የመዋቅርና የጽ/ቤቶቻችን ኹናቴ
የተወደዳችሁ የኢዜማ አባላትና የጉባዔ ተሳታፊዎች
ኢዜማን እንደገና በሚለው መሪ ቃላችን ውስጥ በጉልህ የሚታወሰው የመዋቅርና የምርጫ ክልሎቻችን አሁናዊ ገፅታ አንዱ ማሳያ ነው። ይህን ከሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩ ያደረገንን ከታች ወደ ላይ የተዘረጋውን መዋቅራዊ አደረጃጀታችን ወደ ምንፈልገው ተቋማዊ ማንነት ማድረስ እንደምንችል አምነንበት ነው። ፓርቲያችን ወደ መራጩ ህዝብ ለመድረስ መዋቅራዊ ይዘቱን ተቋማዊ ቅርፅ ማስያዝ ነው። ይህን ፓርቲ ከህዝባዊ ድጋፍ በተጨማሪ የተቋም ባለቤት ልናደርገው ይገባል። መላው ኢትዮጵያዊያን በየምርጫ ክልላቸው በጋራ በመግባባት ዘመናዊ ፖለቲካ የሚሰሩትን ኹናቴ ማመቻቸት ተቀዳሚ ተልዕኳችን ይሆናል።
ፓርቲያችን ኢዜማን ከሌሎች የሀገራችን የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚለየው የአደረጃጀት መሠረቱን ከምርጫ ክልል መጀመሩ ነው። ይህ ፓርቲው ህዝባዊ መሠረት እንዲኖሩት ካደረጉት የኢዜማ አምዶች መካከል አንዱ ነው። ፓርቲያችን በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሄድ ከተፈለገ የማያቋርጥ የመዋቅር አደረጃጀት ክትትል ያስፈልገዋል። የማህበራዊ መሠረቱን ተደራሽነትና ስፋት እንደገና በማጥናት እንደየአስፈላጊነቱ የመዋቅር ማሻሻያም ሊያደርግ ይገባል። የኢዜማ ተቋማዊ መሰረት ከዋና ቢሮው በተጨማሪ ሌሎች ክረምት በጋ የሚሰሩ 24/7 ለአባሎቻችን ክፍት የሆኑ የፖለቲካ ስራ የሚሰራባቸው ተቋማዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት።
በቀጣይ ለ3 ዓመታት በእናንተ ይሁንታ የፓርቲያችን ዋና ፀሐፊ ከሆንኩ በየመዋቅሩ የሚገኙ የምርጫ ክልሎችን ከመጎብኘት ባለፈ የእያንዳንዱ ጽ/ቤት ጉዳይ የዋና ቢሮው ጉዳይ ሆኖ ህግና አሰራር በሚፈቅደው መልኩ ሁሉም የምርጫ ክልሎች የተጠናከረ ተቋም እንዲኖራቸው ያለመታከት እሰራለሁ። የጠቅላላ ጉባዔው በሚሰጠኝና በቀጣይም የሚደራጀው የብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ አቅጣጫ የኢዜማን ተቋማዊነት ከዋና ቢሮ ባሻገር ወደ መራጩ ህዝብ ልብ እንዲዘልቅ እሰራለሁ!
ኢዜማን እንደገና!
ዶ/ር ካሣሁን ደለነ
ዕጩ ዋና ፀሐፊ

የተከበራችሁ የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ተሳታፊዎች
የተከበራችሁ የኢዜማ አባላትና ደጋፊዎች
እኔ ጌታቸው ጳውሎስ እና
ኤልሳቤጥ ሉቃስ
ከሰኔ 28-29/2017 ዓ.ም ድረስ በሚከናወነው የኢዜማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ እንደሚፈቅደው አሰራር በዚህ ጉባዔ የኢዜማ ከፍተኛ የጉባዔ ተመራጭ አመራሮች መካከል በሊቀ መንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት ለመወዳደር ታጭተናል። የከፍተኛ አመራሮች አስመራጭ ኮሚቴ ባደረገው የውስጥ ምዘና ላይ ኢዜማን በመሪነት ለማገልገል ብቁ ዕጩዎች መሆናችን ታምኖ ዛሬ ከፊት ለፊታችሁ ቆመናል።
በዚህ የፓርቲያችን ከፍተኛ የመወሰን ስልጣን ባለው የጠቅላላ ጉባዔ ፊት ቀርበን ለኢዜማ ምን እንደምንሰራ ያለንን ሀሳብ እንድናጋራ ስለፈቀዳችሁና ትኩረታችሁን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን!
