tgoop.com/fideltutorial/1186
Create:
Last Update:
Last Update:
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ፤
------------------------------------
(ሰኔ 02/2017 ዓ.ም) በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናው የሚሰጠው በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ነው።
በዚህ ዓመት በሚሰጠው የመውጫ ፈተና 190,787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ እና ከዚህም ውስጥ 102 ሺ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፈተናው በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች በሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት በበይነ መረብ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ ጨምረው ገልጸዋል።
BY Fidel Tutorial (ፊደል የጥናት አገልግሎት)

Share with your friend now:
tgoop.com/fideltutorial/1186