tgoop.com/ethio_physics/659
Create:
Last Update:
Last Update:
ሩሲያ በሰማይ ላይ እርሻ ልትጀምር ነው
ሩሲያ እፅዋትን በከፍተኛ ደረጃ ለማምረት የሚያስችላትን ሙከራ ዓለም አቀፉ የህዋ ምርምር ጣብያ ላይ በሚገኘውና ኖውካ በሚሰኘው አዲሱ የምርምር ክፍሏ ልታከናውን ነው፡፡ በሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ስር ባለው ኢንስቲትዩት ኦፍ ባዮሜዲካል ፕሮብሌምስ ውስጥ የባዮሜዲካል ቤተ ሙከራ ዋና ሀላፊ የሆኑት ዩሪ ስሚርኖቭ እንደሚሉት ሙከራው ወደፊት በከፍተኛ ደረጃ እፅዋትን ለማምረት የሚችል የአትክልት ስፋራን ጠፈር ላይ ለመፍጠር ያለመ ነው፡፡
ሙከራው የሚከናወነው በቀንድ አውጣ አምሳል የተሰራ የአትክልት ስፍራን ጠፈር ላይ ባለው በዚህ ቦታ በመላክ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ እፅዋቱን በተለያዩ ወቅቶች አትክልት ስፍራው ላይ በተወሰነ ርቀት አከታትለው ሲተክሏቸው በየጊዜያቱም ምርቱን የሚሰበስቡ ይሆናል፡፡ በቦታው የሚተከለው የመጀመሪያው አትክልት የናፓ ጎመን ሊሆን እንደሚችልም ዩሪ ስሚርኖቭ ጠቁመዋል፡፡ ታድያ ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ የህዋ ተመራማሪዎቹ ለመመገብ ሲፈቀድላቸው የተወሰነው ደግሞ ወደ ምድር እንደሚላክ ተነግሯል፡፡ ወደፊትም የህዋ ተመራማሪዎቹ አዝዕርት፣ ስራ ስሮችን እና ቲማቲምን በቦታው ያመርታሉ ሲሉ ዩሪ ገልፀዋል፡፡
Join 👉 www.tgoop.com/ethio_physics
BY Ethio Physics 🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/ethio_physics/659