tgoop.com/fionteabewzeorthodox/12835
Create:
Last Update:
Last Update:
የሰላማ አባባሎች
+እኛ ኢትዮጵያውያን የጀግንነታችን ምልክት ሃይማኖታችን ነው፡፡
+ አሁን እናንተ ይህ የነገረ መለኮት ትምህርት እንዴት ይዋጥላችኋል ገና እኮ የምትበሉትንና የምትጠጡትን፣ የሚጠቅማችሁንና የሚጎዳችሁን ለይታችሁ የማታውቁ ሕፃናት ናችሁ፡፡ ምክንያቱም ማርና ወተት ከቤታችሁ አውጥታችሁ ሸጣችሁ አረቄ ገዝታችሁ የምትጠጡ ሰዎች ይህ የነገረ መለኮት ምግብነት ጠቀሜታማ እንዴት ይረዳችኋል፡፡
+ የሰው ልጅ ጽድቅ አስፓልት ሆኖለት ከሚመላለስበት ይልቅ እርሱ የኃጢአት አስፓልት ሆኖ አጋንንት እንዲመላለስበት ይመረጣል፡፡
+ ሰማይ የሚያክል እንጀራ ቢሰጥህ ቀና ብለህ የሰማዩን ከዋክብት ተመልከት፡፡
+ የሰው መውደቅ አምላክን እስከሞት አደረሰው
+ ገዳም መንፈሳዊ ሐኪም ቤትና መንፈሳዊ የጤና መኮንኖች መፍለቂያና ማሠልጠኛ ነው፡፡
+ የምናስተምረው ለአዋቂዎች ነው፡፡ አላዋቂና ሲሚንቶ የጠጣ መሬት አንድ ነው፣ ውኃ አይቋጥርም፣ ሁልጊዜ ደረቅ ነው፤ ለዚህ ምን ይሁን ተብሎ ያጠጡታል፡፡
+ አላስፈላጊ ኢትዮጵያዊነት በልብ መሸጥ ነው፡፡ ራስንም መለወጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የሆነ አሠራር ደግሞ _መጨረሻው የኋሊት መውደቅ ነው፡፡
+ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚመጣ ሥልጣን ሁሉ የውርደት ሥልጣን ነው፡፡
BY ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

Share with your friend now:
tgoop.com/fionteabewzeorthodox/12835