tgoop.com/ethio_physics/655
Last Update:
#ከስቴፈን_ሀውኪንግ_አንደበት
#የተደገመ
የአርክቲክ እና የአንታርክቲክ በረዶ ግግር መቅለጥ ከፀሀይ መነጭቶ በግግር በረዶዎቹ ላይ ተንፀባርቆ ወደ ስፔስ የሚመለሰውን የሶላር ኢነርጂ መጠን ይቀንሳል፣ ይህም ማለት ከፀሀይ የመነጨው አብዛኛው ሶላር ኢነርጂ እዚሁ ምድር ላይ ታምቆ ይቀራል ማለት ነው፣ ይህ ደሞ በምድር ላይ የሙቀት መጠን እንዲጨምር ያደርጋል በዚህም ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ ይፈጠራል፣ ለውጡ በምድር ላይ ያሉ ጥቅጥቅ ደኖችን(አማዞን ጫካን) ጨምሮ ለሰደድ እሳት ተጋላጭ እንዲሆኑ መንገድ ይከፍታል፣ የደኖች መመናመን ደሞ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚለቀቁ እንደ Carbon dioxide የመሳሰሉ በካይ ጋዞች ከአትሞስፌራችን ላይ ሳይወገዱ እዚሁ አትሞስፌራችን ላይ ታምቀው እንዲቀሩ ያደርጋል።
በዚህም ምክንያት በከባቢ አየራችን ላይ የሙቀት መጠን ከበፊቱ በጣም ይጨመራል ይህ ደሞ ከባህር ብዙ መጠን ያለው carbon dioxide እንዲወጣ እና hydride ወደ ocean floor እንዲሰርግ ያደርጋል። እነዚህ ክስተቶች ግሪንሀውስ ኢፌክት(greenhouse effect) እንዲጨምር ያደርጋሉ እናም የሙቀት መጠኑ ከበፊቱ ይበልጥ በጣም ይጨመራል። በአስቸኳይ የአየር ንብረት ለውጡን ወደ በፊቱ መመለስ ይኖርብናል። ከቻልን!
"ፕሮፌሰር ስቴፈን ሀውኪንግ (ቲዎሮቲካል ፊዚስት)"
እኤአ (1942 - 2018)
ከስቴፈን ሀውኪንግ አንደበት
ተፃፈ በ አዲስ
ፊዚክስ፣ስነ ፈለክ፣ጥልቅ ሕዋ እና ተዛማጅ ሳይንሶች ይዳሰሳሉ ☄🌓🌞💫💥
join us 👉 @ethio_physics
BY Ethio Physics 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/ethio_physics/655