Telegram Web
ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን
ለተወጋዉ ጎንህ
ለበትረ መስቀልህ
ለፈሰሰዉ ደምህ
ቀራንዮ ሞትህ
ጎለጎታ ቤትህ
ኪራላይሶን ማረን ለዛ ህማማትህ።
አባ አባታችን
በጥፊ ስመታህ እጆቼን ይዘሀኝ ልማርህ ብለሀል
ዉሀ አልሠጥም ብዬ በከርቤ ኮምጣጤ ጉንጭህን ሞልተሀል
ጠማኝ አባቴ ስል ይሄ አይጠቅምም ብለህ
የዘላለም ዉሀ ለኔ አዘጋጅተሀል።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን..........
መፃጉ ሆኜ ሳለሁ መዳኔን ሽተሀል
አልጋህን ተሸከም ብለህ ምረሀኛል
ሰንበት አፈረሰ እያልኩ መክሰሴን
ጌታ አረሳሁትም ማራት ይህቺን ነፍሴን።
ጎንህን ወጋሁት በጦሩ ጎርጉሬ
አቤቱ ማዳንህ አይኖቼን አበራህ ትተህ መነወሬን።
የሀጥያቴ መብዛቱን አይተህ ሳትጠየፍ
ፈራሽ ሰዉነቴን አፈር ማንነቴን ተመልክተህ ሳታልፍ
እኔ የከንቱ ከንቱ ፊትህን ተጠይፊ
የማይፈርስ አካልህን ፍቅርህን ጠፍፌ
ማረዉ ብለህ ስትል ሰዉነቴ ቀፎት
ምራቅ ተፋዉብህ ለኔ መምጣትህን እኔነቴ ክዶት።
ኪራላይሶን ማረን
ስለናትህ ማረን................
ሸክማችሁን በኔ ጣሉት ብለህ ስትል
ችግሬን ጥዬብህ
እንቅልፍና እረፍትን ባንተ አገኘዉብህ
ችግሬ አንሶብኝ
መስቀል ማሸከሜን ጌታ አትይብኝ
ከኃላ እንድትፈጥን እየገፈተርኩ
ከፊት ቀስ እንድትል እየገፈተርኩ
መሬት ስትወድቅ እያንቀለቀልኩ
ስትነሳ ደግሞ እያወዛገብኩ
መቼ ይረሳኛል እንዳንከራተትኩህ።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን...............
መዳፍህ ይታየኛል
ጭቃ አበጃጅቶ እኔን የሰራልኝ
ዳብሶ የፈወሰኝ
እኔ የእፉኝት ልጅ
አዴራ አላዶር ሳዳርና ዳናት በሚባል ችንካሮች
መዳፍህን በሳዉ አለምን በያዙ በነዛ ድንቅ እጆች።
እግርህን ቸነከርኩ ምድርና ሰማይ ሊችሉት ያልቻለ
አልፋና ኦሜጋ በመስቀል ላይ ዋለ።

ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@leoyri
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
.. ህልሜን አደራ!
((በውቀቱ ስዩም))
.
ባይመረመሬ ፥ ጥበብ ተሽከርክሮ
ከወርቃማ ብርሃን ፥ ከብርማ ፀዳል
የተሰራ ሸማ ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ስር ፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ ፥ ከህልሞቼ በቀር፤
:
የኔ ውድ እንግዲህ
ህልሜን እግሮችሽ ስር ፥ ከዘረጋሁ ወዲህ
ዝግ ብለሽ እርገጪ ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና ፥ የምትራመጂ።

。。。 የማለዳ ድባብ©
የሆሄያት ህብር 🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ሰሞንኛ!

(በእውቀቱ ስዩም)

ልጅ ሆነን፥ ለመጀመርያ ጊዜ ፕራንክ ሲያደርግ ያየሁት የሰፈራችን ልጅ ሙሉጌታ ይባላል፤ የብረት አለሎ በጨርቅ ጠቅልሎ መንገድ ላይ ያስቀምጣል ፤ ከዚያ፥ ቤተክስያን ስመው ወደ ቤታቸው እሚመመለሱ አረጋዊ  ሲያይ፥

“አባ”

“አቤት”

“ እሷን ኳስ ይምቱልኝ እስቲ”

ሰውየው “ አሁን መታሁ ልዤ! የተባረከ ይሁን ! “ብለው መንገዳቸውን መቀጠል ፋንታ ፤ እንደ ጠቦት ፍየል ወደ ሁዋላ ተንደርድረው፥ ወደ ፊት ተመልሰው ፥ ያንን ጨርቅ ለበስ አለሎ በእግራቸው ይደነብቁታል፤

ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ፥ ዊልቼራቸውን እያሽከረከሩ ሲያልፉ ያየ ያገር ሰው፥
“ አባ! ምን ገጥሞት ነው?” ይላቸዋል፤

“ በራዛ ዘመቻ ጊዜ ሻቢያ የጠመደው ፈንጅ አግኝቶኝ ነው “

ርጉሙ ሙሉጌታ ፕራንክ ያደረጋቸው ሰውየ፥ በበኩላቸው ፥በዚህ አይነት  ህብረተሰቡን ፕራንክ ሲያደርጉት ኖሩ!
........

ይቺን የጻፍኳት፥ ሰሞኑን   በአንድ አለም አቀፍ አውቆ- አበድ እና በሀይሌ ሪዞርት መካከል በተደረገው ውዝግብ ፥ ከሀይሌ ጎን መቆሜን ለማመልከት ነው🙂

ከጥቂት አመታት በፊት ፥ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ሀብታም ድርጅት ስልጠና ብሎ የተወሰኑ የኪነጥበብ ባለሟሎችን መርጦ  ሀይሌ ሪዞርት አምስት ቀናት አስቀመጠን፤ የቅንጦትን ምንነት ያየሁት ያኔ ነው፤  የአልጋውን ምቾት ባሰብኩት ቁጥር እስካሁን ድረስ እንቅልፌ ይመጣል፤   በማደርያችን ውስጥ የሀይሌ ፊርማ ያረፈበት የምቾት እቃ ተቆጥሮ አያልቅም፤

የመታጠቢያ ቤቱን ቁምሳጥን ከፈት ሳደርገው ፥አምስት አይነት ሳሙና በበልቃት ተደርድሮ አገኛለሁ፤   ለብብት ብቻ የተለየ ሳሙና ተዘጋጅቷል ፤ እኔ የሰራ አከላቴን ለመታጠብ አንዱን ብልቃት ብቻ እጠቀምና የቀረውን ለክፉ ቀን  በቦርሳየ ውስጥ እከዝነዋለሁ፤

 
የስልጠና ጊዜ አልቆ ተሰናብተን ከሆቴሉ  ስንወጣ፤ ዘበኛው፤ ቦርሳየን ፈተሸው፤

  ከሰላሳ ብልቃት ሳሙና እና ከአምስት ፎጣ በቀር ምንም አላገኘብኝም፤ 

ዘበኛው ከማሰናበቱ በፊት ያለኝን አልረሳውም፤

“ ብርድ ልብሱን  ለምን ተውከው? ”
@sirak6
https://www.tgoop.com/gGetem
አዳም ወደ ማምሻ!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።
ባለ ክንድ ብንሆን ባለ ግዙፍ ጡንቻ
ምን እህል ብንሰፍር ባንድ ሺህ ስልቻ
ጢያራ ብናበጅ ፥ በአየር ብንከንፍ
ልንዘምን ብንተጋ ፥ ለማወቅ ባንሰንፍ
ከባህር ብንሰምጥ ፥ ከዓሳ ብንላፋ
በአራት 'ግር ቆርቆሮ.. .
ግንባር ተቀምጠን ፥ ደረት ብንነፋ
።።።።
ገላችን ቢፋፋ ወዙ ቢጭረቀረቅ
ሊዋብ ገፅታችን ፥ በጌጥ ቢጥለቀለቅ
ህንጣ ብንደራርብ አንዱን በአንዱ ላይ
ስሌት ብንቀምር ፥ የታችና የላይ
የእንጀራቸን ዳሩ.. .
ሌማት ጠርዙን ጥሶ ፥ ቁልቁል ቢንጠለጠል
ገብሴን ችግር ያለ...
የጠኔ ሙቀጫ ፥ ጀርባችን ባይንጋለል
ማድጋቸን ሞልቶ ፥ ማሰሮው ባይጓደል
ምን ቅጥር ብንለይ፥ በግንብ ተከልለን
በርምጃቸን መሀል..
እግር ብናነሳ ፥ አፈር ተጠይፈን
።።።
ደርሰን ብንፎክር፥ በአጀብ ተይዘን
ጨረቃን ብንገዛ ፥ ሕዋ ላይ ተጉዘን
ሩቅ ብንመጥቅ
ብንከንፍ ብን'ደረደር
ጋደል ያለን 'ለታ
አልጋችን ምድር ናት ፥ አንሶላችን አፈር።
@gGetem
www.tgoop.com/gGetem
የእውነት ትንሳኤ 🚩
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ©

የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
አዘጋጅ እና ማጀቢያ ሙዚቃ፦ሔመን👧
-ከአዲስ አቀራረብ ጋር
>>በየቀኑ አዳዲስ ግጥም ይደርሳቹ ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@gGetem
>>Comment  @leoyri
💆"ለእውነት እንቁም"
አዳም ወደ ማምሻው....👨
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ ቤርሳቤህ ሀብተ ወልድ(ቤሪሲ)👧
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#የሳምንቱ ገፅ🕤
#ከድንቅ አቀራረብ ጋር....😘😢
👧እንደ ፀሐይ🌞
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ
ሙዚክ፦ማህደር እንዳለ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

👉 #የመድረክ ስራ
#LIVE ...
@gGetem
@gGetem
@sirak6

👉በመድረክ ላይ እንደቀረበ_
ረስቼሻለው!!!
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#ለጁማችን_
የሳምንቱ ገፅ🕤
አሁን መጉዳቷ ነው
ልቧ ብላል ውልቅ!
እኔን ልታሳቅቅ...
ካይን የራቀ በሚል
የሰነፎች ብሂል…
'ርቆ  ለመዘንጋት
ልፊ ብሎ ፈጥሯት
መሄድ መኮብሏ ...
ጓዟን ማንጠልጠሏ
መራቋ ከቀዬው...
መውጣቷ ከመንደር
ልቤ ቤቷ መሆኑ
ካልገባት በስተቀር
እንዴት ትሄዳለች ?
ሸሽቶ ድል ለመንሳት
ይልቅ ለልቤ ቤት…
ኪራይዋን መክፈሌን
ሰዎች በነገሯት !!
===
(ሚካኤል . አ)
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
ይናፍቀኝ ነበር
(ገጣሚና ሰአሊ ገብረክርስቶስ ደስታ)
...

ዞሮ ዞሮ ከቤት
ይላል የኛ ተረት ::

አቧራው ፀሃዩ ይናፍቀኝ ነበር፤
አፈሩ ጠጠሩ ይናፍቀኝ ነበር::

የመንደር ጭስ ማታ…….
ይናፍቀኝ ነበር የሳር ቤት ጥቀርሻው
መደቡ ምሰሶው፤
ማገሩ ግድግዳው፤ አጥሩና ጥሻው::

የፈራረሰ ካብ………
ቀጭን ጠባብ መንገድ በመንደር የሚሮጥ፤

ቅጠል የሸፈነው፡
ሳር ያለባበሰው፤
እነዚህ እነዚህ ይናፍቁኝ ነበር፤

የተቆላ ቡና ፤
የሚወቀጥ ቡና፤
የጎረቤት ቡና አቦል ሁለተኛ፤
የተረጨ ቆሎ የሚያርቅ መጋኛ፤
የሚጨሰው ዕጣን………

እንጀራ በመሶብ ወጥ የፈሰሰበት
ያገልግል እንጀራ፤ የሚቧጠጥ ፍትፍት፤
የክክ ወጥ የሽሮ፤
የስጋ የዶሮ፡፡

ይናፍቀኝ ነበር ቅራሪ ጉሽ ጠላ፤
ይናፍቀኝ ነበር ፊልተር ዞማ ኮላ፡፡

ያገራችን ድግስ……..
ከበሮው ጭፈራው፤
ዝላዩ እስክስታው፤ ስካሩ ሁካታው፡፡

ትርክምክሙ ነገር ግፍያው ትንቅንቁ፤
ኳኳታው እርግጫው ዘፈን ድብልቅልቁ፡፡

“አሸወይና ወይና“
“እስቲ እንደ ጎጃሞች“
“አሲዮ ቤሌማ… ኦሆሆ አሀሀ…"
የቄስ ትምህርት ቤት
የህፃናቱ ድምፅ፤

“ሀ...ሁ…ሂ…ሃ…“ ዜማ ነበር የናፈቀኝ
የጽጌ ጭፈራ ነበር የናፈቀኝ፡፡

ከበሮ ፅናፅል፤
ሆሳዕና ጥምቀት፤
ፋሲካ ገና ሁዳዴና ስግደት፤
ቡሄ ሆያ ሆዬ፤
የእስላሞች አረፋ የኦሮሞች ሸጎዬ፤
የቁልቢ ገብርዔል፤
ልደታ፤
ፍልሰታ፡፡

ዕንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ፤
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡

ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት፤
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡

ሌላም ብዙ ነበር…
ሌላም ….ደግሞ ሌላ…..፡፡

ያገሬ ሰው ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ጠይም ቆዳ ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ቀይ ዳማ ነበር ጥቁር ቆዳ ነበር፤
ቁርንጫጭ ከርዳዳ፤ ዞማ ጠጉር ነበር፤

ያገራችን ቋንቋ…
ያገሬ ሙዚቃ ያገራችን ዜማ፤
ጥበብ እጀ ጠባብ ያገራችን ሸማ፤
ነበረ ናፍቆቴ ለሁሉም…
ለሁሉ፡፡

ለሸዋ፤ ለወሎ፤ ለትግሬ፤ በጌ ምድር፤
ለጎጃም ወለጋ፤ አሩሲ ኢሉባቡር፤
ኤርትራ ገሙጎፋ፤
ሲዳሞና ከፋ፡፡
ለሁሉም ለሁሉ ነበረ ናፍቆቴ፤

አለብኝ ትዝታ
ዘመዶቼ ሳሙኝ፤
ጓደኞቼም ጋብዙኝ፤
ሊስትሮ ጨብጠኝ::

ባለጋሪ ንዳ መንደሩን አሳየኝ፤
ያገሬ ልጅ ቆንጆ “ቤት ለእንግዳ በዪኝ“፡፡

አለብኝ ትዝታ…..
አዲስ አበባ ላይ ነበረ ናፍቆቴ
መናገሻ ነበር፤ እንጦጦ ነበረ፤
ኤረር ጋራ ነበር፤ ዝቋላ ነበረ፤
ጃን ሜዳ ነበረ፤ ኮተቤ ነበረ፤
ገፈርሳ ነበረ፤ ጉለሌ ነበረ፤

አዲሱ ከተማ…
“መርካቶ ዲጂኖ ችምችም ያለው መንደር“
ከተማው እንብርት ደጃች ውቤ ሰፈር
የቸርችል ጎዳና፤
የባቡሩ ጣቢያ፤
ቢሾፍቱ ነበረ፤ ናዝሬት፤ ሞጆ አዋሽ::
ድሬዳዋ ነበር፤
ዓለምማያ ነበር::

ሐረርጌ ነበረ የተወለድኩበት
እናትና አባቴን ጥዬ የሄድኩበት::
የሚካዔል ጓሮ…
ሐረርጌ ነበረ፡፡
ዞሮ ዞሮ ከቤት…
አገሬ ነበረ እኔን የናፈቀኝ::
ኢትዮጵያ ነበረች♥️
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
ተአምር
    ተአምር
       ተአምር


ቅሎች ተወርውረው ድንጋይን ቢሰብሩ
አዕዋፋት ተስበው እባቦች ቢበሩ
ዶሮዎች አርግዘው ሰው እንቁላል ቢጥል
ካህያ አናትላየሰ ሁለት ቀንድ ቢበቅል
ጋሪው ቀድሞ ቢጓዝ ከፈረሱ በፊት
ውሀ ሽቅብ ፈሶ ቢጠለቅ በወንፊት
ቀፎ ሙሉ ጤፍን ችለን ብንቆጥር
ከምላሳችን ላይ ፀጉር ብናበቅል
አይገርምም አይደንቅም አናስበው ከቶ
ከዚህ በላይ ተአምር ከደጃችን ሞልቶ።



👉የ1000 ዋስ
@sirak6
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👂ነጋሪት በጆሮ👦👂
#የጆሲ_ደብዳቤ_®
#ቀን_06_06_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
@yosikeman
Share&join🔔🕕
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
👂📩ነጋሪት በጆሮ📩👂
👩‍⚖🧑‍⚖
#የቃልዬ_ደብዳቤ_®
#ቀን_20_03_2010_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
የፍቅር ደብዳቤዎች

@gGetem
@gGetem
@leoyri
​​●●◦🍃የይቅርታ መሐልይ🍃◦●●

ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡

ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡

ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡

✰ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም

@gGetem
@leoyri
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ ...
ቀናቴ ከሸሸ
ትዝታሽ ከራቀኝ
ህመም ከተሻለኝ
ሲዘነጋኝ መልክሽ 
ተተረሳኝ ድምፅሽ
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ ...
ቅስሜ ከሟሸሸ
እንደ ጋሪ ፈረስ 
የኋላው ተጋርዶኝ ..
ታሪክሽ ሰይጣኑ
ጠበል ተረጭቶበት
እየጮኸ ለቆኝ ..
ሀሞቴ ሲመርር 
ኮሶ ሲሆን ሬት 
አንጀቴ ሲደድር
እንደ ድርቃም መሬት..
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ.. .
ልቤ ከጠለሸ
ስምሽ እንደ ንጉስ
ተሽሮ በሌላ ...
ገላዬ ሲለምድ
የአዲስ ሴት ገላ 
ሁሉ ሲፈጣጠም
ሲዘጋ ክፍቱ በር 
እንዲህ ሆኜ ባይሆን 
መምጣት ጥሩ ነበር !!

(ሚካኤል.አ)

@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
የሆሄያት ህብር💐💐💐
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#አይፀለይም !

ለሁሉም ግዜ አለው ፥ ይሉትን ዘንግቼ
ያላቅሜ ፀሎት ፥ ሱባኤ ገብቼ
በፆም ተግቼ
ስጠኝ በአንዲት ጀንበር
እያልኩኝ ሳስቸግር
እርሱም ዝም አላለኝ ፥ ልመናዬን ሰምቶ
የምፈልገውን ፥ አደለኝ አብዝቶ
እኔመች አውቄው ፥ እንደምሞት ቶሎ
ለካ አይፀለይም
አታስርበኝ እንጂ ፥ ጥጋብ ስጠኝ ተብሎ።

​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©       በሜሮን ጌትነት
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ 


ምንጭ ➸ ሶልያና
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @leoyri
የሆሄያት ህብር💐💐💐
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#አይፀለይም !

ለሁሉም ግዜ አለው ፥ ይሉትን ዘንግቼ
ያላቅሜ ፀሎት ፥ ሱባኤ ገብቼ
በፆም ተግቼ
ስጠኝ በአንዲት ጀንበር
እያልኩኝ ሳስቸግር
እርሱም ዝም አላለኝ ፥ ልመናዬን ሰምቶ
የምፈልገውን ፥ አደለኝ አብዝቶ
እኔመች አውቄው ፥ እንደምሞት ቶሎ
ለካ አይፀለይም
አታስርበኝ እንጂ ፥ ጥጋብ ስጠኝ ተብሎ።

​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©       በሜሮን ጌትነት
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ 


ምንጭ ➸ ሶልያና
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @sirak6
2024/05/24 03:49:28
Back to Top
HTML Embed Code:


Fatal error: Uncaught Error: Call to undefined function pop() in /var/www/tgoop/chat.php:243 Stack trace: #0 /var/www/tgoop/route.php(43): include_once() #1 {main} thrown in /var/www/tgoop/chat.php on line 243