Telegram Web
ከላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደተሞከረው ኢዜማ እንደገና ስንል ምን ማለታችን ነው? በማለት በገለፅነው መሰረት የፓርቲያችን ማሻሻያዎች ለዘለቀታነት ከሚያስፈልጋቸው የውስጥ ግምገማ: የመዋቅርና አደረጃጀት ኹናቴ እና ተተኪ አባላትና አመራሮችን ከማፍራት አኳይ ተመልክተናል። ይህ ከመሆኑ በፊት የኢዜማ እንደገና ማሻሻያ ሀሳብ አስፈላጊነት ለምንድን ነው የሚለውን መግለፅ አስፈላጊ ነው። ፓርቲያችን ሀገራዊ ተደራሽነት ያለው እንደመሆኑ ከሚጠበቅብን ሀላፊነት አንፃር የኢዜማ እንደገና ማሻሻያ ሀሳብ በግልፅ የሚተገበርበትን አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ይጠበቅብናል።

ኢዜማን እንደገና ማሻሻል ጊዜውን የሚመጥን እና ወቅታዊውን የፖለቲካ ተለዋዋጭነት የሚስተካከል ቁመና ላይ ለማድረስ ይረዳናል። ከዚህ ቀደም ፓርቲያችን በሚመሰረትበት ወቅት የነበረው ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ የፖለቲካ ብያነ ከአሁኑ እና ወደፊት ሊመጣ ከሚችለው የፖለቲካ ውስብስብነት አንፃር ፓርቲያችን ራሱን በውስጥ ተሀድሶ በመገምገም እንደገና ማሻሻል አለበት ብለን እናምናለን። ኢዜማ ሲደራጅ የነበረው የኢትዮጵያ ነገባራዊ ፖለቲካ በአሁኑ ሰዓት የተለየ ቅርፅና ይዘት ላይ ስለሆነ በዚያው ትዪዩ ዋና ዋና የፕሮግራም: የደንብ: የፖሊሲ: የአሠራር: የአደረጃጀትና ሌሎች መስኮችን በማጥናትና በማስጠናት ብቁ ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን መሪ የፖለቲካ ድርጅት እንዲሆን ኢዜማን እንደገና መስራት ይጠበቅብናል።

የዚህ የማሻሻያ ሀሳብ የሚፈለግበት ዐበይት ምክንያቶቹ እንደሚከተሉት ቀርቀዋል።

1, በሀገር አቀፍ ደርጃ የምንታገልለት የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎች አሁናዊ ሁኔታን በመገምገም በቀጣይ ለምናደርገው የማህበራዊ ፍትህ መርሆዎች ግብ ለመምታት

2, የኢዜማ የውስጥ ደክመቶቹንና ውጫዊ ገፅታ ግንባታውን ለማሻሻል

3, የፓርቲያችን ነባር አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና አዲስ አደረጃጀቶችን ለመፍጠር

4, ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ቅድሜ ዝግጅት ለማድረግ

5, የኢዜማን ህዝባዊ ቅቡልነት ለማደስና አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ ፓርቲያችን ኢዜማ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደገና ወደ ገናናነቱ መመለስ ስላለበት እኛም እናንተ ብትመርጡን በቀጣይ ሦስት ዓመታት ውስጥ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን አድርገን እንሰራለን።

ኢዜማን እንደገና ለማሻሻል የያዝናቸው የመነሻ ምክንያቶች በሙሉ እና በቅንጅት የፓርቲያችን ህልውና የሚያረጋግጡ ናቸው ብለን እናምናለን። ከላይ የተጠቀሱትን በዝርዝር ለመመልከት በቅን ልቦና የራስን Ego (ዕብሪት) በማክሸፍ በቀጣይ ሁላችንም በመሰጠት የምንታገልላቸው የጋራ ዓላማዎቻችን ናቸው። እያንዳንዱን ነጥቦችን በአጭሩና በግልፅ ቋንቋ ማብራራቱ አስፈላጊ በመሆኑ እንደሚከተለው ዘርዝረናቸዋል።

1, በሀገር አቀፍ ደርጃ የምንታገልለት የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎች አሁናዊ ሁኔታን በመገምገም በቀጣይ ለምናደርገው የማህበራዊ ፍትህ መርሆዎች ግብ ለመምታት

ኢዜማን እንደገና ማሻሻል እንዳለብን እናምናለን። ፓርቲያችን በውስጡ ዴሞክራሲን እየተለማመደ የሚገኝ ፈር ቀዳጅ ድርጅት መሆኑ እሙን ነው። ይህ ለሰለጠነ ፖለቲካ ከሚፈለጉት ግንባር ቀደም ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በቀጣይም ኢዜማ አካታችነቱ ላይ በማትኮር በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሴቶች የሚወስኑበት: አካል ጉዳተኞች የሚመሩት እና ወጣቶች የሚሰበስቡት የፖለቲካ ጥምረት መፍጠር ይገባናል ብለን እናምናለን። ኢዜማ አካታችነቱ እየሰፋ የሚሄድ ፓርቲ ሆኖ ግልፀኝነቱ አርዓያ ሊሆን ይገባዋል ብለን እናምናለን። የማህበራዊ ፍትህ ጥያቄዎች በዋናነት ለሚቆሙለት የዜጎች የጤና አጠባበቅ: የትምህርትና አዕምሮ ማጎልመቻ ስልጠናዎች ተደራሽነትና ጥራት: የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከየተቋማቱ በመገምገም በቀጣይ ለሚከናወነው ፖለቲካ ትግል በአትኩሮት የሚሰራበትን ዘርፍ መለየትና አተገባበሩን እንደፓርቲ መምራት አስፈላጊ በመሆኑ መሠረታዊ የማህበራዊ ፍትህ አምዶችን በመለየት ለአዲስ የትግል ንቅናቄ መዘጋጀት ስላለበት ፓርቲያችን እንደገና ማሻሻያ ማድረግ ይኖርበታል ብለን እናምናለን።

2, የኢዜማ የውስጥ ደክመቶቹንና ውጫዊ ገፅታ ግንባታውን ለማሻሻል

ፓርቲያችን ከሌላ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ህግና መመሪያን በማዘጋጀት: ደንቦችን ወደ ተግባር በመለወጥ: በአንፃራዊነት የተሻለ መሠረት ላይ መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው። ቢሆንም ኢዜማ እንደሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ዕኩልነት ፍትህ ለሚያደርገው የዓላማ ፅናቱ እና ከሚጠበቅበት አንፃር ልል የአሠራር ክፍተቶችና የውስጥ ድክመቶች እንዳሉት አይካድም። በህግና በመመሪያ ፓርቲያችን ያልተማከለ ስርዓት የቀረፀ ቢሆንም ግን አፈፃፀም ላይ የሚስተዋለው የሀይልና የስልጣን ማዕከላዊነትን ማስቀረት ተቀዳሚ ሥራችን ይሆናል። የኢዜማ ከፍተኛ የስልጣን አካል የሆነው የጠቅላላ ጉባዔ ለቀጣይ 3 ዓመታት ፓርቲያችንን በአመራርነት እንድናገለግል ከመረጠን በየውይይት አጀንዳው የሚከሰተውን የሀብት ማሰባሰብ ስራን በአንድ መምሪያ አደራጅተን ለቀጣይ የሀብት አሰባሰብ የስራ ክፍልን እናደራጃለን። ከድክመቶቻችን አንዱና በአደባባይ ከሚያስወቅሰን መካከል ቀዳሚ የፓርቲ ልህቃንና ገለልተኛ ልህቃን ከኢዜማ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጥበቅ ዋና ተግባራችን ይሆናል። ስለዚህ ኢዜማን እንደገና በማሻሻል የተሻለ ቅርርብና ግንኙነት እንድኖረን እናደርጋለን።

