Telegram Web
መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
~~~~የሆሄያት ህብር ®~~~~~~
ከአልጋዬ ግርጌ ሸሚዜን ሰቅዬ
ሳልተኛ አደርኩኝ
ባይጥ እንዳይበላ ባሳብ ተንጠልጥዬ።።
🌴🌴🌴 © ሊዮ ማክ @Leoyri
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
@gGetem
@gGetem
@gGetem
#የሔርሞን_ማስታወሻ



...........እውነት ሁሉም እንደነገርኩሽ ነው፤ድሮ የምታቂት ያቺ አመለ ኩሩ ልጅ አገረድ ዛሬ ላይ 'ለት በ'ለት በምትፈፅመው አዳፋ ግብር በጭካኔ ጃጅታለች።
እንዴት ካልሺኝ እታለም በዘመን አመጣሽ ዘመናይነት ደራሽ ውሀ ከስሯ ተነቅላ ከብስባሽ መሀል ተገኝታለች....

ዘመኑ ዘረ-አዳምን እንደ ዳይኖሰር ዝርያ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል።
ምክንያቱም ባለንበት ጊዜ ሰው ዘሩን በቅጡ እንኳን ተክቶ እንዳያልፍ ወንድ ከወንድ ሴቷም በተመሳሳይ ከሴቷ ጋር ጋብቻን ይፈፅማሉ።
.......ይህን ተቋቁመው ያለፋት ደግሞ ድንገት ያለ መተማመን ቢያረግዙ በየቀዬው ተሸጉጠው አላፊ አግዳዊውን እናውቅልሀለን በሚሉ የተለምዶ አላዋቂዎች ሰው ለመሆን ጉዞ ያልጀመረውን ሰው ከመንገድ ያስቀሩታል።
ኡፍፍፍ እታለሜ እንዴት ብዬ ልንገርሽ መቼ በዚህ በቃና ብለሽ.....

#ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ
(ይቀጥላል)👱‍♀

የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ

for_comment @sirak6
www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
#እንዳትገረሙ
ከአቅጣጫችን በፊት — ጉዞው በመቅደሙ
እንደዚያ ነው ግብሩ — በምላስ ለቆሙ
ዘቅዝቀን ሰቅለነው — የተፈጥሮን ካርታ
እግራችን ይታያል — በራሳችን ቦታ
===||===
እያዩ ፈንገስ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👂ነጋሪት በጆሮ😋👂
#የጆሲ_ደብዳቤ_®
#ቀን_20_02_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
የሆሄያት ህብር📝📝
#የሔርሞን_ማስታወሻ ...........እውነት ሁሉም እንደነገርኩሽ ነው፤ድሮ የምታቂት ያቺ አመለ ኩሩ ልጅ አገረድ ዛሬ ላይ 'ለት በ'ለት በምትፈፅመው አዳፋ ግብር በጭካኔ ጃጅታለች። እንዴት ካልሺኝ እታለም በዘመን አመጣሽ ዘመናይነት ደራሽ ውሀ ከስሯ ተነቅላ ከብስባሽ መሀል ተገኝታለች.... ዘመኑ ዘረ-አዳምን እንደ ዳይኖሰር ዝርያ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል። ምክንያቱም ባለንበት…
የሔርሞን_ማስታወሻ







         ኡፍፍፍፍ መቼ በዚህ በቃና ብለሽ እታለም ከዚህ የእግር ብረት ከሆነ የአለም ፈተና ሲወድቁ  ሲነሱ አልፈው በስንት እና ስንት እንግዳ ሀሳብ ሲናጡ ከርመው ለትዳር የበቁት ደግሞ ፊርማቸው ገና ቀለሙ በውል እንኳን ሳይደርቅ በበነጋው ለፍቺ ፊት እና ኃላ እየተማሩ ሰርክ የፍርድቤቱን ደጃፍ ከአፍ እስከ ገደፍ የሞሉት እነማን መሰሉሽ...?!......እኚው ትናትን "በሆታ" ተሞሽረው ዛሬ ጎጃቸውን በዋይታ የሚያጠናቅቁ የሁለት አለም ተጋሪዎች ናቸው።

        እታለሜ መቼም ይህን ስታነቢ ትናንት  በችግር ምክንያት ትተሻት  የተሰደድሺው ያቺ ሚስኪን በባህሏ እና ፈሪሀ እግዚአብሔር የነበራት ያቺ ሀገር በእውን መሆኗን ለማመን ከራስሽ ጋር ሙግት እንደገጠምሽ እርግጠኛ ነኝ።



  .....ግን በዚህስ ቢያበቃ ጥሩ አይደል ከላይ የገለፅኩልሽ ጥንድ ተጋሪዎች ይህን በጥረታቸው እና በፈጣሪ እርዳታ ቢሻገሩትም ዘመን ቀመስ በሆነ እንግዳ ትምህርት ሴቲቱ ተሰብካ አራርቆ መውለድ አልያም ቤት፣መኪና፣ንብረት፣ኮተት፣ወዘተ...መስፈርት ቀዳሚውን ቦታ ይይዙና አልኩሽ ያለ እኚህ መስረተ በሌላቸው ተልካሻ ምክንያቶች መላ አካላቷ እንደ ጦር ሜዳ መሬት እየተከፋፈተ ይቀበራል።በዚህም ዘረ-አዳም ለአራተኛ ጊዜ ከመፈጠር ደጅ ሳይሳካለት እንደመከነ ይቀራል እልሻለው።

መቼም ይህን ስልሽ ይህ ነገር ለወንድየውም የለውም ማለትሽ አይቀርም😭😭😀 እኔ እስካገባደድኩት እድሜ አልሰማሁም ምን አልባት አድሮ በነጋ ቁጥር የዚች ባልተኛ አለም ነገር መላ ቅጡ ስለማይታወቅ መፈብረኩ አይቀሬ ነው....

🛖ሔርሞን ነኝ የዳር ሀገሯ
           🏙በስደት ላለሺው እታለሜ
       #ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ

(ይቀጥላል)👱‍♀
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ

ለሒስ  @sirak6
ለቤተሰባዊነት www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake Péterøs👦☞Ye Yerijo Leጅ)
💫
.....እኔ ለወሎ ልጅ..
#ገጣሚ_ሚካኤል_አስጨናቂ
#አንባቢ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tgoop.com/leoyri
www.tgoop.com/gGetem
💯 quality 👉👌
Plc share&Join
🎬&📶
#Mâŕťå_Žèŵđų (ማርዘዊ)
━━━━━━━━━━━━
#የትውልዴ_ዕጣ

እንዳያልፍ ካ’ባት ደጅ ፥ አያት ከዋለበት
በጠዋት ቢነቃም ፥ ፀሃይ ዘገየበት
የኔ ዘመን ትውልድ ፥ ከማር የወጣ ዕቃ
የትም ዓሳ ልሶት ፥ ላገሩ ማይበቃ

ጊዜ አደናግሮ ፥ አደረገው ሰብይ
አንጋጦ በተስፋ ፥ ይጠብቃል ነቢይ
ሲያጣ ሲመክን ፥ የጠበቀው ከላይ
ጥያቄ በመውለድ ፥ ይጨብጣል ድንጋይ

ደሙም እንደገና ፥ ተከዜን ያስንቃል
ጥያቄ አስቀርቶ፥ የሱ ጀምበር ያልቃል፡፡
 
​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
        ✍🏽© የሱፍ ግዛው ዓለምጉድ
    ╰══•••┈ 📔 ናፍቆት
               ┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
                          ፳፻፲፪ ዓ.ም

ምንጭ ➸ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @leoyri
ሸርተትበገዛ አንደበት
እመዳፌ ያለች ግልጦሽ ያልዳሰሳት
መታፈሪያ ጥዑም መለያ ቢሆናት
ፈቀቅ ከእምነት ጥግ፤
እንዲሁ በቀላል ለይስሙላ ወገግ፤
ሆኖ ቢጎበኛት....
አረፈችው አሉ....
          ብትደክም በጩኸት።

ደግሞ አሉ እኮ ነው፤
ባልተገራ ወሬ ለ'ውነት ያልቀረበ
በማይፀና ልሳን ሀሠት  የተራበ።
ከእውነታ ውሎ ከሀቅ ያላደረ
   ብዙ ልሳን አለ!!!!!
® #ሊዮሪ
@leoyri
@gGetem
18/12/2013ዓ.ም (WR)
🔎🔎ሀቅን ባናስተውላትም እንመለከታታለን!!!!!!!
ላጤዎቹ Part 2
@Ethio_tereka
🎬 ላጤዎች ክፍል 2

ደራሲና ተራኪ ሀኒ ያባቷ ልጅ ና አስረስ አየለ



ሼር ያድርጉ
"አእምሮህን እንደ አንድ የአትከልት ስፍራ ተመልከተው:: አንድ የአትከልት ስፍራ የተለያዩ አትክልቶችን የሚያበቅለው ስለዘራህበት ብቻ አይደለም፡፡ ብትዘራበትም ባትዘራበትም አረምም ሆነ "ወፍ ዘራሽ ነገሮችን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ ጥሩ ዘርን ከዘራህበት የዘራሀበትን ጥሩ ዘር ያበቅላል፡፡ መጥፎ ዘር ከዘራህበትም እንዲሁ፡፡ ምንም ዘር ካልዘራህበት ደግሞ ይህንና ያንን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ አእምሮህም እንዲሁ ነው፡፡ በገጠመኞችና በተለያዩ ሁኔታዎች የሚገቡ “ወፍ-ዘራሽ” ሃሳቦችን ማብቀሉ ካልቀረ ፤ መልካም ነገርን እየዘራህበትና ጥሩ ጥሩውን እያሰብከ ጣፋጭ ሁኔታዎች መፍጠር ትችላለህ፡፡

   👤ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
_ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _
📚ማጋራት መተሳሰብ ነው !
      @sirak6
      www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
🇪🇹 የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ዘለሽ ከበላዬ ፥ አፍፌሽ በክንዴ
ለማሰስ የበዛኝ ፥ አካልሽ ሁዳዴ
አየር እያማገ ፥ ሲፈስ ባካሌ
ልቤ ሲንሸራተት ፥ ፍቅርሽ ነው ክልሌ !

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© አብርሀም ተክሉ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ አብርሀም-ተክሉ
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @Leoyri
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
ነጋሪት በጆሮ😋👂
#የጆሲ_ደብዳቤ
#ቀን_01_01_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
የጥበብ ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
Audio
ዛሬን ይመርብህ
ገጣሚ፦ አዜብ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
@sirak6
@gGetem
የማለውቀው ምክኒያት
ክፍል አንድ

"አያሌው ሞኙ ሰው አማኙ "
የሚለው የሀገሬ ዜማ ለእኔ የተዜመ እስኪመስለኝ ድረስ ተበሳጨው። በእርግጥ ያበሳጨኝ ለሶስተኛ ጊዜ #ሴት አምኜ የልቤን በር ከፍቼ ያስገባኋት ሴት እንደከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ እርሷም ለምክኒያትነት በማይበቃ ነገር ተለየችኝ። ደግሞ እኮ ገና በተለያየን በሁለተኛ ቀናችን ሌላ ፍቅርኛ መያዟን ስሰማ ነው።አቤት ፍጥነት መቼም አጃኢብ ነው።

ከመጀመሪያዋ ጋር የተለያየነው ከአመታት  #ከበፊት ከተለያየችው ፍቅረኛዋ ጋር በሁሉ ነገር ስለምታነፃፅረኝ ነበር።  አቤት የመጀመሪያዋን ባወኩት እንዴት ያለ መልዓክ መሰላቹ (ሴጣን) የእርሱ እዳ ነው የተረፈኝ።

ሁለተኛዋ ደግሞ በጣም ችኩል ናት እንዴት ልወዳት እንደቻልኩ እንጃ ሲበሳ ስጦታ የምትወድ ሰር-ፕራይስ ካልተደረኩ የምትል ነበረች። እኔም እርሷን ለማስደሰት ዱምቡሎ አልቀረኝም ሁሉን ጨረስኩ።
ታዲያ ወንድ ሲያፈቅር ምን የማያደርገው የለ እኔም እርሷን ከእኔ ዘንድ ለማቆየት ብዙ ሞከርኩ ግን አልሆነም ሳንቲም ጨረስኩ #በገቢ የተሻለ ተገኘ ሄደች።

  በጆሲ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
የማላውቀው ምክነያት
ክፍል ሁለት
ሶስተኛዋ በፍቅር ክንፍ ያለች ነበር የመሰለኝ። ነገሩ ግን ከመክነፍ ያለፈ ሆነና በረረች እኔም ከመጀመሪያዋ እንደተማርኩት ከሁለቱ አመዛዝኜ የተሻለች ስለመሰለችኝ በረራዬን በእርሷ ልክ ለማድረግ አጣጣር ጀመር። ስልክ ስናወራ ጆሬዬ እስኪግል ነበር ለሊትማ እንቅልፍ ለምኔ እንደ ቤተ መንግስት ጥበቃ  የለሊት ፈረቃ  ስልክ ላይእንዳፈጠጥን ንጋትን የሚያበስረው የሰፈራችን ጆሮ ይጮሃል። ጠዋት ፀሀይ ከእልፍኟ ሳትወጣ ለማኝ ሳይፀዳዳ የፁፍ መልዕክት ትልካለች።
አንድ ቀን ታዲያ ስልኬ ዘጋ ለሳምንታት የእንቅል ጥም የዛለው ሰውነቴ እንቅልፉን በነፃነት አጣጣመ። ለሊቱን ሳልገለበጥ አደርኩ። ጠዋት ስነቃ ድባቴ የለ መፍዘዝ የለ እነንቃት እነ ትጋት ብሩህ የሆነ የማሰብ ችሎታ ተክተልትለው በውስጤ ፈሰሱ እንቅልፍ ለጤና አስፈለጊ መሆኑን ተገለጠልኝ። 

ቀትር ላይ የተዘጋው ስልኬን ሰከፍት ያልተሳካ ጥሪ መዓት ስልኬ ላይ ይዘንብ ጀመር። መልሼ ደወልኩላት። አነሳችው ተበሳጭታ ነበር እንደውም አራስ ነበር ሆናለች የሚለው ጥሩ አገላለፅ ይመስለኛል። ማታ ምን እንደሆንኩ የኔን ምክኒያት ሳጠይቅ ስለማትወደኝ ነው ለእኔ ስለማታስብ ነው ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ተናግራ ማታ ከስራ ስትወጣ ደውልልኝ ብላ ስልኩን ዘጋችው።
 
በጆሲ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
የማላውቀው ምክኒያት
ክፍል ሦስት
አመሻሽ ላይ ከስራ ስወጣ በጎዳናው እንደ ጉንዳን የሚርመሰመሱትን ሰዎች እየተመለከትኩ አንድ የጓደኛዬን ግጥም ማንሰለላሰል ጀመርኩ።

ትርምስ አንግሶ በተቃኘ አለም
ማርመምን መናፈቅ የሚገርም አይደለም
የሃሳብ ብዘሃነት ሰው የመሆን አውነት
ባለማግኘት ቅዠት
አዕምሮም ቢጠፈር በገለጣት ህይወት
ለአፍታ እድሜው እንጂ አይድንም ከመሞት
በምኖር ምህዳር የህይወት መዝገቡ በተገለጠበት
ከችግር ቁልቁለት አልሞ ለማቅናት
ቢጥርም ባይጥርም
ሰው ከተፃፈለት እጣ ፈንታ አይዘልም።
             @ ገጣሚ ሊዮ ማክ(ሲራክ)

ይህንን ግጥም እያንሰላሰልኩ ለብዙ ሰዓታት ሰለ ህይወት ራሴን ስጠይቅ ስመልስ ሳወተጣ ሳወርድ ቅየው።  ፍቅረኛዬ ደውልልኝ ማለቷን ዘነጋሁት። እንዳለችውም እኔ ለእርሷ ግድ እንደሌለኝ እንደማልወዳት እንደማላስቦት መረጋገጫ ሆነላት። በማግስቱ ስደውል አታነሳም እርሷም ሳትሰናበተኝ ሄደች። ግን ቆይ እስኪ ንገሩኝ በየ ቀኑ በየ ሰዓታቱ መደዋወል የግድ ነው በፍቅርኛሞች ህግ ?
እንደኔ እንደኔ እንጃ.....!

  በጆሲ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
2024/06/16 00:40:58
Back to Top
HTML Embed Code: