊል ተቀዳጅቶ አዩት፤ ተድላ ደስታ የሚያደርግበትና የሙሽርነቱ ቀን ነውና።
📖መኃ 3፥11

❖ … ነገርና ግን የሾኽ አክሊልን በመቀዳጀቱ በምድራችን ላይ የበቀሉትን አሜከላና እሾኽ ርግማንን አጠፋልን።
📖ዘፍ 3፥18

❖ ራሱንም በዘንግ በመመታቱ የታላቁን እባብ ሰባቱን ራሶቹን ዐሥሩን ቀንዶቹን አጠፋልን።
📖ራእ 13፥1

❖ ሊቁ ቅዱስ ኤራቅሊስም ስለፈጸመው ካሳ እንዲኽ አስተምሯል

“እንዘ ይትቄጸል አክሊለ ሦክ አብጠለ ኲነኔሁ ለቀኖተ ሞት ወእንዘ ቅንው ዲበ ዕፀ መስቀል ኢተዐርቀ እምነ መንበሩ…”
👉የእሾኽ አክሊል ደፍቶ የሞትን ሥልጣን ፍርድ አጠፋ፤ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ሳለ ከዙፋኑ አልተለየም፤ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ አልተለየም፤ በምድር አይሁድ እንደ በደለኛ ሲዘብቱበት፤ መላእክት በሰማይ የከበረ ጌትነቱን ይናገሩ ነበር።
📚ቅዱስ ኤራቅሊስ

❖ እጆቹና እግሮቹ ስለመቸንከሩ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት ዐድሮ በመዝሙር ላይ

“ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዙኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤ ዐጥንቶቼ ኹሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም” በማለት ውሻ ከአፉ ያወጣውን መልሶ ለምግብነት እንዲፈልገው፤ አይሁድም ኦሪትን እለፊ ካላት በኋላ ሲሠሯት በመገኘታቸው በውሻ መስሎ ትንቢት ያናገረባቸው ሲኾን፤ ይኽም ሊፈጸም ንጹሓት እጆቹና እግሮቹ በምስማር ከዕፀ መስቀሉ ጋር አያይዘው ቸንክረውታል፡፡ 
📖መዝ 21፥16

❖ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስን በማምራቷ በድላ ነበርና ለርሷ ካሳ ሊኾን ንጹሓን እግሮቹ ሲቸነከሩ፤ በእጆቿም በለስን በመቊረጧ ንጹሐ ባሕርይ አምላክ እጆቹ በችንካር ተቸንክረዋል፡፡

❖ በመቸንከሩም ለ5ሺሕ 500 ዘመን በሰው ልጆች ላይ የሠለጠነ የሞት ችንካር ጠፍቶልናል፤ ምስጋና ይግባውና ኢየሱስ ክርስቶስ በመቸንከሩ ስለፈጸመው ካሳ ደናግል ሲተነትኑ

“ወበቅንዋቲሁ ሠበረ ለነ ቀኖተ ሞት …”
👉በመቸንከሩም የሞት ችንካርን አጠፋልን፤ ሔዋን በእግሮቿ ወደ ዕፀ በለስ ስለ ተመላለሰች እጆቹንና እግሮቹን በመቸንከር ከፍሏልና፤ በእጆቿም የበለስን ፍሬ ስለቈረጠች ፈንታ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል በሥጋው ከመስቀል ዕንጨት ጋራ ተቸነከረ በማለት አስተምረዋል፡፡

❖ መተርጒማን ሊቃውንት እንዳመሰጠሩት ጌታ በዕንጨት መስቀል ላይ መሰቀሉ ስለምን ነው ቢሉ፤ እሾኽ በሾኽ ይነቀሳል ነገር በነገር ይወቀሳል እንዲሉ በዕፀ በለስ ምክንያት የገባውን ኀጢአት በዕፅ ለማውጣት በዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሏል፡፡

❖ ጌታችን ከምድር ከፍ ከፍ ብሎ ስለምን ተሰቀለ ቢሉ

 “እምከመ ተለዐልኩ እምድር እስሕብ ኲሎ ኀቤየ”
👉ከምድር ከፍ ከፍ ባልኊ ጊዜ ኹሉን እስባለኊ ብሎ ነበርና ይኽነን ሊፈጽም ነው።
📖ዮሐ 12፥32

❖ ዳግመኛም ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ መሰቀሉ “ኅሩይ ማእከለ እግዚአብሔር ወሰብእ” እንዲል አምላክ ወሰብእ ኾኖ እንዳስታረቀን ለማጠየቅ፡፡

❖ በመጨረሻም ምድርን በኪደተ እግሩ እየተመላለሰ እንደ ቀደሳት፤ ዐየራትን ደግሞ ሥብ እያጤሱ አስተራኲሰውት ነበርና አየራትን ለመቀደስ ነው፡፡

❖ ንጹሐ ባሕርይ ጌታችንን አይሁድ መስቀሉን አሸክመው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ከወሰዱት በኋላ ኹለት ወንበዴዎችን በቀኝና በግራ አድርገው ጌታችንን በመኻከል ሰቅለውታል።
📖ማቴ 27፥38፤
📖ማር 15፥27፤
📖ሉቃ 22፥23፤
📖ዮሐ 19፥18

❖ ክፉዎች አይሁድ ይኽነን ያደረጉበት ምክንያት በክፋት ነው፤ ይኸውም በቀኝ የሚመጡ ሰዎች በቀኝ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት፤ በግራ የሚመጡ ሰዎች በግራ የተሰቀለውን ወንበዴ አይተው “ይኽ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ወንበዴ ነው” ይሏቸዋል፤ ከዚያም ጌታን “ይኽስ ምንድ ነው” ብለው ሲጠይቁ “ይኽስ ከርሱ ልዩ ነውን አንድ ነው እንጂ” ብለው ሰዎችን ለማሳሳት ያደረጉት ነው፤ ዳግመኛም አነገሥንኽ ብለውታልና ቀኛዝማች ግራዝማች ሾምንልኽ ለማለት ለመዘበት።

“ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና” የሚለው ትንቢቱን ሊፈጽም ሲኾን ምሥጢሩ ግን እኛን ከጻድቃን ጋራ አንድ ያደርገን ዘንድ ርሱ ከበደለኞች ጋር ተቈጥሯል፤ ሌላውም በዕለተ ምጽአት እኛን ኃጥኣንን በግራ ጻድቃንን በቀኝ ታቆማለኽ ሲያሰኛቸው ነበር።
📖ኢሳ 53፥12
📖ማቴ 25፥33፤
📖ራእ 1፥7

❖ በኹለት ወንበዴዎች መኻከል ከሰቀሉት በኋላ ጲላጦስም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ጽሕፈት በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው።
📖ዮሐ 19፥18-22

❖ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “ርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለኽ አትጻፍ” ሲሉት፤ ጲላጦስም “የጻፍኹትን ጽፌአለኊ” ብሎ መልሶላቸዋል፤ ይኽነንም በሕማማት ድርሳኑ ላይ ሲተረጒሙት

“ወዝ መጽሐፈ ጌጋይ ዘጸሐፎ ጲላጦስ ወአንበሮ መልዕልተ ርእሱ ይደምስስ ለነ በኲሉ ጊዜ መጽሐፈ ዕዳነ ዘጸሐፉ አጋንንት”

አዘጋጅ ዲ/ን ቡሩክ ይርጋ ዘዉብ
🎚🎚🎚 እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን 🎚🎚🎚

🎚🎚🎚ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰኝ ያድርሳችሁ አሜን 🎚🎚🎚



ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት
#ሥርዓተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘዓርብ_ስቅለት

👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፲፪ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም፤ ርግዘተ ገቦሁ ነአምን፤ ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን፤ ዬ ዬ ዬ፤ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ።

በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ምስባክ
መዝ: ፳፮ ፣ ፲፪
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፤
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ፤
እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በዜማ በኅብረት ይበሉ:-

👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፩ - ፲፬ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል።

👉🏽ማር: ፲፭ : ፩ - ፭ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽእዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

👉🏽ሉቃ: ፳፪ : ፷፮ - ፸፩ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ።

👉🏽ዮሐ: ፲፰ : ፳፰ - ፵ ከተነበበ በኋላ
ወጸቢሆ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን "#መልክዐ_ሕማማት" ያድርሱ።

👉🏽ዐርብ #ጠዋት በ፫ ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) አርዑተ መስቀል ፆረ (፪)፤ ይስቅልዎ ሖረ፤ ዬ ዬ ዬ፤ ከመ ኪያነ ይቤዙ እግዚእ ኮነ ገብረ።

በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ መዝሙር ፴፬ትን ፫ ቦታ ከፍሎ በውርድ ንባብ ይበል። በቀመጠል ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል እየተሰገደ:-

ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ።

ይ.ዲ ምስባክ:- መዝ: ፳፩ : ፲፮
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።

👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፲፭ - ፲፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አኃዝዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ።

👉🏽ማር: ፲፭ : ፮ - ፲፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀበ ሎሙ ኢየሱስሃ ይስቅሉ።

👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፲፫ - ፳፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዓውደ ምኲናን።

👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፩ - ፲፪ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፫ቱ ሰዓት ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዓ_ሕማማት ያድርሱ።

#ዐርብ_በስድስት_ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ተሰቅለ (፫)፤ ወሐመ ቤዛ ኲሉ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ።

በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ያለው ምንባብ ይነበባል።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከገላትያ በውርድ ንባብ ይበል። ከዚያም ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-

ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤
ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብሕ ኲልነ፤
ይእዜኒ ወዘልፈኒ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፳፩ : ፲፮
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ
ወኆለቊ ኲሎ አዕፅምትየ
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:-

👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፳፯ - ፵፭ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ።

👉🏽ማር: ፲፭ : ፲፮ - ፴፫ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምኦን ከመ ይፁር መስቀሉ።

👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፳፯ - ፵፬ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን።

👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፲፫ - ፳፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ፪ኤ ፈያት።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል የሰዓቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ።

#ዐርብ_በዘጠኝ_ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ሶበ ሰቀልዎ(፫) ለእግዚእነ፤ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

በመቀጠል "#ለከ_ሃይል" ይባላል። ከኦሪት ምንባብ እስከ ተአምረ ኢየሱስ ምንባብ ይነበባል። ከዚያም በኃላ ካህኑ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል በዜማ እየተሰገደ:-

ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ።

ዲያቆኑ ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ከ ግብረ ሕማማት በውርድ ንባብ ይበል። በመቀጠልም ሶስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በስዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ፤ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገፃቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ)። አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምጽ በሀዘንና በፍርሃት በለቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ። እንደገናም "አምንስቲቲ"ንና "ተዘከረነ እግዚኦ"ን እያንዳንዱን አንድ አንድ ጊዜ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቁጥሩ ፲፪ እስኪሞላ ድረስ) ይበሉ። ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ (በውርድ ንባብ) እያስገባ ያንብብ።

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-

አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ

ይ.ካ ከሕዝቡ ጋር በቅብብል:-

ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤ ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ፤ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ።
ይ.ሕ በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።

ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፷፰ : ፳፮
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ፤
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።

ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ:-

👉🏽ማቴ: ፳፯ : ፵፮ - ፶ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ።

👉🏽ማር: ፲፭ :፴፬ - ፴፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ።

👉🏽ሉቃ: ፳፫ : ፵፭ - ፵፯ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ።

👉🏽ዮሐ: ፲፱ : ፳፰ - ፴ ከተነበበ በኋላ
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ።

ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ"#ኪርያላይሶን" ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ። ከዚያም በመቀጠል #የሰዓቱን_መልክዐ_ሕማማት ያድርሱ።

#ዐርብ_በአስራ_አንድ_ሰዓት

አቡን
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ(፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሃተ ዘእንበለ ዐቅም፤ ዬ ዬ ዬ፤ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ፤ እንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ።

በዚህ ሰዓት "ለከ ሃይል፣ ኪርያላይሶንና መልክዐ ሕማማት" #የለም
.............
ምንጭ ፦ የአ/አ/ዩ/ሳ/ቴ/ፋ/ ግቢ ጉባኤ
❗️❗️❗️
በማስተዋል የሚነበቡ ስለ ሕማሙ አባቶች ከፃፉልን ፦

"እንዲፈረድበት ራሱን አሳልፎ በሰጠበት ቀን እንዲህ ካደረገ ሊፈርድ ሲመጣ ምን ያደርግ ይሆን? ሊሞት በመጣበት ጊዜ ይኼን ኃይል ካሳየ ለዘለዓለም ሊገዛ በሚመጣ ጊዜ እንዴት ኃይልን ያሳይ ይሆን? "
👉 ቅዱስ አውግስጢኖስ

ጌታችን አይሁድ ሊይዙት በመጡ ጊዜ በነሱ የወታደር ኃይልና ብዛት ሳይሆን በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ስለመስጠቱ ሲያብራራ ሁለት ጊዜ "ማንን ፈለጋቹ" ብሎ ሲጠይቃቸው"የናዝሬቱ ኢየሱስን" ብለው ሲመልሱ "እኔ ነኝ" ብሎ ጌታችን ቃሉን በመስጠቱ በአምላክነቱ ኃይል እንደወደቁና ለእኛም ለአይሁድም በፈቃዱ እንደተያዘላቸው ሲያጠይቅ ነው።

ከሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ
ገጽ 86
ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ ።


📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ዐበጥዎ ለስምዖን ከመ ይፁር መስቀሎ ።


📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ክልኤ ፈያት ።


📜 - ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ቀትር ሶቤሃ ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን ።
"ሮማውያን የሚሰቅሉትን ሰው ምን ያህል ዕርቃኑን እንደሚያዋርዱት አይሁድ በተግባር አይተው ስለሚያውቁ ጌታችን በዚህ በአሰቃቂ አሟሟት እንዲሞትና ‹እውነት እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ ደርሶበት ይሰቀል ነበር?› እያሉ እንደ ማስረጃ በማቅረብ ‹ክርስቶስ አይደለም!› ለማለትና ክርስቲያኖችንም ለበዓል በመጣው ሕዝብ ፊት በጌታ መሰቀል ለማሸማቀቅ ነበር፡፡

እነርሱ ለማሸማቀቅ ብለው እንዲሰቀል ቢያደርጉም እኛ ግን በመሰቀሉ አፍረን አናውቅም፡፡ ‹‹የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ፤ መመካት ቢያስፈልግም ‹‹ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› እያልን እንድናፍር ባዘጋጁት የጌታችን መሰቀል እንመካበታለን፡፡ (ገላ. ፲፮፥፲፬ ፩ቆሮ.፩፥፳፫)"
❮❮ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ - ዮሴፍ ኒቆዲሞስም ጌታችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ገነዙት ❯❯

📜 ወንጌለ ማቴዎስ 27 📜


⁵⁷ በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤
⁵⁸ ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።
⁵⁹ ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፥
⁶⁰ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።
⁶¹ መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።





⁶² በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና፦
⁶³ ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፦ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን።
⁶⁴ እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም፦ ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት።
⁶⁵ ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው።
⁶⁶ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።
2024/05/03 22:20:34
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243