3, የፓርቲያችን ነባር አደረጃጀቶችን ለማጠናከርና አዲስ አደረጃጀቶችን ለመፍጠር ኢዜማ እንደገና ማሻሻያ መደረግ አለበት።

የኢዜማ አደረጃጀት እንደሚታወቀው ከታችኛው የምርጫ ክልል መሠረት የተጣለለትና በመሰረቱ የፀና ፓርቲ ነው። አሃዛዊ መረጃውች እንደሚጠቁሙን ኢዜማ በምስረታው ወቅት ከነበረው መጠነ ተደራሽነት በአሁኑ ሰዓት በእጅጉ ቀንሶ እንደሚገኝ ይታወቃል። ይህ እያሽቆለቆለ ያለውን የመዋቅር ቁጥር ለመታደግ በየአስተዳደራዊ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የኢዜማን መዋቅር የሚደግፉ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ቢሮዎች ለመክፈት ፓርቲው የተወሰኑ ማሻሻያዎችን ማድረግ አለበት። ይህ በምርጫ ክልሎች የሚሳበብ ድክመትን ለማስቀረት እንዲሁም የአባላት ፖለቲካዊ ተሳትፎን ለመጨመር አስፈላጊ ማሻሻያ ማድረግ ይጠበቅብናል።

የኢዜማ እንቅስቃሴ ዘመን ያፈራውን የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሁሉም ትግል በአካል ስለማይፈፀም እንደፓርቲ 'ዲጂታል ኢዜማ' የሚል ፕሮግራም ቀርፀን በዲጂታል ዓለምና በሰው መሰል አስተውሎት የተደገፉ ስራዎችን ለመስራት ከአሁን የአደረጃጀት ማሻሻያዎችን እንደገና መፈተሽ አለበት። የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጠይ ከሚፈትናቸው የሰው መሰል አስተውሎትና የዲጂታል ውንጀላዎች አንፃር ኢዜማ ከወዲሁ ቅድሜ ዝግጅት አድርጎ ጠቅላላ ጉባዔው የፓርቲያችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ጊዜ ያመጣቸውን ዘመነኛ ዕውቀቶችን በመጠቀም ከዘመኑ ጋር ዕኩል መራመድ ይጠበቅበታል ብለን እናምናለን።

4, ለ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ቅድሜ ዝግጅት ለማድረግ ኢዜማን እንደገና ማደራጀትና ማሻሻል እንደሚያስፈልግ እንረዳለን።
እንደሚታወቀው የፖለቲካ ፓርቲዎች በዋናነት የሚደራጁት በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ተረክበው ፖሊሲያቸውን ማስፈፀምና ያመኑበት ለመወሰን ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ በየምርጫ ውድድሩ የሚከናወኑትን ሂደቶችን በማለፍ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመስረት ነው። እኛም ፓርቲያችን በቀጣይ በሚደረገው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ የየምክር ቤቶችን ወንበር መቆናጠጥ ይጠበቅብናል። ለዚህ ደግሞ የሚጠበቅብን ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ብቻ ሳይ ግዴታችንም ነው። ካለፈው 6ኛው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ በቀሰምነው ልምድና ዕውቀት በቀጣይ ለሚከናወነው ምርጫ ራሱን በአደረጃጀትም ሆነ በፖሊሲ ቁመና የደረጀ ዕጩዎችንና ተመራጮችን ለማዘጋጀት ሲባል በአዲሱ የምርጫ ቦርድ አዋጅ መሠረት ኢዜማም እንደገና ራሱን በመፈተሽ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት።

5, የኢዜማን ህዝባዊ ቅቡልነት ለማደስና አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ

ፓርቲያችን ኢዜማ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደገና ወደ ገናናነቱ መመለስ ስላለበት ኢዜማ እንደገና ራሱን ማቅረብ አለበት የሚል አቋም አለን። የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የህልውናው መሠረት በውስጡ የያዘው ፖሊሲ እና መሪዎቹ ላይ ያለው ህዝባዊ ቅቡልነት ነው። ኢዜማ ተወዳጅ አመራሮች እና የተሻሉ ፖሊሲዎችን በውስጡ ይዞ ህዝባዊ ቅቡልነትን እስካላገኘ ድረስ በቀጣይ ለሚጠብቀን ሀገራዊ ሀላፊነት ዐቢይ ተግዳሮት ይሆንብናል። የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎቹ በፓርቲያቸው አጠቃል አቋም ላይ የመተማመኛ ድምፅ እንዲሰጡ ከተደረገ በኋላ ህዝባዊ ቅቡልነት ያሳጡንን ውሳኔዎቻችን የመቀልበስ ግዴታ አለብን ብለን እናምናለን። ኢዜማ በአባላቱም ይሁን በመራጩ ህዝብ ተቀባይነትንና ቅቡልነት ለማግኘት እስከዛሬ የመጣበትንና የወሰናቸውን ውሳኔዎችን እንደገና በማጤን ወደ ግቡ መድረስ አለበት።

