tgoop.com/fkr_be/603
Last Update:
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(((አድዋ)))
°ዛሬን በትላንት ውስጥ°
ክብር..
ሉአላዊነት..
የተፈጥሮ ሀብት..
ይህን ሁሉ በአንድ በያዘች ሀገር፤
ቆራጥ ጀግና በተወለደበት ምድር፤
......
የሞትን ፅዋ ሊያጠጡን፤
ጀግንነት ክብራችንን ሊነጥቁን፤
ከጉልበታቸው በታች ሊያረጉን፤
በኛ ላይ ሀያል ሊሆኑብን፤
ፋሺስት ጣሊያን ገብ ሀገራችን፤
.......
ግን ግን.............
በአድዋ ላይ ተዋጋን..
ተዋግተንም ታሪክ ሰራን..
ታሪካችንም ተፃፈልን..
ኣያቶቻችን ነፃ አወጡን....
አጥንትና ደማቸውን ለግሰው...
በአንድነት በፍቅር አቆሙን....
.........
በሰይፍ በጋሻ ተዋግተው....
በባዶ እግር ተሯሩጠው...
የፈጣሪን ክብር ለማሳየት ...
አድዋ ላይ ታቦት ይዘው...
ቅ.ጊዮርጊስን ከፊት ለፊት ...
አሰልፈው..
በእለተ ቀኑ ጉድ አረጉ፣
ለኢትዮፕያዊነት ተሸነፉ፣
ለባንዲራ ክብር ወደቁ፣
ደማቸውን ኣፍስሰው፣
አጥንታቸውን ከሰከሱ፣
የዛሬይቱን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል፣
ታሪክ ፅፈው ድል አርገው አለፉ።
..........
እናም የደግና ልጅ........
በዚህ ነገር ብዙ እንማር
አንድነት...
መተሳሰብ....
ፍቅር.....
የጋራ ሀሳብ....
ከምንም በላይ ደግሞ....
ሀገር......
.....
በአንድነት ውስጥ ትኖራለህ..
ከተሳሰብክ ፍቅር ካለህ ትከብራለህ...
በጋራ ሀሳብ ከተስማማህ፤
በልዩነት ውስጥ ከተዋደድክ፤
የእኔ-ነት ስሜትን አጥፍትህ፤
ቀእኛ-ነት ስሜት ከተካህ፤
በሉአላዊ ሀገር ላይ ትኖራለህ።
......
ፀብና ግጥትን
ብሎም ጦርነትን
አትመኝ ወጃጄ....
ታሪክ እንዳያይህ
ያ ያድዋ ዘመን
እንዳይታዘብህ...
ትናንትን በዛሬ
ዛሬን በትላንት ውስጥ
ፅፈው የለም እንዴ!!!!
...ሴላቪ...
አድዋ
አድዋ
አድዋ
አድዋ
አድዋ
ታሪክ ይቀጥላል
ጦርነት ግን........
💚💛❤️
✍ተፃፈ በ @Mak_bale
(((ዛሬ)))
@joftdav
@joftdav
@joftdav
BY የኔ ደብዳቤዎች
Share with your friend now:
tgoop.com/fkr_be/603