Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1882 - Telegram Web
Telegram Web
app-release.apk
83.8 MB
አፑን አውርዱና ከ ጥቅምት 20 ጀምሮ የሚሰጠውን freshman mid ፈተና ለመውሰድ ተዘጋጁ ።
🙏1712
#MoE

በ 2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደምትችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም #የማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች፦

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
4. ሲቪል ሰርቪርስ ዩኒቨርሲቲ
5. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
6. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
7. ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት

የሞላችሁትን ምርጫ በ student.ethernet.edu.et በኩል ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@remedial_tricks
15🔥1
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የተቋሙ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም  መሆኑን አሳውቋል።

በዚህም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ውጤት ያመጣችሁና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ በዋናው ግቢ፤ በ2017 ዓ.ም የማካካሻ ትምህርታችሁን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች ትምህርታችሁን ስትከታተሉ በነበራችሁበት ካምፓስ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@freshman_tricks
16🔥4
#InjibaraUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@freshman_tricks
10
የጥሪ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ  ጊዜ ጥቅምት 17-18/2018 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - በዋናው ግቢ 
የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

@freshman_tricks
7🤩2
#HaramayaUniversity
#የጥሪ ማስታወቂያ

ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ ተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ

በ2018 በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የፍሬሽማን ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በሪሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠው ፈተና አማካይ ውጤት 50% እና በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ በ ጥቅምት 17 እና 18፣ 2018 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን።

@freshman_tricks
9
📣MaddaWalabuUniversity

በ2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዘዟቸው የሚገቡ፦
➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

@freshman_tricks
10
📣ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ

ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ እና 2ተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!

በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ አንደኛ ዓመት የሚያስገባ/የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ፣

በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ አንደኛ ዓመት ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና

2ተኛ ዓመት ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን

የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 17-18/2018 ዓ.ም እንዲሁም

በቅጣት ምዝገባ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን

ትምህርት የሚጀምረው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ማሳሰቢያ፡

መጠኑ 3በ4 የሆነ 4 ጉርድ ፎቶግራፍ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ አንሶላ፣ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትመጡ፡፡

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የ8ኛ፣የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት እና ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት የትምህርት መረጃዎች ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ የማይመለስ፣

ለሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት ክፍል ምደባ ፈተና እና ኦሬንቴሽን የሚሰጠው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን የትምህርት ክፍል ምደባ ያለፈው ተማሪ ባለው ክፍት ት/ክፍል ብቻ የሚመደብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ውጭ ዘግይቶም ሆነ ቀድሞ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት!!

@freshman_tricks
7
📣odabultum university

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ዉጤት አምጥታችሁ በ2018 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሬሜዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ዉጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን

ጥቅምት 17 እና 18 ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ጥቅምት 19፣ 2018 ዓ.ም መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

@freshman_tricks
4
📣 Debre Markos University

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የየ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

@freshman_tricks
4
#Woldia University

በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከትምህርት ሚኒስቴር ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አድስ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲያችን በመደበኛ መርሀ ግብር የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎችና በ 2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር በተለያዩ ምክንያቶች መልሶቅበላ/Withdrawal በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 17--18/2018 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታደርጉ እያሳወቅን በምዝገባ ወቅት፡

የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ኦርጅናልና ኮፒ፣

ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪቢት ኦርጅናልና ኮፒ፣

አራት 3X4 የሆኑ ጉርድ ፎቶ ግራፎች

የሌሊት አልባሳት እና የስፓርት ትጥቅ አሟልታችሁ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም፡፡

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች መማር ማስተማር ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

@freshman_tricks
7
📣DebreTaborUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በቅርቡ በሂሳብ ትምህርት ላይ የውጤት ማስተካከያ ስለተደረገ በድጋሜ በትምህርት ሚኒሰቴር ውጤት ማሳዎቂያ ፔጅ ላይ ውጤታችሁን ቼክ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ምደባችሁን ይፋ እንዳደረገ ጥሪ በሌላ ማስታዎቂያ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡

@freshman_tricks
12
📣 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ እና በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ሐሙስና ዓርብ ጥቅምት 13 እና 14 ቀን 2018 ዓ/ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በዚህ መሠረት በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በ2017 ትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት በተማራችሁበት ካምፓስ እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ኩልፎ (Kulfo Campus)፣ አባያ (Abaya Campus)፣ ጫሞ (Chamo Campus) እና ዋናው ግቢ (Main Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፤ ሳውላ ካምፓስ (Sawula Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉና ምዝገባ እንድትፈጽሙ እንገልጻለን፡፡

በዩኒቨርሲቲው አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ከታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement

ማሳሰቢያ፡-

1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንዲሁም አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት


@freshman_tricks
50👍1
ከዚህ ቀደም ከፍላችሁ ቆይታችሁ ክፍያው 2 ቀን ያለፈው ከሆነ  ወደ አፑ ለማዞር የከፈላችሁበትን ፎቶ ወደ አፑ የምትልኩ ተማሪዎች መጀመሪያ ላይ Admin ላይ በመግባት ሁለት ቀን አልፎኛል በማለት ስልክ ቁጥሩ የራሳችሁ መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ነው የምንበቀበለው ። payment የምትልኩበት ቀን ሁለት ቀን ካላለፈው ግን በቀላሉ ማረጋገጥ ስለምንችል ሀሳብ ሳይገባችሁ መላክ ትችላላችሁ ።
12
#UniversityOfKabridahar

ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ከጥቅምት 13 እስከ 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አስር 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@freshman_tricks
6
2025/10/25 14:41:21
Back to Top
HTML Embed Code: