tgoop.com/ethiopiawinnetaa/828
Create:
Last Update:
Last Update:
አትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺሕ ሜትር መሰናክል የዓለም ሪከርድ ሰበረ
አትሌት ለሜቻ ግርማ ትላንት ምሽት በፓሪስ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር የ3 ሺሕ ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈ።
7:52.11 በሆነ ደቂቃ የገባው ለሜቻ ግርማ በሳይፍ ሳኢድ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ከአስራ ስምንት ዓመታት በኋላ የግሉ ማድረጉን ከዓለም አትሌቲክስ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ሌላኛው በርቀቱ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው አትሌት አብርሃም ስሜ 8:10.73 በሆነ ደቂቃ አራተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በሌላ በኩል ትናንት ምሽት በተካሄደው የፓሪስ ዳይመንድ ሊግ 5 ሺሕ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
ሌላኛዋ አትሌት እጅጋየሁ ታየ ደግሞ በርቀቱ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን የወርልድ አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
BY Ethiopiawinnet CDCR( ኢትዮጵያዊነት) 🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/ethiopiawinnetaa/828