tgoop.com/ethio_physics/658
Last Update:
International Space Station (ISS)
አለምአቀፉ የጠፈር ጣቢያ
#ክፍል_፩
ይህ ጣቢያ አምስት ታላላቅ የጠፈር ኤጀንሲዎች በጋራ ያቋቋሙት የጠፈር ምርምር ጣቢያ ሲሆን፤ እያንዳንዱ የጣቢያው ክፍል ከምድር በSpace Shuttle ተጭኖ ወደ ጠፈር ከተወሰደ በኋላ አዛው ጠፈር ላይ ተገጣጥሞ አሁን የያዘውን ቅርፅ ሊይዝ ችሏል። በዚህ መቹ ሰው ሰራሽ Low Earth Orbit ሳተላይት በውስጡ ብዙ ምርምሮች ይካሄዳል። እነዚህም፦ ማይክሮ ግራቪቲ፣ ስፔስ ኢንቫይሮሜንት ምርምር ላብራቶሪ፣ አስትሮ ባዮሎጂ፣ አስትሮኖሚ፣ ሜትሮሎጂ፣ ፊዚክስ እና ሌሎች ተዛማች ሳይንሶች ናቸው።
ጣቢያው በተጨማሪም ለጨረቃ እና ማርስ የሚያገለግሉ ስፔስ ክራፍቶችን እና በነዚሁ ፕላኔቶች ለረጅም ግዜ ተልዕኮ( long-duration missions) የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ይመረምራል፣ ይፈትሻል።
ሳተላይቱ በቅርብ ምህዋር 418Km እና በማዶ ምህዋር 422Km ከምድር ርቆ ምድርን በቀን 15.49 ግዜ በሚገርም ፍጥነት ማለትም 27,600Km በሰዓት በሆነ Orbital speed እየተምዘገዘገ ይዞራታል።
ይህ 440,725ኪ.ግ የሚመዝን ሳተላይት በውስጡ 101.3KPa ወይም 1atm. አትሞስፌሪክ ግፊት ያለው ሲሆን በውስጡም 79% ናይትሮጅን እና 21% ኦክስጅን በውስጡ ይዟል፤ ይህ ደሞ ምድር ላይ ካለው የአትሞስፌሪክ ግፊት እና የኦክስጅን-ናይትሮጅን ንፅፅር ጋር ተመሳሳይ ያደረገዋል፤ ይህ ደሞ ማንኛውም ሰው በዚህ ሳተላይት ውስጥ ያለምንም ተጨማሪ ኦክስጅን መኖር ያስችለዋል።
ይቀጥላል... join 👉 @ethio_physics 👉 @ethio_physics
BY Ethio Physics 🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/ethio_physics/658