ፓርቲያችን ኢዜማ ከምስረታው ጀምሮ የመጣበትን መንገድ በመገምገም ለቀጣይ ዘመን ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅ ሁሉም የሚመለከተው የፓርቲው አካል በጋራ በመወያየት ኢዜማን እንደገና ማጠናከር: ማደራጀትና ወደ ትግል ማስገባት ይኖርብናል። ለዚህም ደግሞ በቀጣይ ፓርቲውን የቀደመ ክብሩን እንደገና ለመመለስ በአጭሩ የሚከተሉትን ሥራዎችን ለማስጀመርና በብቃት ለመምራት ተዘጋጅተናል።
የጠቅላላ ጉባዔው ሀሳባችን ተቀብሎ ይሁንታ ብናገኝና ብንመረጥ የሚከተሉትን ተግባራት እናከናውናለን!
1. ኢዜማ ይዞት የተነሳው የትግል መነሻ ሀሳብ እና ዓላማ ሳይሸራረፍ ዕውን እንዲሆን እንሰራለን:
2. ድርጅታችን በመርህ ላይ የፀና እንዲሆን እና በሕዝብ ዘንድ ያለው ተቀባይነት እንዲጪምር የማድረግ ስራዎችን እንሰራለን:
3. የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎች ያለስስት የሚታገሉለት እና የሚኮሩበት ድርጅት እንዲሆን እናደርጋለን:
4. የምርጫ ክልሎዎች ራሳቸውን በገንዘብ፣በሰው እና ቴክኖዎሎጂ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ከማዕከል የቴክኒክ እና ሙያ ድጋፎችን እናደርጋለን:
5. የ7ኛው ዙር ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ብቁ: ተመራጭና ተገዳዳሪ ድርጅት እንዲሆን የማዘጋጀት ሰራዎችን ከወዲሁ እንጀምራለን:
6. አባሎቻችን ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የማንቃት: ማብቃት እና የማደራጀት ስራዎችን እንሰራለን:
7. የዜጎችን እና የአባላትን መብት እና ደህንነት እንዲከበር ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በትብብር እንሰራለን:
8. በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሀገራችን የመወሰን አቅም ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ያለመታከት እንሰራለን:
9. የብሔር ፓለቲካ ወደ ኋላ ያስቀረውን ስሁት አካሄድ በዜግነት ፖለቲካ እንዲቀየር ከሚተባበሩን ተቋማት እና ግለሰቦች ጋር እንሰራለን:
10. ኢዜማ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የመሪነት ሚናውን እንዲጫወትና ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት ማንበር ሰመናዊ ኮከባችን እንዲሆን መምሪያዎቻችንና መዋቅሮቻችን እናበቃለን:
11. የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የጥንካሬው መሠረት በውስጡ የያዛቸው አባላት እና ደጋፊዎች እንደመሆናቸው የኢዜማ አባልነት ዜጎች ወደው ፈቅደው የሚመርጡትና በአባልነት የሚታቀፉበት በማድረግ የምርጫ ወረዳዎች እንዲጠናከሩ የሚያስችሉ ስራዎችን እንሰራለን:
12. የማህበራዊ ፍትህን ማስፈን ራዕያቸው ካደረጉ ከአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ሀገራት የሚገኙ መሰል ራዕይ ካላቸው ተቋማት ጋር በጋራ እንሰራለን።
13, ሴቶች: ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች የማህበረሰባችን አካል ተደርገው በፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ከተመልካችነትና ከአድማጭነት ዘልቀው የመሪነት ሚናቸውን እንዲጫወቱ እንሰራለን።
ክቡራንና ክቡራት
ከላይ የጠቀስናቸውን ዐበይት ተግባራትን ስንከውን ከኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ: የፓርቲው ብሔራዊ አመራሮች: የምርጫ ክልሎችና ከሌሎች የኢዜማ አካላት ጋር በመቀናጀት ታላቅ ዓላማና ራዕይ ያነገበውን ፓርቲያችንን እንደገና ወደ ቀደመው ክብሩ እና ለህዝባችን ይዞት የገባውን ቃል እንዲፈፅም እንሰራለን።
በዚህ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፓርቲያችን እንደገና የመታደስና የማጠናከር ተግባር ለመፈፀም የጠቅላላ ጉባዔውን አደራ ለመቀበልና ይሁንታ ለማገኘት በታላቅ ትህትና እንጠይቃችኋለን!
ኢዜማን እንደገና!
ጌታቸው ጳውሎስ ( ዕጩ ሊቀመንበር)
ኤልሳቤጥ ሉቃስ (ዕጩ ምክትል ሊቀመንበር)