የኢዜማን ማሻሻያ የጠቅላላ ጉባዔው እንዲቀበል የምንጠይቅበት ምክንያቶች በዋናነት ከላይ የጠቅስናቸው ሲሆኑ እኛ በዕጩነት የቀረብነው ተወዳዳሪዎች ኢዜማን እንደገና ማሻሻል አስፈላጊነቱን ያመንበትን ምክንያቶችን አቅረበንላችኋል። የጉባዔ ተሳታፊዎች በሙሉ ድምፅ የኢዜማን እንደገና መሻሻል በመቀበል ለአገልጋይነት እንድትመርጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ዶ/ር ካሣሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቅዳሜ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሰኔ 28/29 ስለሚያካሒደው የሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን በተለይ በሥራ ሂደት የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል የህገ ደንብ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ ምክትል ሊቀመንበር ማዕረጉ ግርማ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የ #ኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
ማዕረጉ ግርማ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ፡፡

እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

ኢዜማ የሚታወቅበትን የአካታቸነት መርሕ ዕውን ለማድረግ አካል ጉዳተኞችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ትርጉም ባለው መልኩ ማሳተፍ እዳለበት አምናለሁ፡፡

የኢዜማ ልክ እያንዳንዱን የኅብረተሰብ ክፍል በማካተትና በማሳተፍ በልኅቀትና በትጋት ለድርጅታዊ ጥንካሬ መሥራት ነው፡፡
ኢዜማ በልኩ እንዲኾን ያለኝን የትምህርት፣ የሥራና የፖለቲካ ልምድ በመጠቀም በትጋት ለማገልገል ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም ዶ/ር ሙሉዓለምን ተገኘወርቅ ለሊቀመንበርነት፣ እኔ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም ወይዘሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዕጩ ዋና ጸሐፊ ዋሲሁን ተስፋዬ መልዕክት

“ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች!
ዋሲሁን ተስፋዬ ነኝ፡፡

ኢዜማ በዚህ ወር መጨረሻ በሚያከናውነው ኹለተኛ መደበኛ ጉባኤ ለዋና ጸሐፊነት ለመወዳደር በዕጩነት ቀርቤያለሁ፡፡
እንደሚታወቀው ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢዜማን በልኩ በሚል መሪ ቃል የምረጡኝ ቅስቀሳ እያከናወንሁ ነው፡፡

የኢዜማ ልክ የዳበረ ተቋማዊ ባሕልን መገንባት ነው፡፡ ፓርቲያችን ጠንካራ የሥራ ባሕል ገንብቶ ግብ ተኮር የድርጅት መዋቅር እንዲኖረው ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ያስፈልገዋል፡፡

ድርጅታችን ኹንተናዊ ተግባራቱን በጠንካራ አመራር እንዲያከናውን ያለኝን ልምድ ከስልታዊ ዕቅድ ጋር በማቀናጀት በሳል አመራር ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ፡፡

ኢዜማን በልኩ ብለን የተሰባሰብነውን አመራሮች ማለትም ዶ/ር ሙሉዓለምን ተገኘወርቅ ለሊቀመንበርነት፣ አቶ ማዕረጉ ግርማን ለምክትል ሊቀመንበርነት፣ እኔ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬን ለዋና ጸሐፊነት እንዲሁም ወይዘሮ አሰፉ ተረፈን ለፋይናንስ/ትሬዠረር ኃላፊነት እንድትመርጡ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

#ኢዜማን በልኩ! ትጋት፣ ዲሲፕሊን፣ ልኅቀት”
2025/06/25 05:41:16
Back to Top
HTML Embed Code: